2012-01-12 15:06:18

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ለአምባሳደሮች ያደረጉት ንግግር ተወደሰ ፡


ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ የኤውሮጳውያን አዲስ ዓመት ሲገባ እንደሚከናውነው ሁሉ የዚህ አዲስ ዓመት 2012 መባቻ

በቅድስት መንበር ለተመደቡ አምባሳደሮች ቫቲካን ውስጥ በሚገኘው ሐዋርያዊ አዳራሽ ንግግር አድርገዋል።

ቅድስት መንበር ከ179 የዓለም ሀገራት ዲፕሎማቲካዊ ግንኙነት እንዳላት ይታወቃል ።

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ቫቲካን ውስጥ ለተሰበሰቡ አምባሳደሮች ያሰሙት ንግግር የሰው ህልውና እና መሠረታዊ መብቱ ማእከል ያደረገ መኖሩ ይታወሳል ።

ቅድስነታቸው ያደረጉት ረዘም ያለ ንግግር የዓረብ ጸደይ የተባለው በሰሜን አፍሪቃ ሀገራት የተከስተው ህዝባዊ ማዕበል ማውሳቱ የሚታወስ ነው ።

ይሁን እና በቱኒሲያ የቱኒስ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ማሩን ኤልያስ ላሐም በነዲክቶስ 16ኛ ለአምባሳደሮቹ ያደረጉት ንግግር ትኩረት ሰጥተው አስተያየት ሰጥተዋል ።

ጳጳሱ እንደገለጡት፡ በመሠረቱ በነዲክቶስ 16ኛ በቅድስት መንበር ለተመደቡ አምባሳደሮች ያደረጉት ንግግር እንደምያደንቁ ጠቅሰው

ወቅታዊ የሰሜን አፍሪቃ ዓረብ ሀገራት ትኩረት ሰጥተው ያደረጉት ንግግር ትክክለኛ እና ግዝያዊ መኖሩ አመልክተዋል ።

አያይዘው የዓረብ ጸደይ ህዝባዊ ማዕበል የተጀመረው በቱኒሲያ መሆኑ አስታውሰው አጀማመሩ የሰው ክብር እና ግርማ ለማስጠበቅ ትኩረት ያዳረገ እንደሆነ ገልጸዋል።

በቱኒሲያ የርእሰ ከተማ ቱኒስ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ማሩን ኤልያስ ላሐም እንደገለጡት ፡ የቱኒሲያ ህዝባዊ ማዕበል የስራ መብት የመጻፍ የሐሳብ መግለጽና የሕልና ነፃነት ትኩረ ያደረገ ህዝባዊ ማዕበል መኖሩ እና አዎንታዊ ውጤት ማስከተሉ ከሰጡት መግለጫ ለመረዳት ተችለዋል።

የቱኒሲያ ህዝባዊ ማዕበል በክርስትያን እና እስላም ማሕበረ ሰቦች መካከል ዲያሎግ ማለት ሰላማዊ ውይይት ለማድረግ ማገዙም ጳጳሱ አክለው አመልክተዋል።

ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ሃይማኖት የሰላም መሳርያ እንዲሆን በሃይማኖት ስም ማንኛውም ሁከት መነሳት እንደሌለበት በየግዜው ያስተላለፉት መልእክት እውን የሚሆንበት ግዜ ይመጣል ብለው እንደምያስቡም አስገንዝበዋል።

ከዚህ ባሻገር በአሁኑ ግዜ ተከስቶ ያለውን ዓለም አቀፍ ለማለት የሚቻለው የኤኮኖሚ እና ፋይናንስ ቀውሶች ለመፍታት ትጋት ቀና አስተሳሰብ ሞራል ለህዝብ ማሰብ ያስፈልጋል በማለት ቅድስነታቸው ለአምባሳደሮቹ ያደረጉት ንግግር እና የሰጡት ምክር ወቅታዊ መሆኑ እና በተለይ አዳጊ ሀገራት ገቢራዊ ያደርጉት ዘንድ ተስፋ እንደሚያደርጉ የቱኒስ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ማሩን ኤልያስ ላሐም ገልጸዋል።



ከሁሉም በላይ ግን ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳስ በነዲክቶስ የሃይማኖት ነጻነት ከሰው መብቶች ጥበቃ የመጀመርያ እና የሰው ማንነት አንኳር መሆኑ ያሰሙት ንግግር አለፌታ መሆኑ ጳጳሱ አያይዘው አመልክተዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.