2011-12-16 13:31:40

ቅዱስ አባታችን ከሮማ የመናብርተ ጥበብ ተማሪዎች ጋር ለጸሎት


ትላትና ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በቅዱስ ጴጥሮስ ባሲሊካ የሮማ መናብርተ ጥበብ ተማሪዎች የተሳተፉበት ጸሎት ሠርክ መርተው “እንግዲህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ ጌታ እስኪመጣ ድረስ ታገሡ።”(ያዕ. 5፣ 7) ማእከል በማድረግ ሥልጣናዊ አስተምህሮ መለገሳቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ። RealAudioMP3
በዚህ በትላንትናው ሐሙስ የሶስተኛው የዘመነ ምፅአት ሳምንት ጸሎት መሪ ሐሳብ የሆነው እርሱም በመዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ 27 ቁጥር 8 “አቤቱ፥ ፊትህን እሻለሁ ልቤ አንተን አለ” በሚለው ጸሎት ተመርቶ በሮማ ሰዓት አቆጣጠር ከቀትር በኋላ ልክ ብ11 ሰዓት ተኩል የተካሄደ መሆኑም ሲገለጥ። ይህ በሮማ ኅይነተ የመናብርተ ጥበብ ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ተንከባካቢ ጽ/ቤት የተዘጋጀ፣ የዛሬ 20 ዓመት በፊት እ.ኤ.አ. በ 1991 ዓ.ም. ር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ መልካም ፈቃድ መሠረት የተጀመረ ሲሆን፣ በስፐይን የተካሄደው 26ኛው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ምክንያት በስፐይን መናብርተ ጥበብ ዑደት ያደረገው የቅድስት ድንግል ማርያም መንበረ ጥበብ ቅዱስ ምስል ትላትና የተካሄደው ጸሎተ ሰርክ ከመጀመሩ ቀደም በማድረግ የሮማ ላ ሳፒየንዛ መንበረ ጥበብ ተማሪዎች ከስፐይን መናብርተ ጥበብ ተማሪዎች እጅ መረከባቸም የቅድስት መንበር መግለጫ ሲጠቁም፣ ይህ የጥበብ መንበር ቅድስት ድንግል ማርያም ቅዱስ ምስል መንፈሳዊ ዑደት እ.ኤ.አ. ሰኔ 2012 ዓ.ም. በሚካሄደው ዓለም አቀፍ የመናብርተ ጥበብ አስተማሪዎች ጉባኤ በመድረስ የቅድስት ቸቺሊያ ኦርኬስትራ መዘምራን በሚያቀርቡት መዝሙር በሚሸኘው ሥርዓተ ጸሎት የሚጠቃለል መሆኑ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።







All the contents on this site are copyrighted ©.