2011-12-21 14:42:45

ብፁዕ ካርዲናል በርቶነ፦ በእግዚአብሔር ፍቅር ላይ የጸናው ተስፋ


የቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ ብፁዕ ካርዲናል ታርቺዚዮ በርቶነ ትላትና ጧት ሮማ በሚገኘው ሕፃነ ኢየሱስ አቢይ ሀኪም ቤት ሥር በሚተዳደረው የሕፃናት ማከሚያ ቤት የሚገኙትን ሕፃናት የመልካም በዓለ ልደት ምኞት ለመግለጥ እና ለኅሙማን ሕፃናትን የቤተ ክርስትያን እናታዊ ፍቅር በቅርብ ለመመስከር የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ሐዋርያዊ ቡራኬ ለማቅረብ ጎብኝተው ባሰሙት የተስፋ ቃል፣ ቅዱስ አባታችን የሀኪም ቤቱ RealAudioMP3 ሂደት እና አገልግሎት በጥንቃቄ እንደሚከታተሉት እና የዚህ ሀኪም ቤት የሕጻናት ማከሚያ ቤት የሚሰጠው የተዋጣለት አገልግሎት መቼም ቢሆን እንዳይጓደል የሚሰጡት ትኵረት ለሀኪም ቤቱ ሠራተኞች እና ለጤና ጥበቃ ባለ ሙያዎች አረጋግጠዋል።
በዓለ ልደት የሕፃናት በዓል ነው። አንድ ሕፃን ባለበት ሥፍራ ሰማያዊ ቤት ኅያውነቱ እና ሕፃን ሰማያዊ ቤት ለዓለም የሚለግሰው ውበት እና የእዚግአብሔር ቸርነት ማረጋገጫ ነው። በዚያ የሕፃናት ማከሚያ ቤት ያሉት ሕፃናት ያለባቸው ስቃይ በእውነቱ የሕፃናቱ ስቃይ አማካኝነት የሰው ዘር የተስፋ መንገድ በማግኘት በዕለታዊ ኑሮ ጠንቅቆ ለመገንዘብ የማይቻለውን እውነተኛው እና መሠረታዊው የሕይወት ትርጉም በጥልቀት ለመረዳት የሚያበቃ መንገድ ነው።
ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. እ.ኤ.አ. ለ2012 ዓ.ም. አዲስ ዓመት መግቢያ ቀደም በማድረግ ባስተላለፉት ኵላዊ የሰላም መልእክት በመጥቀስ ብፁዕ ካርዲናል ታርቺዚዮ ተስፋው የሚገኘው በእግዚአብሔር ዘንድ ነው። ዓለምን የሚያድነው ኅልዮ ሳይሆን ኅያው ፈጣሬ ኵሉ “እውነት እና መልካም” የእውነተኛው ነጻነታችን ዋስትና የሆነው እውነተኛው እግዚአብሔር ነው። ስለዚህ የሕይወት ቍንጮ አንድ ብቻ ነው እርሱም ፍቅር ነው ብለዋል።
የሕፃነ ኢየሱስ ሀኪም ቤት በዘመናዊነቱ እና በሚሰጠው አገልግሎት ያለው የሥነ ምርምር እድገት የተዋጣለት እና ደስ የሚያሰኝም ነው፣ ሆኖም ይህ ሁሉ ስኬት ኅሙማን በማስተናገድ በፍቅር የተደገፈ ሰውን ማእከል ያደረገ የተሟላ እና ተገቢ የህክምና አግልግሎት የመስጠት ዓላማው በተለይ ደግሞ ለሕፃናት በሚሰጠው አገልግሎት በመመስከር እንዲኖረው አደራ በማለት፣ የሀኪም ቤቱ ሠራተኞች የጤና ጥበቃ ባለ ሙያዎች ፈቃደኝነት የተጋድሎ መንፈስ ትዕግሥት እና የሚሠዋ ፍቅር የሚኖር አገልግሎት ለማቅረብ የሚችለው በእያንዳንዱ ታማሚው ሕፃን የኢየሱስ ገጽ ሲለይ ብቻ ነው። ስለዚህ የኢየሱስ ገጽ ለይቶ ሲታወቅ የአገልግሎቱ ክብደት ቀላል ይሆናል ካሉ ብኋላ፣ ቅዱስ አባታችን ለሁሉም ኅሙማን ለሀኪም ቤቱ ሠራተኞች በተለይ ደግሞ ለሕፃናት ኅሙማን ቅርብ መሆናቸው እ.ኤ.አ. መስከረም 30 ቀን 2005 ዓ.ም. በሀኪም ቤቱ ያካሄዱት ሐዋርያዊ ጉብኝት የሚመሰከረው ሲሆን፣ ሀኪም ቤቱ በአስፍሆተ ወንጌል ተልእኮ የሚሳተፍ ነው በማለት ቅዱስነታቸው የገለጡት ሃሳብ ብፁዕነታቸው አስታውሰው ከቅዱስ አባታችን የተላለፈው የመልካም በዓለ ልደት ምኞት መልእክት እና ሐዋርያዊ ቡራኬ እንዳቀረቡ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።







All the contents on this site are copyrighted ©.