2011-12-23 15:00:06

ብፁዕ አቡነ ጆርዳኖ፦ “በብቸኝነት በሽታ የተጠቁት የኤውሮጳ ዜጎች ፈውስ የአንድ አባት ልጆች መሆናቸው የሚያሰጣቸው የወንድማማችነት መንፈስ ዳግም መሻት ነው”።


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ለቅድስት መንበር የኵላዊት ቤተ ክርስትያን ለቅርብ ተባባሪዎቻቸው ለሆኑት የበላይ ሓዋርያዊ መሥተዳድር አባላት ብፁዓን ካርዲናሎች እና ብፁዓን ጳጳሳት እንደ ተለመደው የመልካም በዓለ ልደት ምኞች ለመለዋወጥ የሚከናወነው ግኑኝነት እና መሪ ቃል የመለገሱ እቅድ መሠረት፣ RealAudioMP3 ትላትና ጧት ቫቲካን በሚገኘው ቀለመንጦስ የጉባኤ አዳራሽ ብፁዓን ካርዲናሎች እና ብፁዓን ጳጳሳት ተቀብለው ባሰሙት ቃል፣ በኤውሮጳ ተከስቶ ያለው የኤኮኖሚ እና የገንዘብ ሃብት ቀውስ ቀዳሚ መሠረቱ የሥነ ምግባር እና የእምነት ቀውስ ነው በማለት፣ ገና የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ሆነው ከመሾማቸውም በፊት በተለያየ ወቅት ያመለከቱት ሃሳብም ሲሆን፣ ይኸንን ሐሳብ አሁንም በሰጡት መሪ ቃል እንዳሰመሩበት በኤውሮጳ ኅብረት የቅድስት መንበር ቀዋሚ ታዛቢ ብፁዕ አቡነ አልዶ ጆርዳኖ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ በማስታወስ፣ ቅዱስ አባታችን የኤውሮጳው ወቅታዊው ሁኔታ በጥልቀት በመመርመር በሚሰጡት አስተምህሮ እና ምዕዳን፣ በእርግጥ በኤውሮጳ አንድ መሠረታዊ ሃሳብ፣ መሠረታዊ የሕይወት ትርጉም፣ ራእይ እና የእምነት መጓደል ኤውሮጳ እያጋጠማት ላለው ዘርፈ ብዙ ቀውሶች ምክንያት መሆኑ አመልክተዋል። ማንኛውም ሥልጣኔ ኅያው የሚሰኘው እና ሂደቱን የሚመራው ከእምነት ከሚመነጨው መሠረታዊ ድጋፍ ውጭ ዘላቂነት ሊኖረው አይችልም፣ ግብረ ሐዋርያት ምዕራፍ 4 ቁጥር 34 “በመካከላቸው አንድ ስንኳ ችግረኛ አልነበረምና መሬት ወይም ቤት ያላቸው ሁሉ እየሸጡ የተሸጠውን ዋጋ ያመጡ ነበርና በሐዋርያትም እግር አጠገብ ያኖሩ ነበር፣ ማናቸውም እንደሚፈልግ መጠን ለእያንዳንዱ ያካፍሉት ነበር” ሁሉም የሁሉም ነበር፣ ማንም ችግረኛ አልነበረም የሚለውን ቃል ጠቅሰው፣ ይኽ የቀደምት ክርስትያኖች የማኅበራዊነት ኑሮ በሁሉም መስክ ይኖር ነበር። እውነተኛው ደስታ ማኅበራዊነት እርሱም የአንድ አባት ልጆች ከመሆናችን ከሚረጋገጠው ወንድማማችነት እንጂ ብቸኝነት ራስ ወዳድነት ግለኝነት በመኖር የሚገኝ አይደለም፣ በአሁኑ ወቅት በኤውሮጳው በመስፋፋት ላይ ያለው በሽታ የብቸኝነት ኑሮ ነው። የሉአላዊነት ጎዞ የብቸኝነት ግብ ያለው እየሆነ ሰብአዊነት እየተዘነጋ መሠረታዊ የኅልውና ጥያቄ መልስ የሆነው በእምነት የሚገለጠው በሞት ላይ ድል የነሣው ሕይወት ያረጋገጠው እግዚአብሔር ችላ እየተባለ ነው። ስለዚህ ኤውሮጳ ከተጋፈጣት ዘርፈ ብዙ ችግሮች ለመላቀቅ ሥነ ምግባር እና እምነትን መተባበር መደጋገፍ መቀራረብ መተሳሰብ የሚያረጋግጠው ወንድማማችነት ዳግም መርኖ ይኖርባታል በማለት የሰጡትን ቃል ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.