2012-01-16 14:19:10

ስደተኞች እና አዲስ አስፍሆተ ወንጌል


ትላትና 98ኛው ዓለም አቀፍ የስደተኞች እና የተፈናቃዮች ቀን ታስቦ መዋሉ ሲገለጥ፣ ቀኑንም ምክንያት በማድረግ ቅዱስ አብታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛም ትላትና እኩለ ቀን ጸሎት RealAudioMP3 መልአከ እግዚአብሔር ከመድገማቸው ቀደም በማድረግ የዚህ 98ኛው ዓለም አቀፍ የስደተኞች እና ተፈናቃዮች ቀን ስደተኛ እና አዲስ አስፍሆተ ወንጌል በተሰኘው መርህ ቃል ዙሪያ አስተምህሮ ማቅረባቸው የቅድስት መንበር መግለጫ ሲያመልክት ቀኑን ምክንያት በማድረግ በአገር አቀፍ ደረጃ በኢጣሊያ ፐሩጃ በሚገኘው ካቴድራል ያረገውን መሥዋዕተ ቅዳሴ የመሩት የከተማይቱ ሊቀ ጳጳሳት የኢጣሊያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ምክትል ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ ጓልቲየሮ ባሰቲ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ ዕለቱ ለኵላዊት ቤተ ክርስትያን ለብሄረ ኅብረተሰብ ጭምር አስፈላጊ መሆኑ ገልጠው፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ 215 ሚሊዮን ስደተኞች መኖራቸው በማስታወስ ከዚህ አኳያ እጅግ ትኵረት የሚጠይቅ ጉዳይ መሆኑ ለማንም የተሰወረም አይደለም፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሕዝቦች ከቦታ ቦታ መዘዋወር ለማኅበራዊ ለባህላዊው ሕይወት በክፈተኛ ደረጃ ለቤተ ክርስትያን አቢይ ተጋርጦ ነው። ይኽ ማኅበራዊ ክስተት ያለው አንገብጋቢነት በጥልቀት በመገንዘብ፣ ቅዱስ አባታችን ዘንድሮ ቀኑ ስደተኛ እና አዲስ አስፍሆተ ወንጌል በተሰኘው ቃል እንዲመራ መወሰናቸውም አስረድተዋል።
የክርስትያኖች ስደተኞች ብዛት እጅግ ከፍ ያለ ነው፣ በሳቸው ሐዋርያዊ እረኝነት ሥር በሚመራዊ ርእሰ ሰበካዎች ለተለያዩ ስደተኞች ማኅበረ ክርስትያን ቤተ ክርስትያን መሰጠቱንም ገልጠው፣ ቤተ ክርስትያን አማኝም ይሁን ኢአማንያን ወይንም የሌሎች ሃይማኖት ተከታዮች አለ ምንም ልዩነት አገልግሎት በመስጠት፣ የተሟላ ሰብአዊ ሕንጸት በማቅረብ፣ በተለያየ ዘርፍ በስደተኛው እና በአስተናጋጁ አገር መካከል መተዋወቅ እና መቀራረብ የሚደገፍ ክርስትያናዊ ሰብአዊ ደገፍ በማቅረብ አስፍሆተ ወንጌል እና አዲስ አስፍሆተ ወንጌል በመለያየት ተልእኮዋ ገቢራዊ ታደርጋለች ብለዋል።
አዲስ አስፍሆተ ወንጌል ሲባል ሌላ ወንጌል ማቅረብ ማለት ሳይሆን የአስፍሆተ ወንጌል አቀራረብ ሥልት ማደሰ ማለት ነው። በርግጥ የጌታ ቃል ዘወትር አዲስ ነው። ስለዚህ ስብከተ ወንጌል ወቅታዊው ማኅበራዊ ኤኮኖሚያዊ እና ሰብአዊ ሁኔታ ግምት መስጥት በሚለው ፍሬ ነገር ላይ ያነጣጠረ ነው።
ከውጭ አገር ለከፍተኛ የትምህርት ዕድል በከተማይቱ የሚገኙት የመንበረ ጥበብ ተማሪዎች ብዛት 120 ሺሕ መሆኑ ጠቅሰው ይኸንን መሠረት በማድረግም በፐሩጃ ክፍለ ሃገር 120 ቋንቋዎች እንዳሉ ገልጠው፣ ስለዚህ ለዚህ ኅብረስደተኛው የሚቀረበው የወንጌላዊ ተልእኮ አገልግሎት ይኸንን ሁሉ ግም የሚሰጥ ብቻ ሳይሆን፣ ለስደተኛው ከስደተኛው ጋር በመሆን ክርስትያናዊ ሰብአዊ እና ማኅበራዊ ሕንጸት ማቅረብ የሚል ሥልት የሚከተልም ነው። ቤተ ክርስትያን ሕገ ወጥ ስደተኛና ሕጋዊ ስደተኛ በሚለው ፖሊቲካዊ አገላለጥ ሳይሆን የአንድ አባት ልጆች መሆናችን ላይ በጸናው እምነት ተደግፋ አገልግሎት በማቅረብ የስደተኛው ሰብአዊ ክብር መብት፣ ፈቃድ እንዲከበር ካለ መታከት አገልግሎት እንደምስተጥ ገልጠው የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.