2011-12-30 13:59:39

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፥ “እ.ኤ.አ. በ 2012 ዓ.ም. ሮማ እናንተን የታይዘ ወጣቶች በጋለ ክርስትያናዊ ስሜት ለማስተናገድ ዝግጁ ነች።”
የታይዘ ወጣት ማኅበረሰብ፦ “ለአንድ አዲስ የትብብር መንፈስ ዓላማ”


እ.ኤ.አ. ከታህሳስ 28 ቀን 2011 ዓ.ም. እስከ ጥር 1 ቀን 2012 ዓ.ም. በጀርመን ርእሰ ከተማ በርሊን የታይዘ ወጣት ማኅበርሰብ ጉባኤ እየተካሄደ መሆኑ ሲገለጥ፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ለእነዚህ የታይዘ ወጣት ማኅበረሰብ የቅድስት መንበር ዋና ጸሐፍ ብፁዕ ካርዲናል ታርቺዚዮ በርቶነ RealAudioMP3 ፊርማ የሰፈረበት ባስተላለፉት መልእክት፣ “የእማኔ ጎዳና በዓለም ሁሉ አቅኑ” የሚል የማበረታታቻ ቃል በማሰማት፣ በዚህ አጋጣሚም የዚህ የታይዘ ወጣት ማኅበርሰብ ጉባኤ እ.ኤ.አ. በ 2012 ዓ.ም. በሮማ “በምድር የእማኔ ነጋድያን” በሚል መሪ ቃል ተሸኝቶ እንደሚካሄድ በማስታወስ፣ ሮማ እናንተን የታይዘ ወጣቶች በጋለ ልባዊ ስሜት ታስተናግዳችዋለች በማለት እንዳረጋገጡላቸው የቅድስት መንበር መግለጫ ይጠቁማል።
የታይዘ የውህደት ክርስትያን መናንያን ማኅበረሰብ አባል የመጽሐፍ ቅዱስ ሊቅ ወንድም ጆን የዚህ ታይዘ ማኅበረሰብ መንፈሳዊነት የሚከተሉ ከተለያዩ አገሮች የተወጣጡ ወጣት ማኅበረሰብ በበርሊን እያካሄደው ስላለው ጉባኤ በማስመልከት ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ የጉባኤው ቁም ነገሩ ስብሰባው እና ግኑኝነቱ ሳይሆን፣ በዚህ በምንኖርበት በሕይወት ላለነው ብቻ ሳይሆን መጪው ትውልድ ጭምር የሚያስተውል አንድ አዲስ የትብብር መንፈስ እንዲነቃቃ እና በምርድ የእማኔ ነጋድያን በእምነት እና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እና በእግዚአብሔር ላይ የጸና ሰብአዊነት ለማረጋገጥ እንዲቻል የሚያንጽ ጉባኤ ነው።
እነዚህ ከኤውሮጳ እና ከኤውሮጳ ውጭ የተወጣጡት የታይዘ ወጣት ማኅበረሰብ ባላቸው የአጋጣሚ ልዩነት ሳይሰናከሉ በጋራ የሕይወት ትርጉም ከክርስትናው የእምነት መሠረታዊ ምንጭ እንዲሁም የቤተ ክርስትያን ሱታፌ በጥልቀት ለመረዳት አቅደው መሰብሰባቸው ወንድም ጆን ጠቅሰው፣ የፖለቲካው ዓለምና መልክዓ ምድር ባህል ጭምር ያስከተለው ልዩነት እና በሕዝቦች መካከል የጋባው የጥላቻው መንፈስ ሳይበግራቸው አንድ አዲስ ሰብአዊነት ለማነጽ የሚቻል መሆኑ የሚመሰክር ጉባኤ ጭምር ነው። በአሁኑ ወቅት በእድሜ ከገፉት ባሻገር በእጅጉ ለመጪው ትውልድ እና የነገው ዓለም ተረካቢው ወጣት ማኅበርሰብ በእጅጉ የሚነካው ተከስቶ ያለው ዘርፈ ብዙ ቀውስ በውህደት እና ከእምነት ምንጭ በተገነባው ሕይወት አማካኝነት በመመልከት ለመቀረፍ የሚቻል ነው የሚል ተስፈኛ ራእይ እንዲኖራቸው የሚያግዝ ጉባኤም ነው።
በርሊን የለያይ ግንብ ትእምርት ነበረች ይኽ ለያይ ግንብ ተወግዶ የሕዝቦች ውህደት እና የግኑኝነት ትእምርት ሆናለች፣ ስለዚህ የታይዘ ወጣቶች ማኅበረሰብ ጉባኤ በበርሊን ማካሄዱ አለ ምክንያት አይደለም በማለት ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.