2011-12-16 13:29:50

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. ኢሰብአዊ ተግባር ዘወትር ኢምክንያታዊ ነው


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ የቅድስት መንበር ዋና ጸሓፊ ብፁዕ ካርዲናል ታርቺዚዮ በርቶነ ፊርማ የተኖረበት ለኮሎምቢያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ጠቅላይ ዋና ጸሓፊ ብፁዕ ኣቡነ ኹዋን ቪሰንተ ኮርዶባ ለኮሎምቢያ ሕዝብ በተለይ ደግሞ በአገሪቱ በታጣቂ ኃይሎች እጅ የታገቱት የመከላከያ ኃይል፣ የጸጥታ ኃይል አባላት RealAudioMP3 እና ተራ ዜጎች ቅርብ መሆናቸው በማረጋገጥ፣ ሁሉም የታገቱት የአገሪቱ ዜጎች ነጻ ተለቀው በተስፋ ከሚጠባበቁዋቸው ቤተ ሶቦቻቸው ጋር እንዲገናኙ ተማጥነው፣ ቤተ ክርስትያን የታገቱት ዜጎች ነጻ ይለቀቁ ዘንድ የማይታክተው ልመናዋ ወደ እግዚአብሔር ከፍ ከማድረግ ሳትቆጠብና የታገቱት ሁሉ ነጻ እንዲልቀቁ የምታካሄደው ስብአዊ እና መንፈሳዊ ጥረት ቀጣይቱ ማበከራቸው የቅድስት መንበር መግለጫ ሲያመለክት፣ ፈጽሞ ምክንያታዊ ሊሆን በማይችለው እገታ ሳቢያ ለተለያየ ችግር ለተጋለጡት እና ለሚሰቃዩት ለታጋቾች ቤተ ሰብ ቅርብ መሆናቸው እና በጸሎታቸውም ኅያው መሆናቸው በማረጋገጥ፣ የኮሎምቢያ ሕዝብ በጉጉት የሚጠባበቀው ሰላም እንዲረጋገጥ፣ አጋቾች እንዲለወጡ እና ለውይይት ሂደት የተጠመዱ እንዲሆኑ ጌታን ጠይቀው፣ ለሁሉም ሐዋርያዊ ቡራኬ በማቅረብ ለታጋቾች ቤተሰብ የተስፋ እናት የሆነቸው ቅድስት ድንግል ማርያም ቅርብ በመሆን ታበረታታቸው እና በዚህ ቅን መንፈስ ተደግፈውም ያጋጠማቸው ፈተና በተበራታ መንፈስ እንዲጋፈጡት እና ተስፋ ካለ መቁረጥ እንዲጸልዩ አደራ ማለታቸውም የቅድስት መንበር መግለጫ አመለከተ።
የኮሎምቢያ ብፁዓን ጳጳሳት ከቅዱስ አባታችን የተላለፈው መልእክት መሠረት ሁሉም ምእመናንና መልካም ፈቃድ ያላችው ዜጎች በሞላ በዚህ በላቲን ሥርዓት ለሚከበረው በዓለ ልደት የማዘጋጃ ታስእት ስለ ታገጉት ሁሉ ነጻነት እንዲጸልዩ ጥሪ ማቅረባቸው ሲገለጥ፣ ለተወሰኑ ዓመታት የእገታ ተግባር ገታ ብሎ ከቆየ በኋላ እ.ኤ.አ. በ 2010 ዓ.ም. ከፍ ብሎ በመቀጠል በጠቅላላ ባለፈው ዓመት 282 ሰዎች መታገታቸው የኮሎምቢያ የመከላከያ ሚኒስትር ቢሮ መግለጫ ይጠቁማል።








All the contents on this site are copyrighted ©.