2011-12-15 15:40:50

ርሊጳ በነዲክቶስ ፊታችን ዓመት ከትንሳኤ በፊት መክሲኮ እና ኩባ እንደሚጐበኙ ተነግረዋል ፡


በላቲን አመሪካ ክፍለ ዓለም የሰፈነውን ድኽነት ለመግታት ስር ሰደድ ኢ ፍሐዊነት የሚፈጸመው ወንጀል እና የሚካሄድወን ሁከት ለማስወገድ ክፍለ ዓለሚቱ የተያዘችውን ጥረት በመጠናከር ትቀጥል ዘንድ ትናንትና ከቀትር በኃላ በቅዱስ ጰጥሮስ ካተድራል በቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ የተመራ ሥርዓተ ቅዳሴ መካሄዱ የቫቲካን የዜና ምንጭ አስታውቀዋል።

በዚሁ የዜና ምንጭ መሠረት ሥርዓተ ቅዳሴ የተካሄደው የጓዳሉፐ ንጽህት ድንግልማርያም መታሰብያ በማድረግ እና የአህጉሪቱ ሀገራት ነጻነታቸው የተቀዳጁበት 200ኛ ዓመት ምክንያትም ነው ።

ቅዱስ ጰጥሮስ ካተድራል ለዚሁ አጋጣሚ የንጽህት ድንግል ማርያም ዘ ጓዳሉፐ ምስል በመንበረ ታቦት ተቀምጦ እና በላቲን አመሪካ ሀገራት ሰንደቅ ዓላማዎች አሽብርቃ በከፊልም የላቲን አመሪካ ሀገራት መንፈሳውያን መዝሙሮች መደመጣቸው ተመልክተዋል።

ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ 16ኛ በዚሁ ትናንትና ከቀትር በኃላ በቅዱስ ጰጥሮስ ባዚሊካ ስለ ላቲን አመሪካ በተካሄደው እና በመሩት ሥርዓተ ቅዳሴ ፊታችን ዓመት 2012 እኤአ ከትንሳኤ በዓል መድኅን ክርስቶስ በፊት በሁለት የላቲን አመሪካ ሀገራት ይኸውም በመክሲኮ እና በኩባ ሐዋርያዊ ዑደት እንደሚያከናውኑ ይፋ ማድረጋቸው የቫቲካን የዜና ምንጩ አስገንዝበዋል።

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ 16ኛ ንጽህት ድንግል ማርያም ዘ ጓዳሉፐ ወደ መለኮታዊ ልጅዋ መድህን ክርስቶስ እንደምትመራን እና እሱ ማለት ኢየሱስ ክርስቶስ የሰው ልጅ ሁሉ ክብር መሠረት የደስታ እና የተስፋ ምንጭ መሆኑ በዚሁ ሥርዓተ ቅዳሴ ባሰሙት ስብከት ላይ ማብራራታቸው የዜና ምንጩ አክሎ አመልክተዋል።

ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ከሥርዓተ ቅዳሴ በኃላ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ሰማያዊት ንጽህት ድንግል ማርያም ወላዲተ አምላክ ዘ ጓዳሉፐ የላቲን አመሪካ እና ካራይቢ ሀገራት ህዝቦች የተሻለ እና ብሩህ መጻኢ እንዲኖራቸውታማልድልን ዘንድ እንጸልይ በማለት ጸሎተ ማርያምን መምራታቸው ተገልጠዋል። ይህ በዚህ እናዳለ ሆኖ ቅድስነታቸው በመክሲኮ እና ኩባ ሀገራት ሐዋርያዊ ዑደት እንደሚያደርጉ ይፋ ካደረጉት በኃላ የሁለቱ የላቲን አመሪካ ሀገራት ጳጳሳትን እና ምእመናን የተሰማቸውን ደስታ መግለጣቸው ከመክሲኮ ክተማ እና ከሃቫና የደረሱን ዜናዎች አስታውቀዋል።

ከመክሲኮ ከተማ የደረሰን ዜና እንዳንመለከተው ፡ በመክሲኮ ከተማ ውስጥ በሚገኘው በንጽህት ቅድስት ድንግልማርያም ዘ ጓዳሉፐ ካተድራል የተገኙ ምእምናን የቅድስነታቸው መክሲኮ ሐዋርያዊ ጉብኝት እንድተነገረ የተሰማቸውን ደስታ በደስታ በእልልታ እና ጨብጨባ ተቀብለውታል።

በዚሁ በተያዝነው ወርሃ ታህሳስ መባቻ እንደ ጎርጎርዮስ አቁጣጣር ስድስት ሚልዮን የላቲን አመሪካ ሀገራት ምእመናን መክሲኮ ላይ የሚገኘው የጓዳሉፐ ማርያም ካተድራል መሳለማቸው ዜናው ለጥቆ አመልክተዋል።

በሌላ በኩል የኩባ ረኪበ ጳጳሳት የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ 16ና ሐዋርያዊ ዑደት በደስታ በተስፋ እና ጉጉት እየጠበቁት መሆናቸው የረኪበ ጳጳሳቱ ቃል አቀባይ ብጹዕ አቡነ ኾሰ ፈሊክስ ፐረዝ መግለጣቸው ከርእሰ ከተማ ከሃቫና ተመልክተዋል ።

የቅድስነታቸው ኩባ ሐዋርያዊ ጉብኝት በዚሁ በተያዝነው ዓመት ሀገሪቱ ውስጥ ከ400 ዓመታት በፊት የተገኘው የርህርህት ቅድስት ድንግል ማርያም ቅርጽ በሚታወስበት ዓመት በመግጠሙ ተጨማሪ ደስታ እንደሚሰጥ ብጹዕ አቡነ ኾሰ ፈልክስ ፐረዝ በተጨማሪ መግለጣቸው ይህ ከሃቫና የደረሰን ዜና ዘግበዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.