2011-12-09 16:22:06

የኤውሮጳ ሕብረት መሪዎች ጉባኤ በብሩሰል


የኤውሮጳ ሕብረት ሀገራት መሪዎች ብሩሰል ላይ ተሰብስበው በወቅቱ ሕብረቱ የገጠመውን ፊናንሳዊ እና ኤኮኖምያዊ ከባድ ቀውስ ለመታደግ በመምከር ላይ እንደሚገኙ ይታወቃል።

የኤውሮጳ ሕብረት ሃያ ሰባት ሀራት አባል አቀፍ መሆኑ እና በጋራ ገንዘብ ዩሮ የታቀፉ አስራ ሰባት ብቻ መሆናቸው የሚታወስ ነው። ፡

በዚሁ ብሩሰል ላይ የሚያካሄዱት ስብሰባ በሕብረቱ ስምምነት ላይ ተሐድሶ በማድረግ ጥብቅ የገንዘብ አያያዝ ፖሊሲ ለመድረግ በሚቻልበት ሁኔታ በመምከር ላይ እንደሆኑ ከብሩሰል የሚደርሱ ዜናዎች አስታውቀዋል።

በነዚህ ዜናዎች ዘገባ መሠረት የኤውሮጳ ሕብረት መሪዎች በዚሁ የብሩሰል የሁለት ቀናት ስብሰባ የሕብረቱ የጋራ ገንዘብ ዩሮ ዋጋ ቢስ ሆኖ እንዳይቀር ለማዳኑ የሚቻለቻውን ሁሉ ለማደረግ ይጥራሉ ።

ባለፈው ሰኞ የዩሮ ህላዌ እውን እንደሚሆን በጋራ መግልጫ የሰጡ የጀርመን መራሂተ መንግስት ኤንገላ ሜርክል እና የፈረንሳ መንግስት መሪ ፕረሲዳንት ኒኮላስ ሳርኮሲ አሁን መጠራጠር መጀመራቸው ተያይዞ ተዘገበዋል።

ፈጣን እድገት ማሳየታቸው የሚታወቁት የምዕራብ ኤውሮጳ ሀገራት መንግስታት የጋራ ገንዘባቸው ካላዳኑ የጋራ ፖሊቲካቸው መክሸፉ ግልጽ እንደሚሆን የሕብረቱ የፖሊቲካ ጠበብት ያመልከታሉ ።

በኤውሮጳ ሕብረት ጉዳይ የፈረንሳ መንግስት ዋና ተጠሪ መስየ ጂን ለኦነት እንዳመለከቱት ፡ ዩሮ ይፈነዳል ሕብረቱ ይበታተናል ይሄም ለመላ ዓለም አስጊ ሁኔታ ላይ ይጥላል ።

በርካታ የኤውሮጳ ሕብረት ሀገራት መንግስታት ሰማይ ጠቀስ ዕዳ እንዳላቸው እና ይህ የሕብረቱ የጋራ ኤውሮ ለመታደግ አስቸጋሪ እየሆነ መምጣቱ የማይዘነጋ ነው።

በዚሁ ዕዳ የተጨነቁ የሕብረት መንግስታት ግሪክ ጣልያን ፖርትጋል ሰሜን ረፓብሊክ አይርላንድ እስጳኛ ይገኙባቸዋል።

መንግስታቱ ካላቸው የዕዳ ጫና ለማላቀቅ ሕብረቱ ገንዘብ ካማውጣት እንዲቆጠብ የፋይናንስ በፋይናንስ ይዘታቸው የተሻሉ መሆናቸው የሚነገርላቸው ጀርመን አውስትርያ ኔዘርላንድስ እና ፊንላንድ እያሳሰሰቡ እንደሚገኙም ተነግረዋል።

በየኤውሮጳ ሕብረት የፋናንስ ቀውስ በእጅጉ የሰጉ የዩናይትድ ስቴትስ መንግስት መሪ ፕረሲዳንት ባራክ ኦባማ የጀርመን መንግስት ቻንስለር ኤንገላ መርክል ስልክ ደውለው ማነጋገራቸው ከብርሊን የመጣ ዜና ዘግበዋል።

የፋይናንስ ሚኒስትራቸው ቲሞቲ ጋይትነር ወደ ኤውሮጳ መላካቸው እና ሚኒስትሩ ከሕብረቱ መንግስታት መሪዎች ጋር እየተገናኙ መሆናቸው ይታወቃል።

ቲሞቲ ጋይትነር ትናንትና ጥዋት እዚህ ጣልያን ውስጥ ከአዲሱ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ማርዮ ሞንቲ ጋር ተገናኝተው ሐሳብ ለሐሳብ ተለዋውጠዋል።

ይህ በዚህ እንዳለ ሆኖ ፡ በኢንዱስትሪ የበለጸጉ የኤውሮጳ ሀገራት የገጠማቸው አስፈሪ እና ከባድ የኤኮኖሚ ቀውሱ የባሕር ማዶ በማደግ ላይ በሚገኙ ሀገራት ተጽዕኖ እያሳደረ መሆኑ የኤኮኖሚ ጠበብቶች ያመለክታሉ ።

በወቅቱ በኤኮኖሚ እና ፋይናንስ ቀውስ በመሰቃየት ላይ የሚገኙ የኤውሮጳ ሀገራት ለድሃ ሀገራት ለእድገት ትብብር ይሰጡት የነበረ ገንዘብ ለመሰረዝ እተደገደዱ መሆናቸው የኤኮኖሚ ኤክስፐርቶች ይገልጻሉ ።

ለጋሽ ሀገራትም እንዲሁ እጃቸው ከመዘራጋት እንዲቆጠቡ ግድ ይሆንባቸዋል ተብሎም እየተነገረ ነው ።








All the contents on this site are copyrighted ©.