2012-01-09 12:40:32

በዓለ ግልጸት (አስተርእዮ ለእግዚእነ)


ዶሙስ ጋሊለያ በሚል መጠሪያ የሚታወቀው በዓለም አቀፍ የኔዮ ካተኩመናለ ካቶሊካዊው መንፈሳዊ እንቅስቃሴ ሥር በሚተዳደረው ማእከል የሚያስደንቅ ሱታፌ የታየበት በዓለ RealAudioMP3 ግልጸት መከበሩ ሲር የዜና አገልግልት አስታወቀ።
በዚያ ጋሊለያ ሕንፃ በተሰየመው ማእከል ውስጥ የሚገኘው የመድኃኔዓለም እናት የተሰየመው ዘርአ ክህነት ትምህርት ቤት አስተዳዳሪ አባ ፍራንቸስኮ ቮልታጆ ስለ ተከናወነው በዓል በማስመልከት ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ በዚህ በዓል በየዓመቱ የሚሳተፈው ምእመን ብዛት ቁጥር ከዓመት ወደ ዓመት ከፍ እያለ መሆኑና የሌሎች ሃይማኖት ተሳታፊዎች ብዛትም ሳይቀር እያደገ መምጣቱ ገልጠው፣ በተለያዩ ቋንቋዎች የልደት መዝሙሮች የጠቢባን ማለት የከዋክብት ተማሪዎች ስግደት እና ገጸ በረከት ለሕፃን ኢየሱስ ማእከል ያደረጉ የተለያዩ ደስ የሚያሰኙ መንፈሳዊ መዝሙሮች ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋችን ለብሶ ለእኛ ቅርብ በመሆን ላይ በጸናው እምነት መሠረት አለ ምንም የሃይማኖት የጎሳ እና የዜግነት ልዩነት ወዳጅነት ለማስፋፋት የሚል ቅዱስ ዓላማ ያለው በየዓመቱ በጋራ የሚፈጸም ክብረ በዓል መሆኑ የሚመሰክር መንፈሳዊነት የታየበት ነው።
ይኸንን እቅድ የወጠኑት የነዮ ካተኩመናለ ካቶሊካዊ እንቅስቃሴ መሥራች ኪኮ አርጉዌሎ መሆናቸው አባ ቮልታጆ ገልጠው፣ ያንን ማእከል መርቀው የከፈቱት ር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሐንስ ጳውሎስ ናቸው፣ ሕንፃው የሚገኝበት ክልል፣ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የብፅዕና ስብከቱን ያሰማበት ተራራ ክልል በጌንሳሬጥ ባሕር ዳር ክልል ያለ በመሆኑም ያለው መንፈሳዊነት እና መልክአ ምድራዊ አቀማመጡም ማራኪ ነው። ማእከሉ ገና ተመርቆ እንደ ተከፈተ ኅብረ ሃይማኖታዊ ገጽታ ያጎላ መሆኑም ገልጠው፣ በክልሉ ያለው ችግር አሁንም ባለበት የጸና ቢሆንም ቅሉ፣ አለ ምንም መደናገጥ እና ፍርሃት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ያለን እምነት በቃል እና በሕይወት በመመስከር፣ የእርሱ ደቀ መዛሙርት መሆናችን የሚለየን ተግባር ለመኖር በምናደርገው ጥረት በጌታ ድጋፍ ሌሎችን ለመማረክ እና ወደ ኢየሱስ ለማቅረብ እየቻልን ነው፣ የሌሎች ሃይማኖት ምእመናን ያላቸው የገዛ እራሳቸው የእምነት መለያ አቅበው የጋራ ሰላማዊ ሕይወት ኑሮ ከተለያዩ ሃይማኖቶች የጋራው ውይይት እና ሰላም የሚመነጭ መሆኑ በመታመን ዓላማ መሠረት የሚሳተፉበት ክብረ በዓል ነው በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.