2011-12-21 14:50:56

የናይጀሪያ ብፁዓን ጳጳሳት የሰላም ጥሪ


በናይጀሪያ ሰሜናዊ ክልል እ.ኤ.አ. ታህሳስ 18 ቀን 2011 ዓ.ም. በማሊካሊ ክፍለ ሀገር ዋና ከተማ ሪማስተ ዳር በሚገኘው በአንድ ሕገ ወጥ መለስተኛ ፋብሪካ በደረሰበት ፍንዳታ አደጋ RealAudioMP3 ሳቢያ አንድ ሰው ለሞት እና ቁጥራቸው ከፍ ያለ ለመቁሰል አደጋ እንዳጋለጠ የሚዘከር ሲሆን፣ ተጠያቂው ገዛ እራሱ ቦኮ ሃራም በሚል መጠሪያ የሚለየው ፍልቃቂ የምስልምና ሃይማኖት ወገን መሆኑ ሲነገር፣ የፍንዳታ አደጋ የደረሰበት መለስተኛው ፋብሪካ አነስተኛ የፍንዳታ ቦምቦች ማምረቻ እንደነበርም የአደጋው ሳቢያ ለመጣራት የተላከው የክልሉ የፀጥታ ኃይል አባላት ሰነድ ያረጋገጣል። ይህ ደግም በዚያ ክልል የተለያዩ ተመሳሳይ ለፍንዳታ አደጋ የሚያገለግሉ አነስተኛ ቦምቦች የሚመረትባቸው ሕገ ወጥ ፋብሪካዎች በመለየት በቁጥጥር ሥር ለማዋል እንዳስቻላቸውም እና ባኮ ሃራም ፍልቃቂ የምስልማ ሃይማኖት አክራሪው ወገን ዋናው ምሽጉ ያደረገበት ክልል መሆኑም የፀጥታ ኃይሎች መረጃ ይጠቁማል። እ.ኤ.አ. ታህሳስ 17 ቀን 2011 ዓ.ም. በደረሰው ተመሳሳይ የፍንዳታ አደጋ ሳቢያ የሞት አደጋ የደረሰባቸው ዜጎች የዚያ ቦኮ ሃራም ቡድን አባላት መሆናቸው የናይጀሪያ የፀጥታ ኃይል መግለጫ ሲያመለክት፣ የናይጀሪያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት በአቡጃ ባካሄደው ስብሰባ የዚህ አይነቱ አደጋ ለእርስ በእርስ እልቂት ምክንያት የሆነው ምርጫ ለማንም የማይበጅ ነው። ሌላውን በማጥፋት የሚገኝ ሰላም ፈጽሞ የለም፣ ስለዚህ ሕዝብ ለእርቅ በመጋበዝ ፍትህ እና ሰላም እንዲረጋገጥ በማሳሰብ፣ ናይጀሪያ ኅብረ ሃይማኖት ኅብረ ባህል እንዲሁም ኅብረ ጎሳ በሰላም ተዋህዶ የሚኖርባት አገር ስትሆን ብቻ ነው ማኅበራዊ ሰላም ሊሰፍንባት የሚችለው፣ ዓመጽ እና የውድመት ምክንያት የሆነውን ሁሉ በማውገዝ የናይጀሪያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት የሰላም ጥሪ አስተላልፈዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.