2011-12-20 09:48:18

የቅድስት መንበር ርእሰ አንቀጽ፦ “እስረኞች እንዳይዘነጉ።”


ሁሌ በሳምንት ማገባደጃ የቅድስት መንበር የዜናና ማኅተም ክፍል ተጠሪ የቫቲካን ረዲዮ ዋና አስተዳዳሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ የሚያቀርቡት ርእሰ ዓንቀጽ በመቀጠል፣ ትላትና ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ሮማ በሚገኘው ረቢቢያ የተሰየመው ወህኒ ቤት ያከናወኑት ሐውርያዊ ጉብኝት ማቴዎስ ወንጌል ምዕ. 25 ርእስ በማድረግ የሰው ልጅ በክብሩ በሚመጣበት ጊዜ ከእርሱም ጋር ቅዱሳን መላእክቱ ሁሉ፥ RealAudioMP3 በዚያን ጊዜ በክብሩ ዙፋን ይቀመጣል…እናንተ የአባቴ ቡሩካን ኑ ዓለም ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ የተዘጋጀላችሁን መንግሥት ውረሱ። ተርቤ አብልታችሁኛልና፥ ተጠምቼ አጠጥታችሁኛልና፥ እንግዳ ሆኜ ተቀብላችሁኛልና፥ ታርዤ አልብሳችሁኛልና፥ ታምሜ ጠይቃችሁኛልና፥ ታስሬ ወደ እኔ መጥታችኋልና።” የሚለው ቃለ ወንጌል ማእከል ያደረገ መሆኑ የሚያብራራውን ርእሰ ዓንቀጹን በመቀጠል፣ ብፁዕ ካርዲናል ካሮሎ ማሪያ ማርቲኒ ወህኒ ቤት የአንድ ኅብረተሰብ መሥታወት፣ የአንድ ኅብረተሰብ ሕይወት ነፀብራቅ፣ የአንድ የታመመ ኅብረተሰብ ያለበት የተለያዩ ቅራኔዎችና ስቃይ የሚንጸባረቅበት ሥፍራ እና ሁኔታ ነው ያሉትን ሐሳብ አባ ሎምባርዲ በርእሰ አንቀጹ ጠቅሰው፣ የእስረኞች እና የቤተሰቦቻቸው ስቃይ የወህኒ ቤት ሠራተኞች ያለባቸው ኃላፊነት እና የሚያጋጥማችወ ዘርፈ ብዙ ችግር በወህኒ ቤት እንዲቆይ የተበየነበት እስረኛ ሕንፀት የሚያግኝበት የተሃድሶ ቤት ከመሆኑ ይልቅ ያለበት ችግር የሚያባብስ ሆኖ ይታያል። የአንድ ወህኒ ቤት ተጨብጭ ሁኔታ የአንድ አገር ሥልጣኔ መመዘኛ ነው ብለዋል።
ቤተ ክርስትያን በሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ተልእኮዋ ቅድሚያ ከምትሰጣቸው የኅብረትሰብ ክፍሎች ውስጥ አንዱ፣ ወህኒ ቤት የሚመለከት መሆኑ አባ ሎምባርዲ ጠቅሰው እ.ኤ.አ. በ 1958 ር.ሊ.ጳ. ዮሐንስ 23ኛ በረጂና ቸሊ ወህኒ ቤት እ.ኤ.አ. ታህሳስ 26 ቀን ያካሄዱት ሐዋርያዊ ጉብኝት፣ ቀርቦ የእስረኞች ችግር እና መጻኢን በማዳመጥ የሰጡት ሐዋርያዊ ምስክርነት እንደ አብነት ዘክረው፣ በበዓለ ልደት ወቅት የሚከናወን ሐዋርያዊ ጉብኝት ብቻ ሳይሆን እያንዳንድዋ ቀን የሚመለከት ሐዋርያዊ ኃላፊነት መሆኑ፣ ቤተ ክርስትያን በወህኒ ቤት በካህናት እና በበጎ ፈቃድ የግብረ ሰናይ ማኅበር አባላት ምእመናን እንዲሁ በደናግል በኩል የምትሰጠው አገልግሎት ይመሰክረዋል ብለዋል።
በተለይ ደግሞ በዚህ በዓለማችን እየታየ ያለው የኤኮኖሚ እና የገንዘብ ሃብት ቀውስ እስረኞች እና በድኽነት ጫንቃ ሥር የሚገኙትን የህብረተሰብ ክፍል አባላት ለመዝንጋት ምክንያት እንዳይሆን አባ ሎምባርዲ የቤተ ክርስትያን ጥሪ በርእሰ አንቀጹ አክለው፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. አፍሪካ ሙኑስ-የአፍሪቃ ቃለ ማኅላ በተሰየመው በአፍሪቃ ለምትገኘው ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን የለገሱት ሐዋርያዊ ምዕዳን ዘንድ፣ በአፍሪቃ በተለያዩ ወህኒ ቤቶች የሚገኙት እስረኞች አሰቃቂው ሁኔታ በማስታወስ፣ ፍትህ እርቅ እና ሰላም በማሳሰብ የሞት ፍርድ በመቃወም የሞት ፍርድ ከወንጀለኛ መቅጫ ሕግ እንዲዘረዝ የሕይወት ባህል ማብራራታቸውንም በማስታወስ፣ ር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሐስን ጳውሎስ ዳግማዎ በሁለት ሺሕኛው የኢዮቤል ዓመት ለእስረኞች ምኅረት ይደረግ ዘንድ በይፋ ያቀረቡት ጥሪ፣ ያስተጋባ ሁሉም ምእመናን የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ በሚፈጽመው ሐዋርያዊ ተልእኮ በጸሎት እና በግብረ ሠናይ ተሳታፊ መሆን እንዳለበት የሚያሳስብ ጭምር መሆኑ በመግለጥ ያቀረቡት ርእሰ ዓንቀጽ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.