2011-12-22 10:03:11

የገና አጠባበቅ አግባብ ፡


ልደተ ክርስቶስ ለማኽበር በጣት የሚቆጠሩ ቀናት ቀሩ እንዴት እንጠበቀው ከቤተልሔም ተነስቶ ዓለምን በሚነካ የብርሃን ጨረር እንዲነካን ይሁን ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ክብረ በዓሉን በማሰብ ያመለኩትት ነው ክቡራት እና ክቡራን አድማጮች በዚሁ በተያዝነው መጨረሻ ሳምንት በጎርጎርዮስ አቁጣጠር ታሕሳስ 25 ቀን በላቲን ሥርዓተ አምልኮ ልደተ ክርስቶ ነው ።

መጠባበቅ ልደተ ክርስቶስ ለህዝበ ክርስትያን የተስፋ እርግጠኛነት መሆኑ የገለጹት ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ፡ መድኅን ዓለም ክርስቶስ ሕፃን የሚያመጣው ብርሃን ፍርሐት እና መጠራጠን ይደመስሳል ብለዋል።

የክርስቶስ ብርሃን ኀያል መሆኑ ህዝበ ክርስትያን በመገንዘብ ልቡ በተስፋ ይሞላል ያሉት ቅድስነታቸው የሰብአ ስገል በአጠቃላይ ሐሳብ ነበራቸው ከሰማየ ሰማያት መልእክት መምጣቱ የመጠበቅ ግዜ መጠናቀቁ አዲስ ግዜ መጀመሩ ተረድተዋል ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ፡

ከሁለት ሺ ዓመታት የመድኅን ክርስቶስ ምጽአት በኃላ የሚጠበቅ ነገር የለም ሆኖም ክብረ በዓል ልደተ ክርስቶስ በንጠባበቅበት በአሁኑ ግዜ ምንድነው የምጠብቀው ብለን መጠየቃችን አይቀርም የምንጠበቅው ተስፋ ነው የምንጠብቀው ብርሃን ነው። በነዲክቶስ 16ኛ ።

የሕይወታችን ሂደት የምንመረምርበት ወቅት ነው ውቅቱ ያሉት ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ፡ የቤተልሔም የብርሃን ጨረር እንዲነካን ብርሃኑ ራሱ ክርስቶስ መሆኑ ጠቅስውም እሱ አብይ እያለ ትንሽ የሆነ ኀያል እያለ ደካማ ሆኖ የቀረበ ክርስቶስን ልባችን ከፍተን በደስታ እንቀበለው ብለዋል።

ከሁለት ሺ ዓመታት በፊት የክርስቶስ ምጽአት ለማብሰር የበራው ኮከብ ሰብአ ሰገል እና ገበሬዎች ክርስቶስ የተወለደበት ቦታ ለቀው እንደሄዱ አልጠፋም አሁንም እየበራ ነው ፡ ብርሃኑ ወልደ እግዚአብሔር ክርስቶስ ነው እና በደስታ እና በፈንጠዝያ እንቀበለው ብለዋል ቅድስነታቸው ።

አያይዘው ቅዱስ አቦና ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ በማያያዝ ወልደ እግዚአብሔር ከሰማየ ሰማያት የወረደው እኩ ነገራት ለመደምሰስ ለሰው ልጅ ከሐጢአቱ ለማዳን ብርሃን እና ተስፋ ለመስጠት እንደሆነ ህዝበ ክርስትያን ይህን ተገንዝበን ክብረ በዓሉ በታላቅ ተስፋ እና ጉጉት እንቀበለው ሲሉ አስገንዝበዋል።

አለ ክርስቶስ መጻኢ ግዜ ጨለማ ነው በሱ ለሚያምኑ ግን በክርስቶስ ወንዘ/ብርሃን ብርሃን እና ተስፋ ነው ህዝበ ክርስትያን የክርቶስ የማይጠፋ ብርሃን መሆኑ በመገንዘብ በዚሁ ብርሃን ብርቱ ናቸው የመጻኢ ግዜ ራእይ ስላለቸው እና ደስተኞች እንሁን አንጨነቅ ሁሉም በወልደ እግዚአብሔር እጅ ስላለ በነዲክቶስ 16ኛ ።

ክርቶስ የመጣው ፍርሐት ድንቁርና ተስፋ ቢስነት ሐሰት ኢ ፍትሐዊነት በነገሰበት ዓለም ነበር ክፉውን ወደ ሰናይ ለወጠ ጨለማው ብርሃን አደረገ እና ጽኑ እምነት እንዲኖረን ያስፈልጋል በለዋል ቅዱስ ኣአባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ልደተ ክርስቶስን በማሰብ ።








All the contents on this site are copyrighted ©.