2011-12-31 09:20:34

ር ሊ ጳ በነዲክቶስ ጸሎት ጠየቁ ፡


ቅዱስ አብታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ የተያዝነው በጎርጎርዮሳዊ ዘመን አቁጣጣር 2011 ተጠቃልሎ ለአዲሱ ዓመት 2012 ቦታ ለቆ እንዳለፈ የተፈጥሮአዊ መቅድስፍት ለሆኑ የዓለም ህዝቦች መንፈሳዊ እና ማተተርያላዊ እገዛ እንዲያገኙ ጸሎት እንዲደረግ እንደሚጠይቁ ቫቲካን ላይ የወጣ መግለጫ ዘግበዋል ።

በዚሁ መግለጫ መሠረት ፡ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ በዚሁ እየተጠቃለለ ባለው ዓመት ውስጥ በተለያዩ ተፈጥሮአዊ መቅሰፍቶች ለኀይለኛ ችግር የተጋለጡ የዓለም ህዝቦች እፎይታ አግኝተው ሕይወታቸው ዳግም ማነጽ ይችሉ ዘንድ መንፈሳዊ እና ማተርያላዊ ርዳታ እንድያገኙ ይፈልጋሉ ።

እሳቸውም ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ በጎርጎርዮሳዊ ዘመን አቁጣጣአር አዲሱ ዓመት 2012 እንደገባ ከመባቻ ወርሃ ጥር እስከ መጨረሻ ወር ድረስ ለችግር ስለ ተጋለጡ የዓለም ህዝቦች እንደሚጸልዩ ይህ ቫቲካን ላይ የወጣ መግለጫ አስገንዝበዋል።

የጣልያን ካሪታስ የውጭ ጉዳይ ዋና ሐላፊ ፓኦሎ በቸጋቶ እንዳመለከቱት ካለፉት አርባ ዓመታት ተመኩሮ እንደተገነዘቡት ሰብአዊ ርዳታዎች እዥግ አስፈላጊ ጠቃሚ እና ታላቅ ደስታ ሰጭ መሆናቸው ተረድተዋል ።

በተፈጥሮአዊ መቅሰፍቶች በጦርነቶች በመሬት መናወጥ የችግር ሰለባ ለሆኑ የዓለም ህዝቦች የዓለም ካሪታሶች እና ግብረ ሰናይ ድርጅቶች የመጀመርያ ርዳታ ለመስጠት እንደሚሽቀዳደሙ ጠቅሰው የሰው ሕይወት ከአደጋ ማዳን የሚበልጥ ነገር እንደሌለ እና ውስጣዊ እርካታ የሚሰጥ ድርጊት መሆኑ በጣልያን ካሪታስ የወጭ ርዳታ ዋና ሐለፊ ፓኦሎ በቸጋቶ ገልጠዋል።

እዚህ ጣልያን ውስጥ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍለ ሀገራት በውሃ ሙላት እና እንዳንዴም ቀለል ባለ የመሬት መናወጥ ለችግር የሚጋለጡ ዜጎች በካሪታስ በኩል የሚሰጠው የመጀመርያ ርዳታ እና በዳግመ ግንባታ የሚሰጠው መጠነኛ ርዳታ ለዚሁ ችግር ሰለባ ለሚሆኑ ሰዎች የሚሰጠው የእግዚአብሔር ይስጥልን ምላሽ አስደሳች እንደሆነ ፓኦሎ በቸርጋቶ አያይዘው አስገንዝበዋል።

ተፈጥሮአዊ መቅሰፍቶች ኀያላን ሲሆኑ የሚሰጠው ሰብአዊ አዳታም እንዲሁ ኀያል እና በርካታ ከሆነ ችግሩ በቀላሉ ለመቋቋም እንደሚቻል ያመልከቱ ፓኦሎ በቸጋቶ የጣልያን ካሪታስ የውጭ ርዳታ ዋና ተጠሪ ርዳታ ተጠይቆ ምላሽ ሲጠፋ ወይም በጣም ዘግይቶ ሲገኝ በጣም እንደምያበሳጭ እና የምያሳዝን አክለው አመልክተዋል።

ሰብአዊ ርዳታዎች ዘላቂ ርዳታዎች ቢሆኑ እንደሚመረጥ እና ብዙ ግዜ የሚሰጡ ግዝያዊ ርዳታዎች ስለሆኑ ለችግር ለተጋለጡ ሰዎች ዘላቂ ርዳታ መስጠት እንደሚያስቸግር ገለጠዋል።

በጣልያን የጣልያን ካሪታስ የውጭ ርዳታ ዋና ሐላፊ ፓኦሎ በቸጋቶ እንደገለጹት ባለፈው ወርሃ ሐምለ በአፍሪቃ ቀንድ ሀገራት ኀይለኛ ድርቅ ተከስቶ ህዝቡ ለርሐብ እንደተገጋለጠ ከሀገራት አቀፍ ማሕበረ ሰብ አስቻኳይ ርዳታ በመገኘቱ በርካታ ህዝብ ከሞት ማዳን ተችለዋል ። በዚሁ አጋጣሚ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ማሕበረሰቡ የርዳታ እጁ እንዲዘረጋ በፍጥነት ያስተላላፉት የርዳታ አደራ እዥግ ጠቃሚ መኖሩ አስታውሰዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.