2011-12-28 14:45:56

የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሳምንታዊ የዕለተ ረቡዕ አጠቃላይ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ (እ.ኤ.አ. 28/12/2011)
እንደ ቤተሰብ በጋራ መጸለይ ያለው ውበት ዳግም ማረጋገጥ
ውድ ወንድሞቼ እና እህቶቼ


የድንግል ማርያም ሮሳሪየም” በሚል ርእስ ሥር የደረሱት ሐዋርያዊ መልእክት) የመቁጸርያ ጸሎት ከእርሷ ጋር ውህደት በመፍጠር ምሥጢረ ክርስቶስ በማስተንተን ላይ የጸና በመሆኑም የዚሁ ጸሎት አርአያ እርሷ ነች ለማለት እንበቃለን።
የማርያም በእግዚአብሔር እይታ መኖር ብቃት የሚጋባ ነው። የዚህ RealAudioMP3 ቀዳሚው ምስክርም ቅዱስ ዮሴፍ ነው። የእርሱ ትሁት እና ቅን ለእጮኛው ማርያም ያለው ፍቅር እና ቍርጥ ፍቃድ መሠረት ሕይወቱ ከማርያም ሕይወት ጋር አስተባበረ። ወንጌላዊው ማቴዎስ ምዕራፍ 1 ቁጥር 19 “እጮኛዋ ዮሴፍ ግን ጻድቅ ነበርና” ሲል የገለጠው ማንነት በማርያም እንዲማረክ ከእርሷ ጋር እንዲተዋወቅ ያደረገው ከእዝአብሔር ጋር ያለው ጥልቅና ልዩ ግኑኝነት መሆኑ ያረጋግጥልናል። ከማርያም በተለይ ደግሞ ከኢየሱስ ጋር ከእግዚአብሔር ጋር አዲስ ዓይነት ግኑኝነት በማጽናት በሕይወቱ እግዚአብሔርን ለየት ባለ አዲስ መንፈስ አማካኝነት በማስተናገድ፣ የእግዚአብሔርን ፍቃድ በመፈጸም በእግዚአብሔር የማዳን ቅዱስ እቅድ ሱታፌው ይጀመራል። ማቴዎስ ወንጌል ምዕ. 1 ቍ. 20 “እጮኛህን ማርያምን ለመውሰድ አትፍራ” ሲል መልአኩ በሰጠው መመሪያ ላይ እማኔ በማኖር ማርያም ከርእሱ ጋር በመውሰድ የእርሷን ዕለታዊ ሕይወት በመካፈል ሁለመናውን ለማርያምና ለኢየሱስ በመስጠት፣ ለተሰጠው ጥሪ ፍጹምና ታማኝ መልስ እንዲሰጥ አድርጎታል። ወንጌላውያን የቅዱስ ዮሴፍ ቃል ኅላዌው ታማኝ የአገልግሎት መንፈስ የተካነው የጽሞና ፍሬ እንደሆነ ይገልጡልናል። እርሱም እንደ እጮኛው ማርያም እና ከእርሷ ጋር በሙሉ መግባባት አማካኝነት የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጨቅላነት እና የጉርምስናው ጊዜ ማለትም የኢየሱስ ኅልውና በዚያች ቤተሰብ አጣጥሞ የኖረ ነው። የአባትነት ኃላፊነቱን በሁለመናው በሙላት የኖረ ነው። በርግጥ እንደ ያይሁድ ሃይማኖት ባህል መሠረት ለኢየሱስ ጸሎት አስተምሮታል፣ ቅዳሜ በሚፈጸመው የጸሎት ሥነ ሥርዓት እንዲሳተፍም ወደ ሙክራብ ወስዶታል፣ በእለታዊ ኑሮአቸውም እንደ አባት መጠንም ቤተ ሰብአዊ ጸሎቶችን መርቷል፣ እንዲህ ካለው የናዝሬት ቤተ ሰብ ዕለታዊ ኑሮ እና ከዮሴፍ የአናጢነት ተግባር፣ ኢየሱስ ጸሎትን እና ሥራን በማፍቀር ለቤተ ሰብ አስፈላጊ የሆነው ዕለታዊ እንጀራ ለማግኘት የሚያበቃው ድካም ለእዚአብሔር ማቅረብን ተምሯል።
ቅድስት ቤተሰብን በጸሎት ላይ እያለች የሚገልጥ አንድ ታሪክ አለ፣ ኢየሱስ 12 ዓመት ዕድሜ እያለው ወላጆቹ ወደ ቤተ መቅደስ እንዳቀረቡት እርሱም ቅዱስ ሉቃስ በምዕራፍ 2 ከቁጥር 41 እስከ 42 እንደሚገልጠውም “ወላጆቹ በየዓመቱ ለፋሲካ በዓል ወደ ኢየሩሳሌም ይሄዱ ነበር። ዐሥራ ሁለት ዓመትም በሞላው ጊዜ እንደ አስለመዱ ወደ ኢየሩሳሌም ለበዓሉ መጡ።” ይህ ዓይነት ንግደት በጸሎት የሚገነባና በጸሎት የሚፈጸም የሃይማኖት መግለጫ ነው። ይኽ በፋሲካ በዓል የሚኖረው መንፈሳዊነት የኢየሱስ ቤተሰብ በየዓመቱ እንደሚኖሩትና በቅድስት ከተማ በሚፈጸሙት ሥርዓቶች ተሳታፊዎች መሆናቸው ያረጋግጥልናል። የአይህዱ ሃይማኖት ተከታይ ቤተሰብ ልክ እንደ ክርስትያን ቤተሰብም ቤተሰብአዊ ጸሎት እንዲሁም የተጓዡ ሕዝበ እግዚአብሔር ክፍል መሆኑ በመገንዘብም ከማኅበረ አማኞች ጋር ይጸልያል። የዚህ ሁሉ ማእከል እና ፍጻሜም ቤተሰብን እና ይፋዊ የሆነው ማኅበራዊው የአምልኮ ሊጡርጊያ የሚኖርበት ፋሲካ ነው።
