2012-01-04 15:33:07

የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሳምንታዊ የዕለተ ረቡዕ አጠቃላይ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ (እ.ኤ.አ. 04/01/2012)
የልደት ኃሴት መስካርያን


ውድ ወንድሞቼ እና እህቶቼ
በዚህ በተገባው የ2012 ዓ.ም. አዲስ ዓመት የመጀመሪያ የዕለተ ረቡዕ አጠቃላይ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ እናንተን ስቀበል በጣም ደስታ ይሰማኛል። በሙሉ ልብ ለእናንተ እና ለቤተሰቦቻችሁ እንደምጸልይ በማረጋገጥ፣ ፍቅር በተሞላው ጽኑ ስሜት ለእናንተ ያለኝን መልካም ምኞት እገልጻለሁኝ። እግዚአብሔር በልጁ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ልደት አማካኝነት ዓለምን በሞላ በኃሴት አጥለቅልቆታል፣ የሰላም ተግባሮች እና እያንዳንድዋንም ቀን ለሰላሙ ያቁም። እ.ኤ.አ. ታህሳስ 24 ቀን ሌሊት በዋዜማ ተጀምሮ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ RealAudioMP3 ጥምቀት በሚጠቃለለው የበዓለ ልደት የሊጡርጊያ ጊዜ ነው ያለነው። የልደት ጊዜ ዓወደ ሊጡርጊያ አጭር ቢሆንም፣ በበዓል ትርጉም እና ባለው ምሥጢር እጅግ ከፍ ያለ ነው። ይህ ወቅት በሁለት ዓበይት የጌታችን ክብረ በዓላት አማካኝነት ይጠቃለላል። እርሱም በልደት እና በአስተርእዮ ነው። ልደት እና አስተርእዮ የሚሉት ቃላት የገዛ እራሳቸውን ሥነ ትርጉም ጭምር ያመለክታሉ። በዓለ ልደት በቤተልሔም የተፈጸመው የኢየሱስ ታሪካዊ ልደት የሚከበበርበት ሲሆን፣ አስተርእዮ ሲባል ደግሞ የግሪክ ቃሉ “epiphaineia” እርሱም ምሥጥራዊ መልኩ የሚያጎላ እግዚአብሔር በጌታችን ሰብአዊ ባህርይ አማካኝነት መገለጡ የሚያበሥር ነው። በዚህ አኳያም የጌታችን ኢየሱስ መገለጥ ዓላማ ያለው አስተርእዮ በተለያዩ ኅብረ ሁናቴዎች አማካኝነት፣ ኢየሱስ የተጠበቀው መሲህ መሆኑ ያወቁት ሰብአ ሰገል በሕፃኑ ፊት የፈጸሙት አስተንትኖ፣ እንዲሁም በዮርዳኖስ ወንዝ የኢየሱስ መጠመቅ ያለው የእግዚአብሔራዊ ግልጸት፣ በቃና ዘገሊላ ባተካሄደው ሰርግ በኢየሱስ የተፈጸመው የመጀመሪያው ምልክት ሥር በማብራራት፣ እነዚህ ሦስት ምልክቶች የሰዓታት ሊጡርጊያ ተደጋጋሚው የኅብረት ድምጽ የሚይጎላው የመልስ ቃል ተብሎ በሚገለጠው በተደጋጋሚው የጸሎት ቃል “ሰርጉ በክርስቶስ እና በቤተ ክርስትያን” መካከል በማስቀመጥ ይገልጠዋል። “ዛሬ ቤተ ክርስትያን ከሰማያዊው ሙሽራ ጋር ውህደት ታደርጋለች፣ ምክንያቱም ኢየሱስ በዮርዳኖስ ወንዝ ኃጢኣትዋን እንጽቶላታል እና፣ ሰብአ ሰገል ገጸ በረከታቸውን በመያዝ ወደ ከበረው ሰርግ ይሮጣሉ፣ በሰርጉ የተጋበዙት ሁሉም ውኃው ወደ ወይን ሲለወጥ ባዩ ጊዜ እጅግ ደስ አላቸው የሚለው ቃል፣ የነግህ ጸሎት በተደጋጋሚው የጸሎት ቃል አማካኝነትም ይገልጠዋል። በዓለ ልደት እግዚአብሔር በሰው ዘር ሰብአዊነት ‘በቤተልሔም ሕፃን’ ውስጥ ገዛ እራሱን ይደብቃል ለማለትም እንችላለን፣ በአስተርእዮ፣ በተመሳሳይ ሰብአዊነት አማካኝነት እግዚአብሔር የገዛ እራሱን መሆን ይገልጣል።
