2011-12-27 09:52:10

የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ስብከት ፡


ትናትና ዕለት እኤአ ታህሳስ 25 ቀን 2011 በላቲን ሥርዓተ አምልኮ በየዓመቱ የሚከበረው የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል ዘንድሮም በታላቅ መንፈሳዊ ስሜት ተከብሮ ውለዋል።

ቅዱስ አባትችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ 16ኛ እኩለ ለሌት ላይ በብዙ ብፁዓን ካርዲናላት ጳጳሳት እና ካህናት ተሸኝተው በቅዱስ ጰጥሮስ ካተድራል ሥርዓተ ቅዳሴ መርተዋል።

ቅድነታቸው የገና በዓል ቅዳሴ በመሩበት ግዜ ባሰሙት ስብከት በሮማ እና በመላ ዓለም የምትገኙ የተወደዳችሁ ውንድሞቼ እና እኅቶቼ ክርስቶስ ለኛ ተወልደዋል ኢየሱስ እንደ ሕፃን ከሰማየ ሰማያት ወርዶልናል ስብሐት ለእግዚአብሔር ይሁን ለሚወዳቸው ሁሉበምድር ሰላም ይሁን ፡ ከእግዚአብሔር የሰላም መልእክት ለመላ ዓለም አዳርሰዋል ብለዋል።

ምእመናን ለድሆች እና ለስደተኞች ለተቸገሩ ሁሉ እንዲጸልዩ እና ክብረ በዓሉ ከፍ ባለ መንፈስ እንድያከብሩት ቅድስነታቸው አሳስበዋል።

ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ የገና በዓል በቅዱስ ጰጥሮስ መስዋዕተ ቅዳሴ ባሳረጉበት ግዜ እና በመሩበት ግዜ ባሰሙት ስብከት አያይዘው ፡

የእግዚአብሔር መልካምነት እና ፍቅር ወሰን የለውም ስለሆነም በልደተ እግዚአብሔር ግዜ ከፍተኛ ደስታ እንዲሰማን ይገባል ብለዋል።

ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሕፃን ታየን እና ሰላም ይዞልን መጣ በአሁኑ በተለያዩ የዓለም ክፍላት የሚታየው ሁከት ግጭት እና ደም መፋሰስ የገና ልደት ሰላም እንድያወርድልን እንጸለይ እናስተንትን ብለዋል ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ።

ስብከታቸው በማያዝዝ ከክርስቶስ ሕጻን ጋር ሆነን ሰላም እናሰፍን ዘንድ በሱ አምነን ካሱ ጋር ሆነን የሰላም መንገድ መያዝ መከተል ከሱ ጋር መራመድ ይጠበቅብናል ብለዋል።

ቅዱስ ፍራንቸሶ ዘ አሲሲ ልደተ እግእነ ወመድኀኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ የበዓሎች በዓል ያለውን አስታውሰው በሰላም እጦት እየተሰቃየች የምትገኘውን ዓለም ሰላም እንዲሰፍንባት ክርስቶስ ህጻንን እንለምን ብለዋል ።

ኢየሱስ ሕጻን የሰው ልጅ ከነበረበት አስከፊ ሁኔታ ለማዳን በቤተልሔም ተወልዶ የእግዚአብሔር ፍቅር አምጥቶ አሳየ ሰውን ለማዳን ኀያል እያለ ደካማ ሆኖ ለሰው ተገለጸለት ያሉ ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ የሰው ልጆች በዚሁ በዓል ሊደስቱ የእግዚአብሔር ፍቅር እንዲሰማቸው ይገባል ብለዋል ቅዱስ አባታችን በነዲክቶስ ።

የገና ትርጉም ከተሞችን ማሸብረቅ እና መገበያየት እውነተኛ የገና ምስጢር መጋረድ እንደሌለበት ቅድስነታቸው በስብከታቸው ላይ አጽንኦት ሰጥተው አመልክተዋል።

እውንተኛ ደስታ እውነተኛ የገና ብርሃን ለማግኘት ኢየሱስ ሕጻን የተወለደበት ቤተልሔምን መሕልናችን መኘት እንደሚጠበቅብንም ጨምረው ሰብከዋል።

የሰው ልጅ ከእግዚአብሄር ጋር ለመገናኘት በንጽሕና ልቡ ከፍቶ ወልደ እግዚአብሔርን ፍለጋ መራመድ እንደሚጠበቅበት አክለው ተናገዋል ።

የሰው ልጅ በትዕቢት ከተወጠረ እና አቅሙ ለይቶ ካልተገነዘበ ከትሑት እግዚአብሔር ጋር መገናኘት እንደማይችል ጠቅሰው እግዚአብሔር ከሰው እውቀት በላይ ነው በማለት በቅዱስ ጵጥሮስ ካተድራል በላቲን ሥርዓተ የገና ሥራዓተ ቅዳሴ በመሩበት ግዜ አስገንዝበዋል።

በገና ግዜ አማንያን ሁሉ በተለያዩ ምክንያቶች ስለ ሚሰቃዩ የድኅነት ሰለባ ስለሆኑ የሚወድዋቸው ቤተ ሰቦቻቸው ጥለው ስለ ሚሰደዱ በሁከት እና በግጭት ሰላም ስላጡ እንዲጸለዩ አሳስበዋል ።



ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ከሥርዓተ ቅዳሴ ፍጻሜ በኃላ የጓተማላ የደቡብ ኮርያ የጋቦን የቡርኪና ፋሶ የሚገኝባቸው ሕጻናት ጋር ተገናኝተው አብሮዋቸው የኤየሱስ ሕጻን ሥርዓተ ጸሎት ደግመዋል አንተ ከሰማይ የወርድክ መንፈሳዊ መዝሙር ተዘምሮ የቅዳሴው ፍጻሜ ሁነዋል ።








All the contents on this site are copyrighted ©.