2011-12-21 14:47:35

ቤተልሔም፣ በዓለ ልደት ለሰላም እና ለፍትህ ምኞት


በእየሩሳሌም የላቲን ሥርዓት የምትከተለው ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ፓትሪያርክ ብፁዕ አቡነ ፉአድ ጥዋል፣ በጋዛ ክልል ለሚኖሩት ለካቶሊክ ማኅበረ ክርስትያን ባሳረጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ RealAudioMP3 ባሰሙት ስብከት፣ ማንኛውም ክርስያን በዓለ ልደት በቤተልሔም የማክበረ እና የመኖር መብቱ ሊከበርለት ይገባል ብለዋል። የእስራኤል የይለፍ ፍቃድ መስጫ ጉዳይ ጽ/ቤት ከ 15 እስከ 35 ዓመት ዕድሜ ክልል የነፈገ ለ 500 የጋዛ ነዋሪ ክርስትያን ምእመናን ለበዓለ ልደት ወደ ቤተልሔም እንዲገቡ ፈቃድ መስጠቱ ሲገለጥ፣ በቤተልሔም በዓለ ልደት ለማክበር የሁሉም ክርስትያን ምእመን መብት ነው ብለዋል።
በዓለ ልደት ሰላም ፍትህ እና የፍልስጥኤም አገር እውቅና ምኞት ያደረገ መሆኑ ጋዜጠኛ ክርስትያን የፍልስጥኤም ዜጋ ቻርሊየ አቡ ሳአድ በመግለጥ፣ እንደ ማንኛው ሕዝብ ነጻ እና በግንብ አጥር ያልተከለለ ሉአላዊ አገር የፍልስጤማውያን መብት ጭምር ነው በማለት፣ ይኽ ደግሞ በፍትህ ላይ ለጸናው ሰላም መሠረት ነው ካሉ በኋላ፣ በዓለ ልደት ይኸንን መንፈስ የሚያንጸባርቅ እና ከሚወለደው ሕፃን ኢየሱስ የሚመኘው ጸጋ ነው ብለዋል።
እ.ኤ.አ. በ 1987 ዓ.ም. አራፋት ለአገረ እስራኤል እውቅና በመስጠት የፍልስጥኤማውያን ለአገረ እስራኤል እውቅና እንዳረጋገጡ ዘክረው፣ ስለዚህ የመንቀሳቀስ መብቱ ተነፍጎ የነገው ሕይወቱ ጨልሞ መኖር በፍልስጥኤማውያን ዘንድ የሚታየው በእስራኤል ውሳኔ የተከሰተው ጫና ሐማስ ለእስራኤል እውቅና እንዳይሰጥ እያደረገ ነው። ስለዚህ በፍልስጥኤማውያን ላይ የሚፈጸመው ጫና ማግለል ለሰላሙ ሂደት አንገብጋቢ ነው በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.