2012-01-13 15:16:42

የኤውሮጳ እና የሰሜን አመሪካ ብፁዓን ጳጳሳት የቅድስት መንበር ጉዳይ አስተባባሪ ድርገት


እ.ኤ.አ. በ 1998 ዓ.ም. በመካከለኛው ምሥራቅ ለምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን እና ምእመናኖችዋን ትብብር እና ቅርበት ማረጋገጥ ዓልሞ የተመሠረተው የቅድስት መሬት RealAudioMP3 ጉዳይ የሚከታተለው የኤውሮጳ እና የሰሜን አመሪካ ብፁዓን ጳጳሳት የጋርው የአስተባባሪ ድርገት በየዓመቱ በቅድስት መሬት የሚያካሂድው ጉባኤ እቅድ መሠረት መመካከለኛው ምሥራቅ ከምትገኘው ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ብፁዓን ጳጳሳት ምእመናን፣ ውሉደ ክህነት እና ገዳማውያም ጋር መገናኘታቸው ሲገለጥ፣ የኤውሮጳና የሰሜን የአመሪካ ብፁዓን ብፁዓን ጳጳሳት የአስተባባሪ ድርገት እ.ኤ.አ. ከጥር 9 ቀን እስከ ጥር 12 ቀን 2012 ዓ.ም. ያካሄደው ጉባኤ ትላትና ከቀትር በኋላ ያወጣው የጋራ ሰነድ አስደግፎ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ማጠናቀቁ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።
የኤውሮጳ እና የሰሜን አመሪካ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤቶች የጋራው የቅድስት መሬት ጉዳይ የሚከታተለው የአስተባባሪው ድርገት፣ በጉባኤው ፍጻሜ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ፣ የመካከለኛው ምስራቅ ሁኔታ የሌላውን መሬት የራስ ማድረግ የሕይወት ደህንነት አለ መረጋገጥ ፍርሃት የዕለታዊ ሕይወት ሥጋት የመሳሰሉት ችግሮች ቀርበው ለመመልከት መቻላቸው በማብራራት፣ የዚህ ሁሉ ተጠያቂው ሌላው ነው ብሎ ኃላፊንቱን ለሌላው ማላከክ እያንዳንዱ ኃላፊነቱን አለ መወጣቱን ነው የሚያረጋግጠው፣ ስለዚህ ስለ እስራኤል መቆም ስለ ፍልስጥኤም መቆም እንዲሁም ስለ ፍልስጥኤም መቆም ስለ እስራኤል መቆማ ማለት መሆን አለበት፣ ይኽ ደግሞ ከሁሉም ጎን ለሰላም እና ለፍትሕ መቆም እንደሆነ አብራርተው፣ በዚህ ዓይነት አመክንዮ ያልተመራ ለመካከለኛው ምሥራቅ አሳቢነት መፍትሔ ሊያስገኝ አይችልም ብለዋል።
ይህ በእንግልጣር እና የወይለስ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ወኪሎች የሊቨርፑል ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ፓትሪክ ከልይ እና የቢርሚንግሃም ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ዊሊያም ከነይ፣ የኢጣሊያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ወኪል የአረዞ ኮርቶና ሳንሰፖልክሮ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሪካርዶ ፎንታና፣ በካናዳ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ወኪል የኤድሞንቶን ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሪቻርድ ስሚዝ፣ በስፐይን ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ወኪል የኡርጌል ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ዦአን ኤንሪክ ቪቨስ ኢ ሲሲሊያ፣ የተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ወኪል የቱክሶን ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ገራልድ ኪቻናስ፣ የጀርመን ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት የአኼን ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሄንሪኽ ሙሲንግሆፍ፣ የፈረንሳይ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ወኪል የአቭርይ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሚሸል ዱቦስት እና የስካንዲናቭያን ብፁዓን ጳጳሳት ወኪል የረይክጅቪክ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ፔረ ቡርኸር፣ የሚያቅፈው የጋራው የብፁዓን ጳጳሳት የቅድስት መሬት አስተባባሪ ድርገት በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ እ.ኤ.አ. ቅዱስ አባታችን ለ 2012 ዓዲስ ዓመት መግቢያ ምክንያት ጥር 9 ቀን 2012 ዓ.ም. በቅድስት መንበር ለተለያዩ አገሮች ልኡካነ መንግሥታት ተቀብለው ባሰሙት ንግግር፣ የሕዝቦች በሰላም የመኖር ሰብአዊ መብት፣ ክብር እና ፈቃድ፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ያለው የአገሮች ሉአላዊነት በውስጥ እና ከጎረቤት አገሮች በሰላም የመኖር ደህንነት እና ጸጥታ ዋስትና የሚያሰጠው ዘላቂነት ያለው ሰላም እውን እስኪሆን ድረስ የውይይት መድረክ ፈጽሞ መቋረጥ የሌለበት ብቸኛ መፍትሔ ነው በማለት ያሰመሩበት ሀሳብ ጠቅሰው፣ ግጭት እና ውጥረት መፍትሔ እንዳያገኝ የውይይት መድረክ ላይ የሚሰነዘረው ዛቻ በተለያዩ አክራርያን እና ፅንፈኞች ከእኔ የተለየው ማግለል የሚለው ጸረ ሰላም ምርጫ ለአደጋ ተጋልጦ እንደሚገኝ በማብራራት፣ ስለዚህ የክልሉ መሪዎች እና የፖለቲካ አካላት ይኸንን የሰላም የውይይት መድረክ ለሥጋት የሚያጋልጠው ምርጫ በቁርጠኝነት በመቃወምና ከሥርዓተ ፖለቲካው በማግለል ምህረት እርቅ የሚያስተጋባ የአይሁድ ሃይማኖት የክርስትና እምነት እና የምስልምና ሃይማኖት ተከታይነትን የሚያከብር ሰላማዊ ጥምረት ማነቃቃት ይጠበቅባቸዋል በማለት የድርገቱ አባላት ብፁዓን ጳጳሳት ፊርማ የተኖረበት የጉባኤው የማጠቃለያ ሰነድ መሠረት በማድግ የሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳጠቃለሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።







All the contents on this site are copyrighted ©.