2011-12-20 09:50:32

አባ ካንታላሜሳ “ሰብአዊ እና ክርስትያናዊ ፍቅር-ኤሮስ እና አጋፐ”


የሐዋርያዊ መንበር ሰባኪ አባ ራኒየሮ ካንታላሜሳ እ.ኤ.አ. በ 2011 ዓ.ም. በዓቢይ ጾም ምክንያት በቅድስት መንበር እመ አምላክ ጸሎት ቤት ለቅዱስ አባታችን እና የቅዱስ አባታችን የቅርብ ተባባሪዎች RealAudioMP3 የእንተ ላእለ ኵሉ ቤተ ክርስትያን የበላይ ብፁዓን ጳጳሳት እና ካርዲናሎች በተገኙበት ያቀረቡት ስብከት በሙላት ያጠቃለለ “ኤሮስ ኤ አጋፐ-ሰብአዊ እና ክርስትያናዊ” ፍቅር በሚል ርእስ ሥር ታትሞ ባለፈው ዓርብ እ.ኤ.አ. ታህሳስ 16 ቀን 2011 ዓ.ም. ለንባብ መብቃቱ የቅድስት መንበር መግለጫ አመለከተ።
ኣባ ካንታላሜሳ ለንባብ የበቃው መጽሐፋቸው ርእስ ሥር ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ እ.ኤ.አ. በ 2011 ዓ.ም. ዓቢይ ጾም ምክንያት በሐዋርያዊ መንበር ያቀረቡት ስብከት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ የደረሱዋቸው ዴውስ ካሪታስ ኤስት-እግዝአብሔር ፍቅር ነው የተሰየመው በመቀጠለም ካሪታስ ኢን ቨሪታተ-ፍቅር በሐቅ የተሰመው ዓዋዲ መልእክት ማእከል ያደረገ እንደነበር በማስታወስ፣ ሰብአዊው ፍቅር፣ የአዕምሮ የግዴታ ፍቅር ሳይሆን የሚያነቃቃ ወደፊት የሚገፋፋ ከሌላው ጋር ለመገናኘት የሚገፋፋ፣ የምትገናኘው የፍቅር ምኞች ማረፊያ ይኽ ደግሞ በፍቅር ግኑኝነት የፍቅር መለዋወጥ እንዳለ የሚያመለክት ነው። ሆኖም ግን ይህ ሰብአዊ ፍቅር ኤሮስ ወደ አጋፐ፣ አሳቢው የሚሠዋው ፍቅር በማደግ መሟላት አለበት ካልሆነ ሌላው ለገዛ እራስ እርካታ መሣሪያ ማድረግ ሆኖ ይቀራል።
አንዱ ለሌላው ጸጋ መሆኑ እና ይኽ ደግሞ በምሥጢረ ተክሊል የሚገለጥ የሚኖር እና የሚመሰከር መሆኑ የሚያስረዳ መጽሓፍ ነው።
እግዚአብሔር ሰውን ይመኛል፣ ይኽ ደግሞ በመጽሐፍ ቅዱስ እግዚአብሔር ለእራሱ ብቻ ሕዝቡን ሲፈልግ፣ እንደ እጮኛ ሲንከባከብ፣ ሙሽራ ሙሽራዋን እንደሚፈልግ ሁሉ እግዚአብሔርም ሕዝቡን በዚህ መልእክ እንደሚገልጠው እና እንደሚፈልገው ይገለጣል። ይኽ ደግሞ ሰብአዊው ፍቅር ያለው ክርብ የሚያረጋገጥ ነው። ይኽ ዓይነቱ ፍቅር በዕለታዊ ኑሮአችን መገለጥ አለበት፣ ሌላው ለእኔ መዳን ቤዛ መሆን አለበት የሚለው፣ ስስታምነት እኔ ባይነት መንፈስ እንዲወገድ የሚል፣ እራሱን የሰዋው ፍጹም ፍቀር የክርስትያናዊ እና ሰብአዊ ፍቅር መሠረት ነው። እራስ ጸጋ አድርጎ ማቅረብ ሌላው እንደ ጸጋ መቀበል የሚያስተጋባ ፍቅር ለሰብአዊ ማኅበራዊ እድገት ወሳኝ መሆኑ የሚያብራራ መጽሓፍ ነው በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.