2011-12-20 09:46:14

የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት የመልአከ እግዚአብሔር ጉባኤ አስተምህሮ(እ.ኤ.አ.18/12/2011)
ማርያም በእግዚአብሔር ሰብአዊ ክብሯ እና ነጻነትዋ የተጠበቀላት ትህትና እና ጥበብ የተሞላች


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ትላትና እሁድ ሮማ በሚገኘው ረቢቢያ የተሰየመው ወህኒ ቤት ሐዋርያዊ ጉብኝት ኣካሂደው እዛው ከእስረኞች ጋር በመገናኘት እና ከእስረኞች ለቀረበላቸው ጥያቄዎች መልስ በመስጠት እምነት ተስፋ ፍቅር መሠረት ሥልጣናዊ አስተምህሮ ለግሰው ወደ አገረ ቫቲካን በመመለስ እኵለ ቀን ከሐዋርያዊ መንበራቸው ካለው መስኮት ፊት ሆነው በአጸደ ቀዱስ ጴጥሮስ ከኢጣሊያ ውጭ እና ውስጥ RealAudioMP3 የተወጣጡ በብዙ ሺሕ የሚገመቱ ምእመናን በተገኙበት ጸሎት መልእከ እግዚአብሔር ከማሳረጋቸው ቀደም በማድረግ፣ በዚህ የበዓለ ልደት መንፍሳዊ ምልክቶች ጎልቶ በሚንጸባረቅበት ወቅት ይኸንን አቢይ የምጽአት ወቅት በእውነተኛው ውስጣዊ ደስታ እንዲኖር ሓደራ ማለታቸው የቅድስት መንበር መግለጫ ይጠቁማል።
በቅድሚያ በደቡባዊ ፊሊፒንስ ክልል የጣለው ኃይለኛው ዝናብ ባስከተለው የጎርፍ መጥለቅለቅ አደጋ ሳቢያ ሰለባ የሆኑትን በተለይ ደግሞ በብዛት ሕፃናት የሚገኙባቸው የሞት አደጋ ላጋጠማቸው ከ650 በላይ የሚግመቱት ከአንድ መቶ ሺሕ በላይ የሆኑት አለ ቤት እና ንብረት ለቀሩት ለተፈናቀሉት ገና ያልተገኙት 800 ዜጎች ሁሉ በማሰብ ቅርበታቸው በማረጋገጥ በጸሎታቸው እንደሚያስቡዋቸው ካረጋገጡ በኋላ፣ በመቀጠል በላቲን ሥርዓት የተገባው ዘመነ ምጽአት ዕለቱ አራተኛው እሁድ ዘብሥራተ ገብርኤል ተብሎ የሚጠራ መሆኑ ጠቅሰው፣ በእግዚአብሔር የማዳን እቅድ የማርያም ድንግልና ያለው አቢይ ትርጉም ነቢይ ኢሳያስ ምዕ 7 ቁጥር 14 “… እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፥ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች።” በማለት የተነበየው ቃል፣ እግዚአብሔር ቃል የገባው በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ትስብእት የሚጠቃለል፣ ማርያም የፀነሰችው ብቻ ሳይሆን የመንፈስ ቅዱስ ሥራ ማለት የእግዚአብሔር ድንቅ ሥራም ነው። በማሕጸንዋ ያደረው ሰው የእርሷ መሆን በመካፈል ኅልውናው ምሉ በሙሉ የእግዚአብሔር የሆነ እንደ መጽሐፍ ቅዱስ ትእምርታዊ አነጋገር እንደማንኛው ሰው ከአመድ የተሠራ ቢሆንም ከላየ ሰማይ የመጣ ነው።
የማርያም ልብ እና አእምሮ ትህትና የተሞላው በመሆኑ እግዚአብሔር በዚህ ልዩ ትህትናዋ አማካኝነት ለወጠው የማዳን እቅድ መረጋገጥ የእርሷ ሰብአዊ ክብር እና ነጻነትዋንም ጭምር በማክበር፣ ከእርሷ እነሆኝ የሚል መልስ የጠበቀ ሲሆን። እነሆኝ የሚል የማርያም መልስ እናትነትን እና ድንግልናን ያጣመረ ሁሉመናዋ ለእግዚአብሔር ክብር የሚል ሲሆን፣ ከእርሷ የሚወለደው ሕፃን ጸጋ መሆኑ የሚያረጋገጥ ነው።
የማርያም ድንግልና ልዩ የማይደገም ሲሆን፣ እያንዳንዱ ክርስትያን የሚመለከት ለእግዚአብሔር ፍቅር ገዛ እራስን ታማኝ በማድረግ በመንፈስ ቅዱስ ድንቅ ሥራ አማካኝነት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን እና መለኮታዊነቱን መቀበል በሕይወት ማስተናገድ ይጠበቅበታል ይህ ደግሞ ልደት ማለት መሆኑ አብራርተው፣ ሁሉም የዚህ ፍቅር መስካሪ እንዲሆን አደራ በማለት ጸሎት መልአከ እግዚአብሔር አሳርገው፣ ሐዋርያዊ ቡራኬ ሰጥተው መልካም ዘመነ ምጽዓት ተመኝተው ሁሉንም ወደ መጡበት ሸኝተዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.