2011-12-12 13:25:44

የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት የመልአከ እግዚአብሔር ጉባኤ አስተምህሮ (እ.ኤ.አ. 11/12/2011)
እውነተኛው ሐሴት ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጋር መገናኘት ነው


ትላትና እሁድ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በብዙ ሺሕ የሚቆጠሩት ከውስጥ እና ከውጭ አገር የተወጣጡ ምእመናን በአጸደ ቅዱስ ጴጥሮስ በተገኙበት እኩለ ቀን ከሐዋርያዊ መንበራቸው ካለው መስኮት ሆነው፣ ጸሎት መልእከ እግዚአብሔር ከማሳረጋቸው ቀደም በማድረግ ጥድፍያ እና ሽርጉድ በተሞላው እለታዊ ኑሮአችን RealAudioMP3 ማስታወስ የሚገባን እውነተኛው ሐሴት ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጋር መገናኘት ማለት መሆኑ የሚያሳስብ አመለካከት ማእከል በማረድረግ ባቀረቡት ሥልጣናዊ አስተምህሮ ዕለቱ ሦስተኛው የምጽአት እሁድ በላቲን ሥርዓት የሐሴት ሰንበት ተብሎ የሚጠራ መሆኑ በመግለጥ፣ በዓለ ልደት ምክንያት በማድረግ በሚነዙት የገበያ ማስታወቂያዎች ሳንታለል፣ ሀሳባችንን ሳንበትን የበዓለ ልደት መሠረታዊ ትርጉሙን ዳግም መቀዳጀት ይኖርብናል። የሐሴት ሰንበት ሁላችንን እውነተኛውን ደስታ እንፈልግ ዘንድ የሚያሳስበ ብቻ ሳይሆን፣ እውነተኛው ደስታችን ማን መሆኑ የሚያመለክተን ጭምር መሆኑ ገልጠው፣ ምንም’ኳ ካለው የኤኮኖሚ እና የቁጠባው ቀውስ አንጻር፣ የገበያ እና የንግድ ዓለም የሚያከናውኑት የማስተዋወቅ ተግባራቸው የቀነሰ ቢመስል ቅሉ በዚህ ለበዓለ ልደት በምንዘጋጅበት ወቅት በሚያሰራጩት የማስተዋወቅ ተግባራቸው ሳንታለል ለነገሮች ሁሉ ወደ ክርስቶስ ባቀናው እይታችን አማካኝነት በመመልከት እና ትርጉም በመስጠት የተስተካከለ ክርስትያናዊ ሕይወት እንኖር ዘንድ አደራ ብለዋል።
እውነተኛው ደስታ ከአንድ ጥልቅ ከሆነ ነገር ጋር የተሳሰረ ነው። ሩጫ እና ጥድፍያ በተሞላው ዕለታዊ ኑሮአችን ውስጥ እንድንረጋጋ የሚያግዘን ዕረፍት ጊዜ መሻት ወሳኝ ነው። ሆኖም ግን እውነተኛው ደስታችን ከእግዚአብሔር ጋር የሚጸናው ግኑኝነት ነው። በሕይወቱ ከክርስቶስ ጋር የተገናኘ እና ክርስቶስን ያገኘ በማንም የማይነጠቀው በጥልቀ ልቡ የመንፈስ እርጋታ እና እውነተኛው ደስታ ያጣጥማል ይኖራልም ብለዋል።
እውነተኛው ደስታ ተራ የተለመደ ሁኔታ ወይንም በግል ጥረት የሚደረስ ሳይሆን፣ ጸጋ ነው። ይኽ ማለት ደግሞ በእኛ ሕይወት ውስጥ ቦታ ልንሰጠው የሚገባን ሕይወታችንን የሚመራው ቅዱስ መንፈስ በማስተናገድ ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ከሚኖረን ኅያው ግኑኝነት የሚገኝ ነው። ቅዱስ አጎስጢኖስ እንደሚለውም የሰው ልጅ ልብ የተሸበረ ነው። በእግዚአብሔር እስካላረፈ ድረስ የመንፈስ እርጋታ እና ሰላም አያገኝም የሚለውን እውነት አስታውሰዋል።
አክለውም በየዓመቱ የሚሰጠው እናቴ ብፅዕት ተረዛ ዘካልኩታ የተሰየመው ሽልማት ዘንድሮ እ.ኤ.አ. መጋቢት 14 ቀን 2008 ዓ.ም. ከዚህ ዓለም በሞት ለተለዩት የአፍቅሮተ ዘቤት ካቶሊካዊ እንቅስቃሴ መሥራች ኪያራ ሉቢክ ተዘክሮ መሰጠቱና እንዲሁም ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት እና ፈቃድ ውሳኔ በተባበሩት መንግሥታ ድርጅት የተደነገገበት የተዘክሮ ዓመት መሆኑም በማስታወስ ከሁሉም በላይ የላቀው እና ቀዳሚው የሰብአዊ መብት እና ፈቃድ መሠረት የሕይወት መብት እና ክብር መሆኑ አስገንዝበዋል።
እዛው የተገኙትን የሕፃን ኢየሱስ የተቀረጸ ምስል ለያዙት ሁሉም ሕፃናት ምስሉን እና ሕፃናቱንም ባርከው እኔ በጸሎቴ እንደማስባችሁ ሁሉ እናንተም በጸሎታችሁ አስቡኝ በማለት ጸሎት መልእከ እግዚአብሔር አሳርገው ለሁሉም መልካም የምጽአት ዘመን እና በዓለ ልደት ተመኝተው ሓዋርያዊ ቡራኬ ሰጥተው አሰናብተዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.