2011-12-19 16:47:09

ር ሊ ጳ በነዲክቶስ ሮማ ውስጥ የሚገኘው እስር ቤት በመጐብኘት እስረኞችን ጠየቀቁ ፡


ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ 16ኛ ትላንትና ረፋድ ላይ ሮማ ከተማ ውስጥ የሚገኘውን ረቢብያ የሰኘው ዓብይ እስር ቤት ጐብኝተዋል።

ቅድስነታቸው በዚሁ እስር ቤት ውስጥ በተለያዩ ወንጀሎች ለእስር ቤት ከተጋለጡ እስረኞች ጋር በተገናኙበት ግዜ እንዳሉት ፡ እግዚአብሔር እንደሚወዳችሁ ልነግራችሁ መጥቻለሁኝ ።

አያይዘው እስረኞች በሚገኙበት ቦታ ክርስቶስ አለ ያሉት ቅድስነታቸው ቅድስት ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን የወንጀል ጥቃት ሰለባ የሆኑ ዕርቅ ፍትሕ እና ሰላም እንደሚያስፈልጋቸው ትገነዘባለች። እስረኞች ሰብአዊ ክብር ያሻቸዋል ብለዋል።

ርሃብተኛች የውጭ ሰዎች በሽተኞች እስረኞች ባሉበት ቦታዎች ራሱ ክርስቶስ የሚገኝበት ቦታ መሆኑ አመልክተው እንዲጐበኝ እንዲታገዝ ይፈልጋል ስለዚህ እዚህ ዛሬ እዚህ መገኘቴ ደስ ይለኛል ።

ዛሬ እዚህ ከናንተ ጋር የሚገኘው ከናንተ ጋር ለመጸለይ ለመወያየት እና ለማዳምጥም ነው በማለት ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳፓጳሳት በነዲክቶስ በረቢብያ ውስጥ ለሚገኙ እስረኞች ገልጠዋል።

ንግግራቸው በማያያዝ የእግዚአብሔር ፍቅር ወሰን የለውም ስለሆነም እሱ እናንተን እንደሚያፈቅራችሁ የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችሁ ለመንገር ነው እዚ የሚገኘው ብለዋል ።

ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ 16ኛ ትናንትና ሰንበት ረፋድ ላይ የረቢብያ እስረኞች በጐበኙበት ግዜ ለእስረኞቹ እንደገለጡት ፡ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የእስር ቤት ተመኩሮ አድርገዋል ፡ ይህ ብቻ አይደለም ፍርድ ቤት ፊት ቀርቦ የሞት ቅጣት ተበይኖበታል ።

ንግግራቸው በማያያዝ ፍትሕን ማረጋገጥ እስረኞችን ዳግም ማስተማር የፍትሕ ስህተት ማስተካከል እንደሚያስፈልግ አመልክተው እስረኞች የተወሰነላቸው የእስራት ግዜ እሰከ ሚጠናቀቅ ሰብአዊ ክብራቸው እና ግርማቸው በማይነካ መልኩ መያዝ አለባቸው ብለዋል ።

በነዲክቶስ 16ኛ ለረቢብያ እሰረኞች ያደረጉት ንግግር በመቀጠል ሰብአዊ እና መለኮታዊ ፍትሕ እዥግ የተለያዩ ናቸው ብለው በእርግጥ ሰዎች መለኮታዊ ፍትሕ ገቢራዊ ሊያደርጉት አይችሉም ግን የሚሰጡን ፍትሕ ትክክለኛ እንዲሆን እንዲታገዙ መለኮታዊ ፍትሕን ማሰብ እና ማስተንተን ይገባቸዋል ሲሉ አመልክተዋል።

እስረኞችን ከማሕበረ ሰብ እና ሕብረተ ሰብ መነጠል ያለባቸውም ያሉት በነዲክቶስ 16ኛ ቅዱስ ጳውሎስ ሐዋርያ ሕግ ሙሉ በሙሉ ማክበር ሲባል ፍቅር ርሕራሔ ማሳየት ማለት እንደሆነ እና ፈሪሐ እግዚአብሔር ሲኖረን እና ለሱ ያለንን ፍቅር ከተገነዘብን የምንሰጠው ሰብአዊ ፍርድ የተስተካከለ ይሆንል ያለውን ጠቅሰው ተናግረዋል።

ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ በዚሁ ትናትና ሰንበት ረፋድ ላይ ሮማ ከተመ ውስጥ የሚገኘው እስር ቤት ውስጥ የሚገኙ እስረኞች በጐበኙበት ግዜ ያደረጉት ንንግር በማያያዝ እስር ቤቱ በእስረኞች ብዛት የተነሳ እሰረኞቹ መጥፎ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ መረዳታቸው ጠቅሰው ይህ ሁለት ቅጣት እንደሚያመለክት ጠቅሰው የመንግስት ባለስልጣናት እንዲያስቡበት ተማጽነዋል።

ልደተ ክርስቶስ ለማክበር አጭር ግዜ መቅረቱ እና ባለስልጣናቱ እስረኞቹን ተስፋ እንዲሰጡ እና በነሱ ላይ የርሕራሔ ተግባር እንዲፈጽሙ አሳስበዋል።

እየሱስ ናዝራዊ ሰዎች ሁሉ በታደሰ ልብ ወደ እግዚአብሔር ሲመለሱ ይደሰታል እና በዚሁ በገና ግዜ ልባችን ማሳደስ ይጠበቅብናል ብለዋል ቅዱስ ኣአባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ 16ኛ የረቢብያ እስር ቤት እስረኞች በጐበኙበት በትናትናው ዕለት ።



በዝምታ በጸሎት እና ባስተንትኖ ሰዎች ሁሉ ከሐጢአት ከእኩይ ተግባር ከትእቢት ከመጥፎ ሐሳብ አራ እንዲወጡ ኢየሱስ ሕጻንን እንልመነው በማለት ቅድስነታቸው አክለው አስገንዝበዋል።

በነዲክቶስ አስራ ስድስተኛ ከተለያዩ እስረኞች የቀረቡልቻው ጥያቄዎችም መልሰዋል ። እስረኞቹ ለቅድስነታቸው ያዘጋጁትን ኬኽ ጣፋጭ ቀምሰው ለእስረኞቹ ሐዋርያዊ ቡራኬ ሰጥተው ተሰናብዋቸዋል ።

ይህ በዚህ እንዳለ ሆኖ የጣልያን የሚኒስትሮች ምክር ቤት የሀገሪቱ እስረኞች ትኩረት ሰጥቶ መወያየቱ እና እስር ቤቶች ከሚገባቸው በላይ እስረኞች በሞምላታቸው መፍትሔ ማፈላለጉ እና 3.300 እስረኞች የቀራቸው 18 ወራት የእስር ግዜ በቤታቸው ቁም እስር ሆነው እንድያሳልፉት መወሰኑ የፍትሕ ሚኒስትር ፓኦላ ሰቨሪኖ አስታውቀዋል ።በጣልያን እስረ ቤቶች ከ25 ሺ በላይ እስረኞች እንደሚገኙ ተገልጸዋል ።

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ እና የጣልያን ርእሰ ብሔር ጆርጆ ናፖሊታኖ የእስረኞች ሰብአዊ መብት እና ክብር እንዲጠበቅ የሰጡት ማሰሳብያ መልካም መሆኑ መንግስት ሁኔታቸው ለማሻሳል በትጋት እየጣረ መሆኑ የፍትሕ ሚኒስትርዋ ፓኦላ ሰቨሪኖ መግለጣቸው የሀገሪቱ መገናኛ ብዙኀን ዘግበዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.