2011-12-12 13:31:39

አፍሪካ እና መገናኛ ብዙኃን


የአፍሪቃ ልኡካነ ወንጌል ማኅበር አፍሪቃ በአፍሪቃ መሠረት የሚያስተዋውቅ ስለ አፍሪቃ ለማወቅ እና አፍሪቃን ለማስተዋወቅ ዓልሞ የመሠረተው አፍሪካ የተሰየመው RealAudioMP3 መጽሔት 90 ዓመተ ጅማሬው መሠረት በማድረግ “አፍሪካ እና መገናኛ ብዙኃን” በሚል ርእስ ሥር የተለያዩ ዓለም አቀፍ ጋዜጠኞች ያሳተፈ የሁለት ቀናት ዓወደ ጥናት እ.ኤ.አ. ከታህሳስ 9 ቀን እስከ ታህሳስ 10 ቀን 2011 ዓ.ም. በኢጣሊያ በርጋሞ ክፍለ ሃገር በምትገኘው የትረቪሊዮ ከተማ የመጽሔቱ ዋና መሥሪያ ቤት የጉባኤ አዳራሽ መከናወኑ የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ሲልቪያ ኮች አስታወቁ።
በዓለም አቀፍ ደረጃ በአፍሪቃ እና ስለ አፍሪቃ የሚቀርበው በጅምላዊ ቅድመ ፍርድ ላይ የጸና የማይለወጥ በበለጸጉት አገሮች ቅቡል የሆነው አሉታዊ የደፈናው አነጋገር እና አገላለጥ ጨርሶ መወገድ እንዳለበት ያሠመረው ዓውደ ጥናት፣ አፍሪቃ የሰብአዊነት እና የሰው ዘር ቀመጥ የሕይወት ትርታ የሚደመጥባት መሆኑ ብዙውን ጊዜ በልኡካነ ወንጌል እና በተለያዩ የካቶሊክ ቤት ክርስትያን የግብረ ሠናይ ማኅበራት እና ሌሎች የሰብአዊ ማኅበራት አማካኝነት የሚጎላው እውነት በዓለም አቀፍ ደረጃ ሊስተጋባ ይገባዋል። የምዕራብ ዓለም የመገናኛ ብዙኃን ስለዚህ አፍሪቃን በትክክል የሚገልጣት ባህል መሠረት በማድረግ የተለያዩ ዜናዎች ያቀርቡ ዘንድ ጥሪ የተላለፈበት መሆኑ ልእክት ጋዜጠኛ ኮች አስታውቀው፣ አፍሪቃን በአሉታዊ ጎኗ ብቻ ሳይሆን በአወንታዊ ጎንዋ ጭምር ዓለም አቀፍ እውቅና ታግኝ ዘንድ የሁሉም የመገናኛ ብዙኃን ኃላፊነት ነው የሚል ሓሳብ ማእከል ያደረገ ሰፊ ውይይት መካሄዱ ገልጠዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.