2012-01-02 14:32:04

በብዙ ሺሕ የሚገመቱ ምእመናን በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ


ትላትና በጎርጎሪዮስ ባሕረ ሐሳብ መሠረት የአዲስ ዓመት መባቻ 2012 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. እኵለ ቀን በሚያቀርቡት ጸሎት መልአከ እግዚአብሔር ለመሳተፍ እና የሚሰጡት አስተምህሮ ለመቀበል በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ከውጭ እና ከውስጥ የመጡ እልፍ አእላፍ ምእመናን መገኘታቸው RealAudioMP3 የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።
ከቅዱስ አባታችን ጋር በመሆን ጸሎት መልአከ እግዚአብሔር ለመድገም፣ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ አስተምህሮ ለመቀበል የተገኙት ምእመናን፣ እምነት በሁሉም የሕይወት ገጠመኝ ዘንድ ያለው አስፈላጊነት በደስታም ይሁን በስቃይ እምነት እና ጸሎት ማረጋጋጥ ብቻ ሳይሆን ዕለታዊ ኑሮ በምስክርነት ሲኖር ሕይወት በሚፈራረቀው ችግር የማይበገር መሆኑ ይታመናል። አለ ምንም ልዩነት ከሁሉም የተለያዩ ሃይማኖቶች ጋር ሰላማዊ ዓለም ለማነጽ ያለው ኃላፊነት የጋራ መሆኑ የሚመሰከርበት ዕለት ብቻ ሳይሆን፣ ሰላም የሁሉም መሠረታዊ እስየት መሆኑ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የሚያስተምሩበት እና ለዚህ ዓለማ ሁሉም በጸሎት እና በእምነት እንዲንቀሳቀስ የሚሰጡት ሥልጣናዊ አደራ በይፋ ለመቀበል የተገኙ መሆናቸው ምእመናኑ ከጸሎቱ ፍጻሜ በኋላ በሰጡት ምስክርነት አረጋግጠዋል።
በላቲን ሥርዓት የጎርጎሪዮስ ባሕረ ሐሳብ መሠረት የአዲስ ዓመት መባቻ የቅድስተ ቅዱሳን አመ አምላክ ቅድስት ድንግል ማርያም በዓል የሚከበርበት ዕለት በመሆኑም የሰላም ንግሥትን ለመማጠን ሁሉም ወደ እግዚአብሔር እንዲቀርብ በዓለም በቤተሰብ ውስጥም የሰላም ንጉሥ ኢየሱስ የቅድስት ቤተሰብ መንፈሳዊነት ነግሦ በዓለም እንዲያንጸባርቅ ማድረግ የሰላም መሠረት መሆኑ ያለው እምነት ኵላዊነት ቤተ ክርስትያን የምታስገነዝብበት ዕለት እንደሆነም ምእመናኑ በሱታፌአቸው እና በሰጡት ቃለ መጠይቅ መስክረውታል።







All the contents on this site are copyrighted ©.