2012-01-09 16:28:29

የእምነት ዓመት ይዘታ መግለጫ ተሰጠ ፡


ፊታችን ወርሃ ጥቅምት አስራ ሀንድ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ዓመተ እምነት እንዲሆን መሰየምዋ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታውቀዋል ።

ስያሜው ወይም ድንጋጌው እስከ ወርሃ ሕዳር 2013 እኤአ እንደሚዘልቅም መግለጫው አክሎ አመልክተዋል።

የእምነት ዶክትሪን የዓንቀጸ ሃይማኖት ቅዱስ ማሕበር ስለዚሁ በቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ሐሳቢነት Porta fidei የእምነት በር በተሰኘው ሐዋርያዊ መልእክት አስታኮ የሚደነገገው ዓመተ እምነት አጭር ማመልከቻ ሰጥተዋል።

ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ በዚሁ ዓመተ እምነት ከክርስቶስ መገናኘት እና የእምነት ሸጋነት የቅድስት ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ማእከል እንዲሆን እንደሚሹ የሃይማኖት ዶክትሪን ወይም የዓነቅጸ ሃይማኖት ቅዱስ ማሕበር አጭር ማመልከቻ ዘግበዋል።

ዓመተ እምነቱ ሐዋርያዊ ኖልዎ ትኩረት የሰጠ መሆኑ እና ኩላዊት ቅድስት ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ረኪበ ጳጳሳት ቁምስናዎች ካቶሊካዊ ማሕበረ ሰቦች እና እንቅስቃሴዎች የሚዳስስ እንደሆነ አጭር ማመልከቻው አስገንዝበዋል ።

ዓመተ እምነቱ ሁለተኛ የቫቲካን ጉባኤ ጅማሬ እና የቅድስት ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን የትምህርተ ክርስቶስ አዋጅ 20ኛ ዓመት በሚታውሱበት ዝክረ ዓመት መካሄዱ በጎ አጋጣሚ እንደሆነም ተወስተዋል።

ይህ በቅድስት ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን የሚታወጀው ዓመተ እምነት በአጠቃላይ ህዝበ ክርስትያን እምነታቸው ለመሳደስ እና ውስጣዊ ለውጥ በማድረግ ወደ እግዚአብሔር እንዲቀርቡ የእምነት ሕሊናቸው እንዲመረምሩ እገዛ ለመስጠት እንደሆነም የዓንቀጸ ሃይማኖት ቅዱስ ማሕበር አጭር ማስታወሻ እና ማመልከቻ አስታውቀዋል።

ዓመተ እምነቱ የክርስትያኖች አንድነት እንዲገኝ በማሰብ ስለዚሁ ጸሎት እና አስተንትኖ ይዘታ ያለው እንደሆነም ተመልክተዋል።

የእምነት ዓመቱ በዓለም ዙርያ የሚገኙ ካቶሊካውያን ኣአብያተ ክርስትያናት አጣምሮ የያዘ እንደሆነም የዓንቀጸ ሃይማኖት ቅዱስ ማሕበር ዘገበዋል።

ይህ በዚህ እንዳለ ሆኖ ፡ የቤተ ክርስትያን ዶክትሪን ወይም የተአምኖተ ሃይሃኖት ቅዱስ ማሕበር ጽሕፈት ቤት ዋና ሐላፊ አባ ሄርማን ጋይስለር ቅዱስ ማሕበሩ በዚሁ ለአንድ ዓመት በሚዘልቀው ዓመተ እምነት የፓስቶራል መምርያዎች መስጠት የፈለበት ዋነኛው ምክንያት ምን እንደሆነ እንድያብራሩ ተጠይቀው ሲመልሱ ፡

ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ 16ኛ በርእሰ ሊቃነ ጵጵስናቸው ግዜ የካቶሊካዊ ሃይማኖት እምነት ተሀድሶ እንዲከናወን የሰጡት መምርያ ተከትሎ የሚደረግ መሆኑ አስታውቅዋል።

ዓመተ እምነቱ ከክርስቶስ ተነስቶ በክርስቶስ ከክርስቶስ ጋር መራመድ ይዘታ ያለው ለካቶሊካዊ እምነት ዳግመ ሕይወት መስጠት መቀስቀስ ያለመ እንደሆነ የገለጹት የቅዱስ ማሕበሩ ጽሕፈት ቤት ዋና ሐላፊ አባ ሄርማን ጋይስለር ፡ ካቶሊካውያን ምእምነናንን ከመድኅን ኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ለማቀራረብ እና ደግሞ ፊት ለፊት ማገናኘት የተለያዩ መንፈሳውያን ክንውኖች ማካሄድ ትኩረት የሰጠ መሆኑ አስገንዝበዋል።

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ዘወትር ሮቡዕ ዕለት ለምእምነናን የሚሰጡት ትምህርተ ክርስቶስ በማስታውስም ትምክህርተ ክርስቶስ የእምነታችን መሠረት እንደሆነ እና ቅድስት ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ምእመናንዋ አቅፋ ለመራመድ ስለምትፈልግ የሚካሄድ መንፈሳዊ ክንውን መሆኑ አባ ሄርማን ጋይስለር ገልጸዋል።



የእምነተ ዓመቱ ፕርግራም ሰፊ መሆኑ እና በዓለም ዙርያ የሚገኙ ካቶሊካውያን ጳጳሳት በየሀገረ ስበከታቸው ትምህርተ ክርስቶስ ለመስጠት ጥብቃ መመርያ እና ማሳሰብያ የሚሰጥ እንደሆነም የቤተ ክርስትያን ዶክትሪን ጽሕፈት ቤት ዋና ሐላፊ አባ ሄርማን ጋይስለር አስገንዝበዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.