በዚህ ኢየሱስ ዐሥራ ሁለት ዓመት ዕድሜ እያለው በሚያወሳው የወንጌል ታሪክ ኢየሱስ የተናገራቸው የመጀመሪያ ቃላቶች “ለምን ትፈልጉኛላችሁ” የሚሉት መሆናቸውም በሉቃስ ምዕ. 2 ቍ. 4 ተዘግቦ እናገኛለን፣ ወላጆቹ ለሶሦት ቀናት ከፈለጉት በኋላ፣ በቤተ መቅደስ በሊቃውንት መካከል ተቀምጦ ሲሰማቸና ሲጠይቃቸው አገኙት” (ሉቃ. ምዕ. 2 ቍ. 49)። ለወላጆቹ “በአባቴ ቤት ልኖር እንደሚገባኝ አላወቃችሁምን?” (ሉቃ. ምዕ. 2 ቍ. 49) በሚሉት ቃላት ይመልስላችዋል። ይኽ በእርሱ የተገለጠው “አባት” የሚለው ቃል ወደ የክርስትያን ጸሎተ ምሥጢር የሚያስገባ ቁልፍ ነው። ኢየሱስ በአንድ ወቅት “በምትጸልዩበት ጊዜ እንዲህ በሉ፦ በሰማያት የምትኖር አባታችን ሆይ…” በማለት ለደቀ መዛሙርቱ ባስተማራቸው ጸሎት ይገልጠዋል። ሆኖም ቀደም በማድረግ ያ ኢየሱስ አባቴ “የበክር ልጅ መሆኑ ያለው ግንዛቤ በሚመሰክር ለማርያምና ለዮሴፍ በሰጠው መልስ የገለጠው ቃል፣ በዚያች የናዝሬት ቤተሰብ ያሳደረው መንፈስ ለመገመቱ አያዳግትም። የአብ ቤት በመሆኑም፣ እዛው በቤተ መቀድስ ለሶሥት ቀን ቆይተዋል። ከኢየሱስ ሕፃንና ጎርማሳ ልብ አማካኝነት የሚገለጠው በማርያም እና በዮሴፍ የሚስተነተነው ከእግዚአብሔር ጋር ያለው የጥልቅ ግኑኝነት ትርጉም አባቴ በሚል ኢየሱስ የገለጠው ቃል የቅድስት ቤተ ሰብ ሕይወት በጸሎት እጅግ የተሞላ እንዲሆን አድርጎታል። ቅድስት ቤተ ሰብ በኢየሱስ ዙርያ የምትሰበሰብ እና ከእግዚአብሔር ጋር ያለው የውሉድነት መንፈስ ዕለት በዕለት ካለ ማቋረጥ የሚኖር መሆኑ በሚገልጠው ከሌሎች ጋር ለሚደረገው ግኑኝነት መሠረት የሆነው የሚስተነተንባት ቀዳሜ የቤተ ክርስትያን አብነት ነች።
ውድ ወዳጆችቼ፦ ወንጌልን ተንተርሼ አጠር ባለ መልኩ በመከፋፈል ቅድስት ቤተ ሰብ፣ በኅብረት ለመጸለይ የተጠራችው የቤተሰብአዊ ቤተ ክርስትያን ምስል መሆንዋ ገልጫለሁ፣ ቤተሰብ የመጀመሪያ የጸሎት ትምህርት ቤት ነች። በእርሷ ዘንድ ሕፃናት ልጆች ገና ከጨቅላነት ዕድሜአቸው ወላጆች ለሚሰጡት አብነት የተመሰገነ ይሁንና የእግዚአብሔር ትርጉም የሚገነዘቡበት ቤት ነው። እውነተኛው ክርስትያናዊ ሕንጸት ከጸሎት ተመክሮ ፈጽሞ የማይነጠል ነው። በቤተሰብ ዘንድ ጸሎት መጸለይ አለመማር፣ በዚሁ መንፈሳዊ እጥረት ምክንያት በኋላ የሚፈጠረው ባዶነት ለመሙላት እጅግ ያዳግታል። በናዝሬት ቤተሰብ ትምህርት ቤት አብነት መሠረትም፣ እንደ ቤተሰብ በጋራ የጸሎት ውበትን ዳግም እንድታረጋግጡና በዚህ መሠረትም እንደ የናዝሬት ቅድስት ቤተሰብ አንድ ልብ እና አንድ መንፈስ እንድትሆኑ አደራ ስል እጋብዛችኋለሁ። አመሰግናለሁኝ ካሉ በኋላ በዚህ ቫቲካን በሚገኘው ር.ሊ.ጳ. ጳውሎስ ስድስተኛ የጉባኤ አዳራሽ ከውስጥ እና ከውጭ ለመጡት በብዙ ሺህ የሚገመቱት ተሳታፍዎች ምእመናን በተለያዩ ቋንቋዎች ሰላምታን አቅርበው ሐዋርያዊ ቡራኬ ሰጥተው ሁሉንም ወደ መጡበት አሰናብተዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.