2012-01-13 15:12:38

ትኩረት ለቤተ ሰብ፣ ድኽነትን መዋጋት


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ትላትና ጧት የላዚዮ ክፍለ ሃገር የሮማ አውራጃ እና ከተማ የበላይ መሥተዳድር አካላትን ተቀብለው ማነጋገራቸው ሲገለጥ፣ ቅዱስ አባታችን ለመሥተዳድሩ የበላይ አካላት ምዕዳን ከመለገሣቸው ቀደም በማድረግ የላዚዮ ክፍለ ሃገር ሊቀ መንበር RealAudioMP3 ረናታ ፖልቨሪኒ፣ የሮማ አውራጃ ሊቀ መንበር ኒኮላ ዚንጋረቲና የሮማ ከተማ ከንቲባ ጃኒ አለማኖ ቅዱስ አባታችን ላደረጉላቸው አቀባበል፣ ለቤተ ሰብ ድጋፍ እና ድኽነትን መዋጋት ማእከል ያደረገ ማኅበራዊ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ እቅድ ገቢራዊ እንደሚያደርጉ የሚያርጋግጥ የምስጋና ቃል ማሰማታቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።
ቤተ ሰብ ወጣቶች እና ማኅበራዊ ጥምረት ወደ ድኽነት የሚገፋፋው የኤኮኖሚ ቀውስ የሚያስከትለው የድኽነት ኑሮ በተሰኙት ነጥቦች ላይ ያተኮረ የድጋፍ፣ የትብብር የሕንጸት ፖለቲካዊ ማኅበራዊ እና ኤኮኖሚያው እቅድ ላይ እንደሚያተኩሩ ሦስቱ የበላይ መሥተዳድር አካላት ባሰሙት ንግግር ማረጋገጣቸው፣ የተካሄደው ግኑኑኝነት የተከታተሉት የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ደቦራ ዶኒኒ ገልጠው፣ ፖልቨሪኒ ባሰሙት ቃል፣ በላዚዮ ክፍለ ሃገር የተደራጀ የካቶሊክ የበጎ አድራጎት ሱታፌ ለማሳየል፣ ለሚወለደው ሕፃን የሚሰጠው ድጎማ እቅድ እንዳላቸው ሲገለጡ፣ የሮማ ከተማ ከንቲባ ጃኒ አለማኖም በበኩላቸውም ባሰሙት ንግግር በሮማ ከተማ አሳሳቢ እየሆነ ያለው የወንጀል ቡድኖች በሰው እና በንብረት ላይ የሚያስከትሉት ጉዳት ጠቅሰው፣ በቅርቡ በወረበሎች የተገደሉት አባት እና ልጅ ቻይናውያን ስደተኞችን ዘክረው የቅትለቱ ድርጊት ተጠያቂዎች የፖሊስ የምርማሪ ሃይል የክትትል ውጤት እንደሚያመለክተውም ስደተኞች ሳይሆኑ እንደማይቀሩ ነው፣ ሆኖም የኢጣሊያ ዜጎች እና ስደተኞች በማለት የሚገለጥ ጉዳይ ሳይሆን፣ ቅንነት በሚሹት እና ሕገ ወጥነት እና አመጽ በሚመርጡ ዜጎች መካከል ባለው ልዩነት ሥር የሚገለጥ ጉዳይ ነው። የዜጎች የከተማ ነዋሪዎች ጸጥናታ እና ደህንነት ማረጋገጥ ለማህበራዊ ጥምረት መሠረት ነው። ከሮማ ሰበካ ጋር በመተባበርም ወጣቶች በምሥጢረ ተክሊል የጸና ቤተሰብ እንዲመሠርቱ ለማበረታታት ብሎም በድኽነት ለሚጠቁት ቤተ ሰቦች እና አዛውንቶች የኤኮኖሚ ድጋፍ ለማቅረብ መወሰኑ ገልጠው፣ ስለዚህ ቤተሰብና ወጣቶችን መደገፍ ተቀዳሚ ዓላማ ነው እንዳሉ ልእክት ጋዜጠኛ ዶኒኒ አስታውቀዋል።
የሮማ አውራጃ ሊቀ መንበር ዚጋረቲ ተከስቶ ያለው አደገኛው የኤኮኖሚ ቀውስ አነስተኛና አበይት ኢንዳስትሪዎች ያላቸው የማምረት አቅም ለአደጋ ከማጋለጥም አልፎ፣ ለሥራ አጥነት መስፋፋት መንስኤ መሆኑ ገልጠው፣ የምርት አውታሮች ድጋፍ ላይ ያተኮረ እቅድ እንዳላቸው በመግለጥ፣ እነዚህ የምርት አውታሮችን መደገፍ የቤተሰብ የወጣቶች እና ለኤኮኖሚው እንቅስቃሴም ዋስትና መስጠት ማለት መሆኑ ማረጋገጣቸው ጋዜጠኛ ዶኒኒ ያስተላለፉት ዘገባ ይጠቁማል።








All the contents on this site are copyrighted ©.