2011-12-29 09:12:57

ር ሊ ጳ በነዲክቶስ ለታይዘ ወጣቶች የላኩት መልእክት ፡


የታይዘ ኤኩመኒካዊ ማሕበረ ሰብ ሳላሳ ሺ ወጣቶች በጀርመን ፈደራል ረፓብሊክ ርእሰ ከተማ በርሊን ጉባኤ እያካሄዱ መሆናቸው ተነግረዋል።

ይህ ከተለያዩ ሀገራት የተውጣጡ ወጣቶች ያሳተፈ ጉባኤ እምነትን ማሰራጨት የተሰየመ ርእስ አንግቦ እየተካሄደ ሲሆን እስከ ፊታችን ሰንበት የሚዘለቅ ጉባኤ መሆኑ ከበርሊን ከተማ የመጣ ዜና አስታውቀዋል።

ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ለዚሁ የታይዘ ኤኩመኒካዊ ማሕበረ ሰብ ወጣቶች ጉባኤ የላኩት መልእልክት ወጣቶቹ በዓለም ዙርያ እምነት እና ተስፋ እንድያሰራጩ የሰው ልጅ የሚገጥሙትን እክሎች በእምነት እና ተስፋ እንዲሻገረው ይህን ተከትሎም ለሰላም እንዲሰራ እንድያበረታቱ መጠየቁ ተመልክተዋል።

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ለታይዘ ኤኩመኒካዊ ማሕበረ ሰብ ወጣቶች ጉባኤ የላኩት መልእክት አያይዞ የሰው ልጅ የፍርሐት ተገጂ ሆኖ መኖር ትቶ እምነትን እንዲላበስ ወጣቶቹ እንዲተባበሩ ማሳሰቡም ቫቲካን ላይ የወጣ መግለጫ ዘግበዋል።

የዛሬ ሰዎች የሚገጥምዋቸው ችግሮች በቀላሉ ለመወጣት እምነታቸው በክርስቶስ ላይ ሲጥሉ ከክርስቶስ ጋር ሲጓዙ ክርስቶስን ወደ መድኅን ዓለም ክርስቶስ ስቀርቡ እና ስያፈቅሩት እንደሆነ መልእክቱ ማመልከቱ መግለጫው አስገንዝበዋል።

የቁስጢንጢንያ ፓትርያርክ ብጹዕ ወቅዱስ ባርቶሎሞለዮ አንደኛ ለታይዘ ኤኩመኒካዊ ማሕበረ ሰብ ወጣቶች ተመሳሳይ መልእክት መላካቸው የቫቲካን መግለጫ አስታውሶ ፡ ፓትርያርኩ የሰው ሕይወት የተለያዩ አድባራት ለመሳለም የሚደረገውን ጉዞ ተመሳሳይ መሆኑ ጠቅሰው ሰዎች በመተባበር የተሻለ ሕብረተ ሰብ ለመመሥረት እንዲሰሩ እና ከሰብአዊ ድርጊቶች እንዳይርቁ ወጣቶቹ ለዚሁ ጉዳይ ትብብር እንድያሳዩ መጠየቃቸው አመልክተዋል።

በሌላ በኩል የሞስኮ እና ኩላዊት ሩስያ ፓትርያርክ ብጹዕ ወቅዱስ ክሪል በበኩላቸው በፌደራል ረፓብሊክ ጀርመን በጉባኤ የተቀመጡ የታይዘ ኤኩመኒካዊ ማሕበረ ሰብ ወጣቶች መልእክት መላካካቸው ከሞስኮ የመጣ ዜና ገልጸዋል።

ብጹዕ ወቅዱስ ክሪል የላኩት መልእክት ሰብአዊ ትብብር በገና ግዜ በተገለጸልን የእግዚአብሔር ስጦታ ላይ የተመሠረተ መሆን እንደሚገባው እና የዓለም ህዝቦች ከመለያየት ይልቅ በመተባበር ምድራዊ ሰላማዊ ሕይወት ያሳልፉ ዘንዳ መኰትኰት ያሻል ሲሉ መጻፋቸው ይህ ከሞስኮ የደረሰ ዜና አስገንዝበዋል።