እያንዳንዳችን ከዚህ በማያልቀው ምሥጢር ምንጭ፣ እንዲረካ እና የተትረፈረፈ የሕይወት ፍሬ እንዲያገኝም፣ በዚህ የዛሬው አጠቃላይ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ አጠር ባለ መልኩ አንዳንድ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ልደት አንኳር የሆኑት ነጥቦችን ለማቅረብ እወዳለሁኝ።
በዚህ ሕፃን-ሰው ሆኖ የሚገለጠው ወደር የሌለው የእግዚአብሔር የመገለጥ ተግባር ፊት፣ በቅድሚያ የሚኖር እና የሚሰማ ስሜት ምንድን ነው? የኃሴት ስሜት ነው። የዓለ ልደት ሌሊት ሊጡርጊያ “ሁላችን በጌታ ደስ ይበለ፣ ምክንያቱም በዓለም አዳኝ ተወልደዋልና” መልአኩም ለእረኞቹ “እነሆ ለእናንተና ለሕዝቡ ሁሉ ደስታ የሚሆን ታላቅ የምሥራች አንግራችኋለሁ አትርፉ” (ሉቃ. 2፣ 10)፣ ይህ በወንጌል የሚገለጠው ቋሚ ሃሳብ፣ ኢየሱስ ከሞት በመነሳቱ ምክንያትም ደቀ መዛሙርትን “በትካዜ እየሄዳችሁ እርስ በርሳችሁ የምትነጋገሩት ይህ ነገር ምንድን ነው?” ሲል ይቆጣቸዋል። ይህ ደስታ ከምንድን ነው የሚመነጨው? በርግጥ የእግዚአብሔር በታሪክ በሚፈጽመው ሁሉ ከልብ የመደነቅ ሁኔታ የሚያፈልቀው ደስታ ነው። ይኽ ደስታ ትሁት ሕፃን ከማስተንተን ዘወትር የእግዚአብሔር ገጽ በሰብአዊነታች ከእኛ ጋር መሆኑ ከመገንዘብ የሚፈልቅ ነው። ልደት ደስታ ነው። ምክንያቱም እግዚአብሔር የሰው መልካም ሕይወት እውነት የሆነው ሰውን ወደ ገዛ እራሱ ከፍ ለማድረግ ሲል ገዛ እራሱን በሰው ሥር ዝቅ አድርገዋልና፣ ቤተ ክርስትያን ይኸንን ሊገለጥ የማይቻለው ምሥጢር ታስተነትናለች፣ የዚህ የበዓለ ልደት ወቅት የሚፈጸመው የሊጡርጊያ ሥርዓቶች መደነቅን እና ደስታን በሚገልጡ ቃላት የተሞሉ ናቸው። በዓለ ልደት ሰማይ እና ምድር የሚወሃዱበት ነጥብ ነው። በዚህ የበዓለ ልደት ወቅት የሚሰማው ስሜት በበዓለ ልደት የተፈጸመው ተግባር ታላቅነቱን የሚያበክር ነው። እሩቅ የነበረው ቅርብ፣ “የማይደረሰው የሚደረስ፣ ከጊዜ በፊት የነበረው በጊዜ ውስጥ መሆን፣ የፍጠረት ሁሉ ጌታ የከበረው ታላቅነቱን በመግለጥ፣ የአገልጋይ ባህርይ ለበሰ” በማለት ቅዱስ ሊዮን አቢይ ይገልጠዋል (2ኛ ስብከት ለበዓለ ልደት)። በዚያ ሕፃን፣ ዘለዓለማዊ ኃያል ቅዱስና ሕይወት ደስታ የሆነው እግዚአብሔር ሁሉም የሚያስፈልገው በመሆን እኛ በሆነው ሁሉ ከእኛ ጋር ኅብረት ፈጠረ።
የበዓለ ልደት ቲዮሎጊያ እና መንፈሳዊነት ይኸንን ተግባር admirabile commercium-የሚያስደንቅ ልውውጥ እርሱም በመለኮታዊነት እና በሰብአዊነት መካከል የተፈጸመው አስገራሚው ልውውጥ በማለት ይገልጡታል። ቅዱስ አታናዚዩስ ዘ እስክንድሪያ (De Incarnation - ትስብእት) በተሰኘው ድርሰቱ አማካኝነት፣ የእግዚአብሔር ልጅ እኛን እግዚአብሔር ሊያደርገን ሰው ሆነ” ያለው ሃሳብ ቅዱስ ሊዮነ አቢይ በበዓለ ልደት ያቀረባቸው ይፋዊ ስብከቶቹ ይህንን ተጨባጭ የሆነው ተግባር ማእከል ያደረገ ነው። እኛ እራሱን ዝቅ ወደ ሚያደርገው የሰው ዘር ፈጣሪ የሆነው ሰው እንዲሆን ለገፋፋው መለኮታዊ ምኅረት የምንማጠን ከሆን፣ በእኛ ዘንድ ላለው ወደ ምናመልከው ባህርይ ከፍ ያደርገናል” (ቅዱስ ሊዮነ አቢይ የልደት ስብከት)። ይህ የሚያስደንቅ መለዋወጥ በክርስቶስ ሰብአዊነት ዘንድ ይፈጸማል። ቃል ሰብአዊነታችንን በመልበስ ሰብአዊ ባህርይ ወደ መለኮታዊ ክብር ከፍ አደረገ። ያ የሚያስደንቅ መለዋወጥ በሁለተኛ ደረጃም በእኛ ተጨባጭ እና ውስጣዊነት አማካኝነት በቃለ መለኮታዊ ባህርይ ሱታፌ የሚገለጥ ነው። “በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ልጁን ላከ፣ ከሴትም ተወለደ፣ የኦሪትንም ሕግ ፈጸመ። እኛ የልጅነትን ክብር እንድናገኝ በኦሪት የነበሩትን ይዋጅ ዘንድ” (ገላትያ 4፣ 4-5)። ስለዚህ በዓለ ልደት እግዚአብሔር የሰው ልጅ ያለው ጥልቅ ክብር እርሱም የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን ለመግለጥ የሰው የመወለድ ተግባር በመፈጸም ቅርብ ሆነ። ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ኃሴት እና ተስፋ በተሰየመው ውሳኔው ሥር “የሰው ልጅ ምሥጢር እውነተኛው ብርሃን የሚያገኘው ሥጋ ሆኖ በወረደው ቃል ምሥጢር ዘንድ”(ቍ.22) መሆኑ ገልጦታል። በሕይወታችን ዘንድ እንዲሠራ እና ሕይወታችንን እውነተኛው የእግዚአብሔር ልጆች ኅልውና ይኖረውም ዘንድ ይህ የሚያስደንቅ መለዋወጥ በምንድን ነው ኅያው ሆኖ የሚገለጠው? በቅዱስ ቍርባን። በቅዳሴ ሥነ ሥርዓት ስንሳተፍ የምድር ፍሬ የሆነው እንጀራን እና ወይን በማቅረብ፣ እርሱም ተቀብሎ ወደ ገዛ እራሱ ለውጦ ገዛ እራሱ ምግባችን ሆኖ በመሰጠት፣ ሥጋውን እና ደሙን ስንቀበል በእርሱ መለኮታዊ ሕይወት ሱታፌ ይኖረናል።
በመጨረሻ ሌላውን የልደት ገጽታ በተመለከተ ሐሳብ ላይ ለማተኮር እሻለሁ በማለት ቅዱስ አባታችን በመቀጠል፣ የጌታ መልአክ በኢየሱስ ልደት ሌሊት በእረኞች ፊት መገኘት በተመለከተ ወንጌላዊ ሉቃስ እንደሚለው “የጌታ ክብርም በዙያራቸው አበራ” (ምዕ. 2፣9)፣ የዮሐንስ ወንጌል መቅድም፣ ቃል የነበረው ሥጋ ሆኖ መመካከላችን ማደሩንም ልክ ወደ ዓለም እንደሚመጣው እያናንዳንዱን ሰው የሚያበራ እውነተኛው ብርሃን አድርጎ ይገልጠዋል፣ “ለሰው ሁሉ የሚያበራው እውነተኛው ብርሃን ወደ ዓለም ይመጣ ነበር” (ምዕ. 1፣9)። የበዓለ ልደት ሊጡርጊያ በብርሃን የተከበበ ነው። የክርስቶስ መምጣት የዓለምን ጭለማ በብርሃን እንዲያንጸባርቅ ያደረገዋል። ያችን ቅድስት ሌሊት በሰማዩ ድምቀት በመሞላትና በሰዎች ገጽ ላይም የእግዚአብሔር አብ ውበትን ያኖራል። በክርስቶስ ብርሃን ተሞልተን በበዓለ ልደት ሊጡርጊያ አእምሮአችን እና ልባችንን የገጹን ብርሃን በገለጠልን እግዚአብሔር ቦግ እንዲል በጽናት ተጋብዘናል። ቀዳሚው የልደት ትንቢት “ሥጋ በሚለብሰው ቃለ ምሥጢር አማካኝነት በአእምሮአችን አዲስ የብርሃንህ ድምቀት ተገልጦልን፣ የማይዳሰስውን እግዚአብሔር እንድናውቅ በእርሱ ዘንድ በፍቅሩ በማይዳሰስው ሓቅ ተመንጥቀናል” የሚል ብሥራት ነው። በምሥጢረ ትስብእት፣ እግዚአብሔር በመልእክተኞች እና በተለያዩ ምልክቶች “በግልጸት” አማካኝነት በመናገር እና በታሪክ ዘንድ በመግባት ዓለም ለማብራት ከማይዘለቀው ብርሃኑ ዘንድ ወጥቶ መጣ።
