2012-01-16 14:20:58

ሥነ ጥበብ ለአዲስ አስፍሆተ ወንጌል ጎዳና


እ.ኤ.አ. ቅዳሜ ጥር 14 ቀን 2012 ዓ.ም. በሮማ ከቫቲካን ውጭ የአገረ ቫቲካን ግዛት ክልል በሚገኘው ጳጳሳዊ የላተራነንሰ መንበረ ጥበብ የሮማ ሰበካ ከባህል ጉዳይ ተንከባካቢ RealAudioMP3 ጳጳሳዊ ምክር ቤት ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ሥነ ጥበብ ለአዲስ አስፍሆተ ወንጌል ጎዳና በሚል ርእስ የተመራ አውደ ጥናት መካሄዱ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።
ይኽ የተካሄደው ዓወደ ጥናት እንዲነቃቃ ያደረገውም፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ውበት፣ ቅዱስ አጎስጢኖስ እንደሚለውም ጥንታዊ ነገር ግን ሁሌ አዲስ ወደ ሆነው ፍጹም ውበት የሚመራ መሆኑ በማብራራት፣ በአስፍሆተ ወንጌል እና በውበት መካከል ያለው ግኑኝነት በማጣመር የሰጡት ሥልጣናዊ ምዕዳን መሆኑ ሲገለጥ፣ ይኸንን ቋሚ ሐሳብ በሦስት ደረጃ እርሱም በቲዮሎጊያ በመገናኛ ብዙሃን እና በሥነ ጥበብ ሥር የተደገፈ አስተምህሮ የተሰጠበት አወደ ጥናት እንደነበርም የቅድስት መንበር መግለጫ ያመልከታል።
የቲዮሎጊያው ዘርፍ ማእከል ያደረገ አስተምህሮ ያቀረቡት የዳግመ አስፍሆተ ወንጌል ጉዳይ የሚከታተለው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ ሪኖ ፊዚኬላ መሆናቸውም ሲገለጥ፣ ብፁዕነታቸው፣ ውበት ለአስፍሆተ ወንጌል ጎዳና መሆኑ ዘክረው፣ የክርስትናው እምነት ከንድፍ እና ከቅብ ባጠቃላይ ከሥነ ጥበብ ጋር ያለው ግኑኝነት አዲስ ሳይሆን፣ ጥንታዊ እና ወቅታዊም ነው። የሰውን ልጅ ለማዳን ገዛ እራሱ ሰው ሆኖ የወረደው ፈጣሪ-እግዚአብሔር እና የዚህ የማዳን እቅድ ፍጹም ወበት የክርስትናው በሥነ ጥበብ አማካኝነት ሲያቀርብ ቆይተዋል፣ እግዚአብሔር ገዛ እራሱን በመግለጥ ፈቃዱ ላይ ሱታፌ ያለው ሥነ ጥበብ በመሆንም፣ እራሱን የገለጠውን እግዚአብሔር በውበት አማካኝነት የተገለጠውን ለመግለጥ የተደረገው እና በመደረግ ላይ ያለው ሥነ ጥበባዊ ጥረት አሁንም ያለ ነው። ጥንታውያን አቢያተ ክርስትያን በውስጣችው ያለው ቅዱስ ምስሎች እና ቅቦች፣ በሥነ ግጥም፣ በሥነ ድርሰት እና ሥነ ቅብና ሥነ ሙዚቃ ቋንቋዎች አማካኝነት የእግዚአብሔር ምሥጢር ለሰው ልጅ ሲገለጥ ቆይተዋል፣ ይህ ቅዱስ ባህል አሁንም ያለ ሆኖ በሊጡርጊያ አማካኝነትም የሚገለጥም ነው። ሊጡርጊያ ያለው ውበት ለገዛ እራሱ የሚሰብክ ቋንቋ ነው።
ውበት የእግዚአብሔር ምሥጢር መግለጫ መሆኑ ያለው ልዩ መብት፣ በአሁኑ ወቅት የተዘነጋ እንደሚመስል አስታውሰው፣ በተለይ ደግሞ ጊዚያዊ ጠፊ ዘላቂነት በሌለው ግኡዛዊ ውበት ላይ እየተተኮረ ውበት ያለው ጥልቅ ትርጉም እየተዘነጋ መሆኑ ገልጠው፣ ወበት ያለው ጥልቅ ትርጉም ዳግም በመጎናጸፍ የአስፍሆተ ወንጌል ጎዳና መሆኑ መመስከር ይኖርብናል እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ ይጠቁማል።
ሮማ በሚገኘው ላ ሳፒየንዛ መንበረ ጥበብ መምህር የሥነ ሕንፃ ንድፍ ሊቅ ፓውሎ ፖርቶገዚ ባቀረቡት አስተምህሮ፣ ሮማ ከተማ ላይ ያተኮረ የሥነ ሕንፃ ንድፍ መሠረት በማድረግ፣ ሮማ በዚህ ሥነ ጥበብ አማካኝነት የእምነት መዝሙር የምትዘምር ከተማ ነች። ሕንፃዎችዋ፣ ሓውልቶቿ፣ ታሪካዊ ቅርሶችዋ በውበት አምካኝነት የእዚአብሔር ምሥጢር የሚያበሥሩ ናቸው፣ የፈጣሪ በሌላው መልኩም የክርስቶስ ውበት የሚጎላባት ከተማ ነች። ዶስቶቪዝኪ ‘የትኛው ውበት ነው ዓለምን የሚያድን’? በማለት ያቀረበው ጥያቄ አስታውሰው፣ በውስጣችን ያለው ውበት ነው፣ ስለዚህ ሰው ወደ ገዛ እራሱ ውስጥ መለስ ብሎ ውስጣዊው ውበቱን በመመልከት እና ከዚህ ውበት ጋር መነጋገር ሲችል ይኸንን ውበት ከገዛ እራሱ በተለያየ የሥነ ጥበብ ዘርፍ በማቅረብ ለመግለጥ ይችላል። ስለዚህ ይኸ በሰው ዘር ውስጥ ያለው ውበት ለአስፍሆተ ወንጌል ጎዳና ነው ሲሉ፣ አቨኒረ የተሰየመው የኢጣሊያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ዕለታዊ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ማርኮ ታርኵይኖ ባቀረቡት አስተምህሮ፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታዮ ሆነው ከመሾማቸው በፊት የካቶሊክ አንቀጸ ሃይማኖት ተንከባካቢ ቅዱስ ማኅበር ኅየንተ እያሉ፣ ‘አቢይ ፈተና እውነት ያልሆነውን ሁሉ ውበት አድርጎ ማቅረብ ነው፣ ይህ ዓይነቱ ውብት ደግሞ ሓሰተኛ ውበት ነው’፣ ያሉትን ሓሳብ መገናኛ ብዙሃን የእውነተኛው ውበት መግለጫ ሆነው እንዲገኙ የሚያሳስብ ነው። የመገናኛ ብዙሃን ለፖሊቲካው፣ ለባለ ሃብቶች እና ተቀባይነት ማግኘት ለሚለው አመለካከት የማያጎበድድ እውነተኛው ውበት መግለጥ የሚችል እውነትን የሚያገናኝ ሲሆን የአስፍሆተ ወንጌል መሣሪያ ይሆናል እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ ይጠቁማል።







All the contents on this site are copyrighted ©.