2012-01-09 12:36:55

የቅድስት መንበር ርእሰ ዓንቀጽ


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ እ.ኤ.አ. በ 2012 ዓ.ም. መጋቢት ወር ማብቅያ በኩባና በመክሲኮ ሐዋርያዊ ጉብኝት እንደሚያከናውኑ የሁለቱ ላቲን አመሪካ አገሮች ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤቶች የሰጡት ይፋዊ መግለጫ፣ የሁለቱ አገሮች ሕዝቦች ፍላጎት እና ጉጉት ማነቃቃቱ ተረጋገጠ። ስለዚሁ በእቅድ ተይዞ ስላለው የሐዋርያዊ ጉብኝት ውሳኔ በማስመልከት የቅድስት መንበር የዜና ማኅተም ክፍል ተጠሪ የቫቲካን ረዲዮ ዋና አስተዳዳሪ ኣባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ በሳምንት ማገባደጃ ለሚያቀርቡት የቅድስት መንበር ርእሰ ዓንቀጽ ማእከል በማድረግ፣ እ.ኤ.አ. ጥር 1 ቀን 2012 ዓ.ም. የመክሲኮ እና የኩባ ብፁዓን ጳጳሳት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ይፋዊ ያደረጉት ዜና አስፍሆተ ወንጌል እና እምነትን የሚያነቃቃ መሆኑ ከወዲሁ ለመገንዘብ ተችለዋል። የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የኩባው ሐዋርያዊው ጉብኝታቸው በኩባ የቅድስት ድንግል ማርያም ዘ ካሪዳድ (የፍቅር እናት) ቅዱስ ምስል RealAudioMP3 በኩባ የባህር ክልል የዛሬ 400 ዓመት በፊት ዓሳ አጥማጆች ያገኙት እና የኩባ ጠባቂ ቅድስት የሆነችውን የፍቅር እናት ቅድስት ድንግል ማርያም ኢዮቤል ጋር የሚጠቃለል ዓቢይ ትርጉም ያለው መሆኑ በማብራራት፣ እ.ኤ.አ. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የቅድስት ድንግል ማርያም ዘ ጓዳሉፐ ዓመታዊ በዓል እና የላቲን አመሪካ አገሮች ከቅኝ ግዛት ነጻ የወጡበት 200 ኛው ዝክረ ዓመት ምክንያት በቅዱስ ጴጥሮስ ባሲሊካ እ.ኤ.አ. ታህሳስ 12 ቀን 2011 ዓ.ም. ባሳረጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ ባሰሙት ስብከት፣ በዓለም አቀፍ ጉዳይ የላቲን አመሪካ ተሳትፎ ንቁ እና የተሳታፊነት ሚናው እጅግ እያደገ መሆኑ ዘክረው፣ የዚያ ክፍለ ዓለም የተሟላ ጉዞ ለተሟላ ሰብአዊ እድገት ያቀና መሆን እንዳለበት በማሳሰብ፣ ለዚህ ዓላማ የዳግመ አስፍሆተ ወንጌል ሚና የማይታበል መሆኑ እንዳረጋገጡ አባ ሎምባርዲ በርእሰ ዓንቀጹ በመጥቀስ፣ በመክሲኮ በክርስቶስ ንጉሥ ቅዱስ ሥፍራ አጠገብ በተሠራው 200ኛ ዓመት በተሰየመው አዲስ አደባባይ ተገኝተው የበዓሉ ተካፋይ ለመሆ ያላቸው ፍላጎትም ይፋ ማድረጋቸው የሚዘከር ሲሆን፣ በመክሲኮ ለቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ የሚሰጠው አቢይ ግምት እና ከሕዝቡ የሚቀርብላቸው አቀባበል ር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ አምስት ጊዜ ያካሄዱት ይፋዊ ጉብኝት፣ እንዲሁም ባለፉት የመጨረሻ ወራቶች የር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ቅዱስ ትሩፋት በመክሲኮ ያከናወነው መንፈሳዊ ዑደት ምስክር ነው።
በቅድስት መንበር እና በመክሲኮ መካከል የዛሬ 20 ዓመት በፊት የተረጋገጠው ግኑኝነት የአገሪቱ መንግሥት የመክሲኮ ሕዝብ ያለው ካቶሊካዊ እምነት እውቅና የሰጠ እና ያከበረ መሆኑ አባ ሎምባርዲ በርእሰ ዓንቀጹ በማስመር፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ከሳቸው በፊት የነበሩት የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ በመክሲኮ ሊጎበኙት ባልቻሉት የአገሪቱ ክልል ለሚያካሂዱት ሐዋርያዊ ጉብኝት ማእከል በማድረግ፣ በአገሪቱ ያለው ድኽነት እና አመጽ ተወግዶ ተስፋ እና ሰላም ለመክሲኮ እና ለመላ ላቲን አመሪካ አገሮች የሚያነቃቃ መሆኑ አባ ሎምባርዲ ገልጠው ርእሰ ዓንቀጹን አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.