2011-12-16 13:33:20

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. ቤተ ክርስትያን የሁሉም እናት ነች


እ.ኤ.አ. እፊታችን እሁድ ታህሳስ 18 ቀን 2011 ዓ.ም. የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ሮማ በሚገኘው ረቢቢያ የተሰየመው ወህኒ ቤት ሐዋርያዊ ጉብኝት በማካሄድ እዛው ከእስረኞች ጋር በመገናኘት እና ከእስረኞች ለሚቀርብላቸው ጥያቄዎች መልስ በመስጠት እምነት ተስፋ ፍቅር መሠረት ሥልጣናዊ አስተምህሮ RealAudioMP3 እንደሚያቀርቡ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።
ቅዱስ አባታችን እ.ኤ.አ. መጋቢት 18 ቀን 2007 ዓ.ም. ሮማ የሚገኘው ካሳል ደል ማርሞ ከ 18 ዓመት ዕድሜ በታች የሆኑት ወጣቶች የሚገኙበት የጸባይ ማረሚያ ወህኒ ቤት ሐዋሪያዊ ጉብኝት አካሂደው እንደነበር የሚዘከር ሲሆን፣ እዚህ ሮማ በሚገኘው ረቢቢያ ወህኒቤት የሚያካሂዱት ሐዋርያዊ ጉብኝት በ 300 ረቢቢያ ወህኒ ቤት ከሚገኙት እስረኞች አማካኝነት አባታችን ሆይ በተሰየመው የወህኒ ቤቱ ጸሎት ቤት ውስጥ አቀባበል እንደሚደረግላቸው የገለጠው የቅድስት መንበር መግለጫ አክሎ፣ በእስርረኞች እና በወህኒ ቤቱ በተለያየ መሥክ ተሰማርተው አገልግሎት በሚሰጡት ዜጎች ጭምር በጉጉት እየተጠበቁ መሆናቸው አመለከተ።
በረቢቢይ ወህኒ ቤት የዛሬ 8 ዓመት በፊት ሐዋርያዊ አገልግሎት መስጠት የጀመሩት የካኖሲያን ደናግል ማኅበር አባል እናቴ ሪታ ደ ግሮሶ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ ብዙዉን ጊዜ እስረኞች በማኅበረሰብ የሚዘነጉ ሆነው ወይንም እያንዳንዱ እስረኛ ያለው ሰብአዊነት እና ሰብአዊ ባህርያቱንም ጭምር ተዘንግቶ ፍርድ የተበየነበት ወንጀለኛ ሰብአዊነቱ በወንጀለኛነት መግለጫ በማጠቃለል የሚገለጥ በመሆኑ። እስረኛው የተበየነበት የእስራት ጊዚያት አጠናቆ ከእስር ነጻ ከሆነ በኋላ ለሚያደርገው ከኅብረተሰብ ተቀላቅሎ የመኖር ሂደቱን ከወዲሁ የሚያሰናክል አመለካከት መሆኑ አብራርተው፣ ስለዚህ እስረኛው ከዚህ ዓይነት ችግር ለማላቀቅ በወህኒ ቤት በበጎ ፈቃድ ማኅበሮች አባላት እና በቤተ ክርስትያን ተልእኮ አማካኝነት በሚፈጸሙት ሐዋርያዊ አገልግሎት ሰብአዊ እና መንፈሳዊ ድጋፍ በማግኘት ወህኒ ቤት የሕንጸት እና የጸባይ ማረሚያ ማእከል እንጂ የኩነኔ ቤት አይደለም በሚል እማኔ መሠረት ተደግፎ ተስፋ ከመቁረጥ ፈተና እንዲላቀቅ ቤተ ክርስትያን ለሁሉም እስረኛ በተለያየ ሐዋርያዊ ግብረ ተልእኮ አማካኝነት ቅርብ በመሆን የተሟላ ሕንጸት ታቀርባለች የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በወህኒ ቤቱ ጉብኝት ይኸንን የሚያበሥር ቤተ ክርስትያን የሁሉም እናት መሆንዋ የሚያረጋግጥ ነው በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.