2011-12-17 10:20:59

ር ሊ ጳ በነዲክቶስ በቅድስት መንበር የተመደቡ የ11 ሀገራት አምባሳደራት ተቀበሉ ፡


በግሎባላይዘሽን የኤኮኖሚ ጥምረት በሚካሄድበት በአሁኑ ተከሰተ ኤኮኖምያዊ ቀውስ ለመወጣት በዓለም ሀገራት መካከል ሁነኛ ትብብር ያስፈልጋል ይህን ያስገነዘቡ ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ 16ኛ በቅድስት መንበር የተመደቡ የአስራ ሀንድ ሀገራት አምባሳደራት ተቀብለው ባነጋገሩበት ግዜ ነው ።

ቅድስነታቸው ንግግራቸው በማያያዝ በአጠቃላይ የዓለም ሀገራት ስራ አጥነት ለመግታት በጋርዮሽ ያለሰለሰ ጥረት እንድያካሄዱ ማሳሰባቸው በበነዲክቶስ 16ኛ እና በአምባሳደራቱ መካከል የተካሄደውን ግንኙነት የተከታተሉ የቫቲካን መገናኛ ብዙኀን አመልክተዋል።

የኤኮኖሚ ጥምረት በጋራ መስራት እና በጋራ ማደግ መሆኑ መገንዘብ እንጂ እንደ አሉታዊ ክስተት መታየት እንደማይገባ ቅድስነታቸው ገልጸዋል ሲሉ መገናኛ ብዙኀኑ አክለው አስገንዝበዋል ።

በቅድስት መንበር ለተመደቡ የአስራ ሀንዱ ሀገራት አምባሳደራት በፈረንሳ ቋንቋ ንግግር ያደረጉ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ለሙሉ ሰብአዊ እድገት እና አመርቂ ውጤት ለማስገኘት ትብብር እዥግ አስፈላጊ መሆኑ አጽንኦት ሰጥተው መግለጣቸው ተያይዞ ተመልክተዋል።

ቤተ ሰብ የትብብር ምንጭ መሆኑ እና ከቤተ ሰብ ወደ ማሕበረ ሰብ ብሎም ወደ ሕብረተ ሰብ መሸጋገር ያለበት ጉዳይ መሆኑንም አስምረውበታል በማለት የቫቲካን መገናኛ ብዙኅን ገልጸዋል። ለዚሁ ሁሉ ቤተ ሰብ የመጀመርያ ትምህርት ቤት መሆኑም አክለው መማልከታቸው ተነግረዋል ።

ግብረ ገብ አልባ የኤኮኖሚ ሥርዓት ክስረት እና ውድቀት ያስከትል እና ይህን ተከትሎ ሕብረተ ሰብ ውስጥ አለመረጋጋት እና አለ መጣጣም ስለሚከሰት ሞራል ወሳኝ መሆኑም ማመልከታቸው ታውቆዋል።

ዓለም አቀፍ መረጋጋት እንዲኖር ለወጣቶች ህንጸተ ሞራል መስጠት እና በመተባበር መስራት ምን ያህል አስፈላጊ መሆኑ ማስተማር እና የዚሁ አዎንታዊ ጉዳይ መልካም አርአያ መሆን ግድ ያላል ማለታቸውም ተመልክተዋል።

ብዝሀ ባህሎች እና እምነቶች አዎንታዊ መሆኑ እና ተከባብሮ ተፈቃቅዶ እና ተባብሮ ለመኖር እንደሚረዱም ቅድስነታቸው ማስገንዘባቸው በበነዲክቶስ 16ኛ እና በአምባሳደርቱ መካከል የተካሄደውን ግንኙነት የተከታተሉ የቫቲካን የመገናኛ ብዙኀኑ ካሰራጩት ዜና ለመረዳት ተችለውል።

ቤተክርስትያን በግልጸተ ክርስቶስ በመታገዝ እና በቸረው ብርሃን በመመራት የሚያጋጥምዋት እንቅፋቶች ሁሉ በመሻገር ለህዝቦች መልካም ሰላማዊ ሕይወት እንደምትተባበር ገልጠው ከአምባሳደራቱ መሰናበታቸው ተገልጸዋል።

>< ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ በኤውሮጳ ሕብረት የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ወኪል የነበሩ የሰላሰአ ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ አንድረ ዱፒ በኔዘርላንድ እና በልጅዩም የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ሆነው እንድያገለግሉ

መሰየማቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አመልክተዋል ።

በሌላ በኩል ብጹዕ አቡነ መረክ ሶልዚንስኪ በአርመንያ ረፓብሊክ የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ወኪል እንዲሆኑ ሰይመዋል በማለት መግለጫው አስታውቀዋል።










All the contents on this site are copyrighted ©.