2011-12-05 14:46:26

“ር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ” የሰላም ሽልማት


በካላብሪያ የሚገኘው አናሲላኦስ የተሰየመው የሥነ ባህል ማኅበር በየዓመቱ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳ ብፁዕ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ የተሰየመው የሚስጠው የሰላም RealAudioMP3 ሽልማት የ 2011 ዓ.ም. ለቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ ብፁዕ ካርዲናል ታርቺዚዮ በርቶነ መስጠቱ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።
ብፁዕ ካርዲናል ታርቺዚዮ በርቶነ የሰላም ሽልማቱን በተረከቡበት እለት ባሰሙት ንግግር፣ የር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ እ.ኤ.አ. መጋቢት 4 ቀን 1979 ዓ.ም. “ረደምፕቶሪስ ሆሚኒስ-የሰው መድኅን” በሚል ርእስ ሥር የደረሱት ዓዋዲት መልእክት በመጥቀስ፣ በምንኖርበት ዓለም በሕዝቦች መካከል የተሟል ሰላም ለማረጋገጥ የሰው ልጅ ሰብአዊ መብት እና ፈቃድ ማክበር ዋነኛ መሠረት መሆኑ ያመለከቱት መርህ በማስታወስ፣ ከዚህ ጋር በማያያዝም ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ የተለያዩ ሁሉም ሃይማኖቶች የጋራ አካፋይ የሆነው የሰው ልጅ ኵላዊ እሴት ማክበር የሚለው ሐሳብ የሰላም እውነተኛ መሠረት መሆኑ የሚያስገነዝብ መሆኑ በተለያየ ወቅት በመደጋገም የሰጡትን ትምህርት አስታውሰው፣ ማኅበረ ክርስትያን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ማእከል በማድረግ የሚለያየውን ግንብ በማግለል ኵላዊ ሰላም እንዲያረጋግጥ የተጠራ ነው እንዳሉ ሲር የዜና አገልግሎ ሲያመለክት ብፁዕነታቸውም በዚህ አጋጣሚ ከረጂዮ ካላብሪያና ቦቫ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ቪቶሪዮ ሞንደሎ ከክፍለ የከሰበካ ካህናት ገዳማውያን እና ምእመናን ጋር መገናኘታቸው ሲር የዜና አገልግሎት አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.