2011-12-16 13:36:01

በድርቅ እና በእርሃብ ለተጠቃው የቀንድ አፍሪቃ ሕዝብ ድጋፍ


በአውስትራሊያ የምትገኘው ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ምእመናን እ.ኤ.አ. ከባለፈው ጥቅምት 2011 ዓ.ም. በድርቅ እና በእርሃብ ለተጠቃው የቀንድ አፍሪቃ ሕዝብ መርጃ RealAudioMP3 የሚውል ከአገሪቱ ፈደራላዊ መንግሥት ጋር በመተባበር ያሰባሰቡት የገንዘብ መዋጮ ድጋፍ ወደ አንድ ሚሊዮን 500 ሺሕ ዶላርድ የሚጠጋ መሆኑ በካሪታስ ለሚጠራው የእንተ ላእለ ኵሉ ቤተ ክርስትያን የተራድኦ ማኅበር በአውስትራሊያ ለሚገኘው ቅርንጫፍ ዋና አስተዳዳሪ ዣክ ደ ግሩት የሰጡት መግለጫ የጠቀሰ ሎ ሶርቫቶረ ሮማኖ የተሰየመው የቅድስት መንበር ዕለታዊ ጋዜጣ አመለከተ።
በዚህ በተካሄደው የገንዘብ መዋጮ ድጋፍ የአውስትራሊያ ሕዝብ በዓለማችን በሚከሰቱት የተፈጥሮ እና ሰው ሠራሽ ችግሮች አማካኝነት ለሚጎዳው ሕዝብ ቅርብ መሆኑ የሚመሰክር ነው። ድኾች ለመርዳት በሚደረገው ማንኛውም ዓይነት ርብርቦሽ አውስትራሊያ በቀዳሚነት ከሚጠቀሱ አገሮች ውስጥ መሆንዋ ደ ግሩት ገልጠው፣ እ.ኤ.አ. በ 2011 ዓ.ም. ድኽነት ለመዋጋት በሚል ዘመቻ ለተካሄደው የድጋፍ ዕቅድ ከአውስትራሊያ የካሪታስ ቅርንጫፍ 9.6 ሚሊዮን እና ባለፈው 2010 ዓ.ም. 9.4 ሚሊዮን ዶላር መሰጠቱ አስታውሰው፣ የገንዘብ ድጋፍ በማቅረብ እቅድ ብቻ ሳይሆን ችግር በደረሰበት ክልል ጭምር የግብረ ሠናይ ማኅበር አባላቶችዋን እንደምታሳትፍ ማስታወቃቸው ሎ ሶርቫቶረ ሮማኖ አስታወቀ።







All the contents on this site are copyrighted ©.