2012-01-02 14:30:06

የቅድስት መንበር ርእሰ ዓንቀጽ፦ “ሕንጸት እና ሰላም”


ሁሌ መሳምንት ማገባደጃ የቅድስት መንበር የዜና ማኅተም ክፍል ተጠሪ የቫቲካን ረዲዮ ዋና አስተዳዳሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ የሚያቀርቡት የቅድስት መንበር ርእሰ ዓንቀጽ በመቀጠል “ሕንጸት እና ሰላም” በሚል ርእስ ሥር ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ጥር አንድ ቀን 2012 ዓ.ም. ወጣት ትውልድ RealAudioMP3 ለፍትሕ እና ለሰላም ማነጽ በሚል ርእስ ሥር ያስተላለፉት ዓለም አቀፍ የሰላም ኵላዊ ውመልእክት ማእከል በማድረግ፣ ይኽ የሰላም መልእክት በሚገባ መስተጋባት አለበት። ምክንያቱም ወጣት ትውልድ ለሰላም የማያንጽ ኅብረተሰብ የነገውን ሰላም ዋስትና ለማረጋገጥ አይችልም።
በሰሜን አፍሪቃ በተለያዩ የመካከለኛው ምሥራቅ አገሮች የተቀሰቀሰው የለውጥ ጸደይ እንዲሁም Indignados - ምሬት ወይንም ቁጣ በሚል ስያሜ ከስፐይን ተነቃቅቶ በተለያዩ ምዕራብ አገሮች ወጣቶች የሚጠይቁት ኅዳሴ እና ለውጥ ጠሪ እንቅስቃሴ በርግጥ የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የሰላም መልእክት ከሁሉም በላቀና ለየት ባለ መልኩ ግምት የሚሰጥ ብቻ ሳይሆን፣ የተከሰተው ምሬት እና ቁጣ ወደ ተገባው ግብ ለመምራት እንዲቻል የሚያግዘው መንገድ የሚያመለክት ነው። ስለዚህ በተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን አልፎ አልፎ ለእነዚህ ቁጡ ወጣቶች የሚሰጡት የመጀመሪያ የዜና ገጽ በቂ አይደለም፣ የሚቀርበው ሕንጸት ወሳኝ ነው። ዛሬ በተስፋ መቁረጥ የተጠቃው ወጣት ትውልድ ከወዲሁ የነገ ሕይወቱ ምን እንደሚሆን ለመገመቱ አያዳግትም፣ ስለዚህ ለዚህ ወጣታ ትውልድ የሚቀርበው አወንታዊ ሕንጸት ለዓለም ወሳኝ ነው።
ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ባስተላለፉት ኵላዊው የሰላም መልእክት ሕንጸት የሚማርክ እና ከበድ ያለ ጎዞ ነው በማለት እንዳሰመሩበት አባ ሎምባርዲ በርእሰ ዓንቀጹ በማስታወስ፣ የወጣት ትውልድ ሕንጸት የቤተሰብ ኃላፊነት ብቻ ሳይሆን፣ የሁሉም ኃላፊነት ነው። ስለዚህ የወጣት ትውልድ ሕንጸት ሁሉም የሚመለከት ቢሆንም ቅሉ፣ በሕንጸት ሙያ ዘርፍ በይፋ አገልግሎት የሚሰጡ ዜጎች ያለባቸው ኃላፊነት እጅግ የላቀ ነው። ሕንጸት በቃል እና በሕይወት የተሸኘ ሕንጸት መሆን አለበት፣ በቃል እና በሕይወት የተደገፈ ሕንጸት አስተማማኝ ብቻ ሳይሆን ሕንጸት ለሚቀርበለት ወጣት ጭምር ማራኪ እና አሳማኝም ይሆናል ብለዋል።
መሠረታውያን እሴቶች ለመተካት ምድራዊነት በሚል ሃይማኖት እና ግብረ ገብ የሚነጥል ቅጥ አልቦ ነጻነት የሚያስቀድም በመስፋፋት ላይ ያለው ባህል አማካኝነት ወጣቱ ትውልድ ምንኛ ለአደጋ መጋለጡ አባ ሎምባርዲ በማብራራት፣ መጪው ዓለም ጨለማ እንዳይሆን ከተፈለገ ይኽ ምድራዊነት ብቻ የሚለው አደገኛው ባህል አሉታዊ እና ሐሰተኛ መሆኑ ማስረዳት ብሎም ቅንነት እና ጽናት ፍቅር ማእከል ያድረገ የተሟላ የሰብአዊ ሕንጸት መርሃ ግብር ማረጋገጥ ወሳኝ ነው በማለት ርእሰ ዓንቀጹን አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.