ከጥቂት ቀናት በኋላ በምናከብረው የእስተርእዮ በዓል፣ ቅድስት ቤተ ክርስትያን ጥልቅ ትርጉም ያለው በነቢይ ኢሳያስ የተነገረው የእግዚአብሔር ቃል ታቀርብልናለች “ብርሃንሽ መጥቶአልና የእግዚአብሔርም ክብር ወጥቶልሻልና ተነሺ፣ አብሪ። እነሆ ጨለማ ምድርን ድቅድቅ ጨለማም አሕዛብን ይሸፍናል ነገር ግን በአንቺ ላይ እግዚአብሔር ይወጣል፣ ክብሩም በአንቺ ላይ ይታያል አሕዛብም ወደ ብርሃንሽ ነገሥታትም ወደ መውጫሽ ጸዳል ይመጣሉ” (ምዕ. 60፣1-3)። ለቤተ ክርስትያን ለማኅበረ ምእመናን፣ ለእያንዳንዳችንንም የቀረበ ወደ ዓለም የአዲስ ወንጌል ምስክርነት እና ብርሃን ለማድረስ ያለን የልኡክነት የኃላፊነቱንም ግንዛቤ እንዲኖረን የሚያመለክት ጥሪ ነው። ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ብርሃነ አሕዛብ በተሰኘው ውሳኔ “ክርስቶስ የአሕዛብ ብርሃን ነውና፣ ይህ በቅዱስ መንፈስ ሥር የተሰበሰበው ቅዱስ ጉባኤ በቤተ ክርስትያኑ ላይ ከሚያበራው ከእርሱ ብርሃን በሚመነጨው የጋለ ስሜት አማካኝነት ወንጌልን በማበሠር ለሁሉንም የሰውን ዘር ብርሃን ለመስጠት ትሻለች” (ቁ.1)። ቤተ ክርስትያን ብርሃን አይደለችም፣ ነገር ግን ከክርስቶስ ብርሃን በመቀበል ገዛ እራሷ በርታ ለሁሉም በዚህ ብርሃን የከበረው ድምቀቱን ታስፋፋለች። ይኽ ደግሞ በእያንዳንዳችን ግላዊ ሕይውት መረጋገጥ አለበት። ቅዱስ ሊዮነ ዓቢይ “ክርስትያን ሆይ የመለኮታዊ ባህርይ ተሳታፊ የሆነው ክብርህን እወቅ፣ ክብር በሌለው በጊዚያዊው ርኻሽ ሁኔታ ዳግም እንዳትታለል ክብርህን እወቅ፣ የዚያ የአካሉ ክፍል የሆንከው ‘መሪህ’ ማን መሆኑን እወቅ፣ ከጨለማው ኃይል ተነጥቀህ ወደ እግዚአብሔር ብርሃን እና መንግሥት ተሸጋግረሃልና” (ቀዳሜ ስብከት በዓለ ልደት)።
ውድ ወንድሞቼ እና እህቶቼ በዓለ ልደት፣ ያንን ሰው በሰብአዊነት እና በድኽነት ሰው የመሆን የእግዚአብሔር ምሥጢር ሕፃን እንድናስተነትን ቆም የምንልበት፣ በተለይ ደግሞ በእርሱ ሕይወት እንድንኖርና የእርሱ ስሜት ሃሳብ እና ግብር የእኛ ስሜት አስተሳሳብ እና ተግባር በማድረግ ያልደት ያመጣው ኃሴት ኅዳሴ ብርሃን በሕይውታችን ሁሉ ይዘነው በመጓዝ ለሁሉም ይኸንን የእግአብሔር ኃሴት ኅዳሴ እና ብርሃን ለማድረስ ያንን ጌታ የሆነው ክርስቶስ ሕፃን በሕይወታችን ዳግም በአዲስ መንፈስ እንድንቀበለው ያስፈልጋል።
ደግሜ በእግዚአብሔር ኅልውና የተቀደሰ መልካም የልደት በዓል ጊዜ እመኝላችኋለሁ ካሉ በኋላ ለሁሉም ከውጭና ከኢጣሊያ ውስጥ ለመጡትን ምእመናን በተለያዩ ቋንቋዎች ሰላምታን አቅርበው ሐዋርያዊ ቡራኬ ሰጥተው ተሰናብተዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.