የዛሬ ሰዎች ብሔራዊ እና ማሕበራዊ ልዩነታቸው አስወግደው በሰላም ተባባረው መኖር መቻል አለበቻው ከስስት እና ከሀብይት መካበት እንዲቆጠቡም እንደምያሻ የሞስኮ እና የኩላዊት ሩስያ ፓትርያርክ ብጹዕ ወቅዱስ ክሪል ለታይዘ ማሕበረ ሰብ ወጣቶች የጻፉት መልእክት ማመልከቱ ተመልክተዋል።

በታላቅ ብሪታንያ የካንተበሪ አንገሊካዊ ሊቀ ጳጳስ ሮዋን ዊልያምስ በበኩላቸው በፈደራል ጀርመን ርእሰ ከተማ ለጉባኤ የተቀመጡ የታይዘ ኤኩመኒካዊ ማሕበረ ሰብ ሳላሳ ሺ ወጣቶች መልእክት መስተላለፋቸው የቫቲካን የዜና ምንጭ ጠቅሶ ፡ ወጣቶች እግዚአብሔር ይወዳችሃል ቀና መንገድም ይመራችሃል እና አይዛችሁ በርቱ እናንተ የመጪው ግዜ ተሳፋ ናችሁ በማለት መጻፋቸው ገልጸዋል።

ዓለም አቀፍ የሉተራን ፌደረሽን ዋና ጽሐፊ ማርቲን ዩንገ በበኩላቸው በእግዚአብሔር እምነት ከለለን የለንም የሐሰት ሕይወት እየመራን ነው ማለት ነው በማለት ለወጣቶቹ በጻፉት መልእክት ላይ ማመልከታቸው ተመልክተዋል።

የአብያተ ክርስትያናት ኤኩመኒካዊ ምክር ቤት ዋና ጽሐፊ ኦላቭ ተቪት በበኩላቸው ይች የምንኖርባት ዓለም በተለያዩ ምክንያቶች በስጋት ተውጣ እንደምትገኝ እና በኛ እና በክርስቶስ ያለውን ፍቅር ላይ ተመስርተን በጋርዮሽ ከተጓዝን ስጋቱ ለመቋቋም እንችላላን በማለት ለታይዘ ወጣቶች መጻፋቸው ታውቆዋል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጽሐፊ ባን ኪሙን በርሊን ላይ ለጉባኤ የተቀመጡ የታይዘ ማሕበረ ሰብ ሳላሳ ሺ ወጣቶች በላኩት መልእክት ፡ ሰዎች በመንግስታት ላይ የነበራቸው እምነት እያጠፉ በሚሄዱበት በአሁኑ ግዜ ዓለም አቀፍ ትብብር የችግሩ መፍትሔ ይሆናል የሚል እምነት እንዳላቸው ማመልከታቸው ከኒው ዮርክ የመጣ ዜና አስገንዝበዋል።

ከኢየሱስ ክርስቶስ በመተሳሰር በዓለም ላይ ርስ በርስ መከባበር እና መፈቃቀድ ከተከስተ ይህን ተከትሎ መተባበር ሊመጣ ይችላል ይህን መልእክት ያስተላላፉ የኤውሮጳ ምክር ቤት ፕረሲደንት ሄርማን ፎን ሮምፐ ናቸው ሲል ከብሩሰል ተመልክተዋል።

የጀርመን ፌደራል ረፓብሊክ መንግስት ቻንስለር ኤንጌላ መርክል በርሊን ላይ ለተሰበሰቡ የታይዘ ኤኩመኒካዊ ማሕበረ ሰብ ወጣቶች እንደጻፉት ዓለማችን ዲሞክራሲ እና አርነት ያሻታል ፡ እነሱ ከሰማይ የሚወርዱ ሳይሆን መታነጽ መንከባከብ የሚያሻቸው ርእሰ ጉዳዮች መሆናቸው መዘንጋት አይገባም ።

የታይዘ ኤኩመኒካዊ ማሕበረ ሰብ መሥራች አሀው ሮጀር በ205 ነሐሰ አጋማሽ ቤተ ክርስትያን ውስጥ በመጠለይ ላይ እንዳሉ በአንድ አእምርአቸው የሳቱ ሴት ልጅ መገደላቸው አይዝነጋም ።

የወቅቱ የማሕበረ ሰቡ መሪ አኀው አሎይስ ሲሆኑ ማሕበረ ሰቡ በዓለም አቀፍ ደረጃ አዲስ የትብብር አጋርነት ለመቀስቀ እየተንቀሳቀሰ መሆኑ በርሊን ላይ መግለጣቸው ከቦታው የደረሰ ዜና አስታውቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.