2011-12-05 14:44:39

“ትንቢተ ኢሳያስ እና ዘመነ ምጽአት”።


የኢጣሊያ የቲዮሊጊያ ማኅበር አባላት የሥነ ቲዮሎጊያ ሊቃውንት ሰረና ኖቸቲ እና ናዲያ ቶስኪ በጋራ ፦ የፍትሕ እና የሰላም ተስፋ” በሚል ርእስ ሥር የደረሱት አዲስ መጽሐፍ ለንባብ መብቃቱ ሲገለጥ፣ በዚህ የእግዚአብሔር እቅድ መረጋገጥ ላይ የሚጸና ተስፋ በማብራራት ቀዳሜ ሥፍራ የያዘው የነቢይ ኢሳያስ መጽሐፍ ኢፍትሐዊነት እና ለእግዚአብሔር እቅድ ክህደት በሚታይበት ዓለም፣ የዘመነ ምጽአት ሊጡርጊያ እይታችን RealAudioMP3 ወደ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ምጽአት የምንኖርበት ወቅት ሊሆን እንደሚችል የሚያብራራ መጽሐፍ መሆኑ የቲዮሎጊያ ሊቅ የኢጣሊያ የቲዮሎጊያ ማኅበር ምክትል ሊቀ መንበር የዚህ መጽሐፍ ደራሲ አንዷ ሰረና ኖቸቲ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ አብራርተው፣ ዘመነ ምጽአት የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቀዳሚው ምጽአት ተዘክሮ የምናከናወንበት ወቅት ብቻ ሳይሆን፣ እይታችን ወደ ዳግማይ ምጽአት እናቀና ዘንድ የሚያሳስብ ወቅት ጭምር ነው። ይኽ ደግሞ ነቢይ ኢሳያስ በመጽሐፉ የሚያመለክተው ምጽአት ያለው ሁለት ገጽታውን የሚያበክር ሲሆን፣ የቤተ ክርስትያን እና የክርስትያን ሕይወት ሥነ ፍጻሜ አድማስ የሚመራ ነው። ስለዚህ መጽሐፉ የክስ እና የተስፋ፣ እግዚአብሔር አብ ታሪክን እየመራ መሆኑ የሚያስገነዝብ ነው ካሉ በኋላ አያይዘውም ሰብአዊ ታሪክ በተፈጸመ ጊዜ እርሱ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የመጀመሪያ ምጽአት እና የመንግሥቱ የእግዚአብሔር መንግሥት ግልጸት ፍጻሜ የሆነ እና ገና የሚሆን ተስፋ የእግዚአብሔር ቃል በገባው ቃል ኪዳን ላይ የሚያጸና መሆኑ የሚተነትን ነው። ስለዚህ ያለው ጊዜ ኢፍትሐዊነት እና እግዚአብሔርን መካድ፣ አመጽ እና ውጥረት፣ ባይተዋርነት የሚያስፋፋው በብዙ ሚሊዮን የሚገመተው ሕዝብ ሕይወት ለአደጋ የሚያጋልጠው የተጨባጩ ታሪክ ልምድ የሚያብራራ ብቻ ሳይሆን፣ ፍጻሜው የሚያመለክት ነው ብለዋል።
በሌላ መልኩ ነቢይ ኢሳያስ ዘመነ ምጽአት እኛ የሚለው ማኅበራዊነት የሚያስተምረን የሕዝብ ወገን ማለት የሕዝበ እግዚአብሔር ወገን መሆናችን የዚህ ሕዝበ እግዚአብሔር ኃላፊነት ተካፋዮች፣ የእምነት ግላዊ እና ማኅበራዊ ገጽታውን የሚያጎላ፣ አስተሳሰብን እና ምርጫችንን የምንለውጥበት ጊዜ፣ የለውጥ ጊዜ መሆኑ ያስተምረናል፣ መለወጥ ፍትህ ሰላም ያጣመረ ተጨባጭ ምርጫ በማድረግ ፍትህ እና ሰላም “ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ” ለማረጋገጥ የተጠራን መሆናችን የሚያስገነዝብ መሆኑ የሚብራራ መጽሓፍ ነው በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.