2011-12-05 14:41:13

የቅድስት መንበር ርእሰ ዓንቀጽ፦ ዘመነ ምጽአት


ሁሌ እንደተለመደው የቅድስት መንበር የዜና ማኅተም ክፍል ተጠሪ የቫቲካን ረዲዮ ዋና አስተዳዳሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ በሳምንት ማገባደጃ የሚያቀርቡት የቅድስት መንበር ርእሰ ዓንቀጽ በመቀጠል ትላትና ዘመነ ምጽአት “የሕፃኑ ዕጣ ፈንታ ምን ይሆን” በሚል ርእስ ሥር ዘመነ ምጽአት ማእከል በማድረግ አቅርበው፣ RealAudioMP3 ወደ በዓለ ልደት ዘእግዚእነ የሚያሸጋግረው ዘመነ ምጽዓት፣ የማዘጋጃ ወቅት መሆኑ በማብራራት፣ ለየት ባለ መልኩም ስለ ሁሉም የዓለም ሕፃናት፣ በስቃይ በአሳዛኝ ሁኔታ እና የተለያዩ አመጽ ሰለባ የሚሆኑት ሕፃናት እና ተስፋቸው ቆም ተብሎ የሚስተነተንበት ወቅት ነው ብለዋል።
“ይህ ሕፃን ምን ሊሆን ይሆን?” ሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ 1 ቁ. 66 ያለውን ወንጌላዊ ጥያቄ የዮሐንስ መጥምቅ እንደ ተወለደ የኤልሳቤጥ እና የዘካርያስ ጎረቤቶች እና ዘመዶች ያቀረቡት ጥያቄ ሲሆን፣ ይህ እያንዳንዳችን ወደ ዓለም የመጣው ሕፃን በተመለከተ የምናቀርበው ተስፋ እና ሥጋት አዘል ጥያቄ ነው። ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ እ.ኤ.አ. ከህዳር 18 ቀን እስከ ህዳር 20 ቀን 2011 ዓ.ም. በበኒን ባካሄዱት 22ኛው ዓለም አቀፍ ሐዋርያዊ ጉብኝት ወቅት ሁሉን የማረከ እና ተመሳሳይ ጥያቄ ያነቃቃው ከሕፃናት ጋር ያካሄዱት ግኑኝነት በሕፃናቱ ተከበው እና እጅ ለእጅ ተያይዘው አብረው ሲራመዱ የታየው ሁኔታ ለገዛ እራሱ ያንን ወንጌላዊ ጥያቄ ዳግም የኖረ ግኑኝነት ነበር ብለዋል።
ቅዱስ አባታችን ለአፍሪቃ እና በአፍሪቃ ለምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ያስረከቡት “አፍሪካ ሙኑስ-የአፍሪቃ ቃለ መሓላ” የተሰየመው ሐዋርያዊ ምዕዳን ዘንድ የሕፃናት ጉዳይ የሚያትት ገና ከመወለዳቸው በፊት የሚገደሉት ሕፃናት፣ በሕፃናት ላይ የሚሰነዘረው ተቀባይነት የሌለው ኢሰብአዊ ተግባር፣ በሰው አነጋገር ያልተፈለጉ እየተባሉ የሚቀጩ ወላጅ አልባ ሆነው የሚቀሩ፣ ሕፃናት ወታደሮች፣ ለእስር እንዲሁም ገና በጨቅላነት እድሜያቸው ለሥራ ዓለም የሚዳረጉት፣ አካለ ስንኩላን ሆነው በመወለዳቸው ምክንያት ለሥቃይ ተላልፈው የሚሰጡት በሁሉም የሚረሱት እርግማን ተብለው የሚታሰቡት፣ የሚሸጡና የሚለወጡ፣ ለተለያዩ ክብር ሰራዥ አዲስ ባርነት ለሆነው ለግብረ ሥጋ አመጽ የሚዳረጉት፣ በጠቅላላ አለ ምንም ብሩህ መጻኢ የሚቀሩትን ሁሉ በርእሰ አቀንቀጹ በመጥቀስ፣ ለእነዚህ ሁሉ ቤተ ክርስትያን ተቀዳሚው ሥፍራ እንደምትሰጥ፣ ለእነርሱ ክብር አበክራ እንደምትንቀሳቀስ፣ በመላ አለም 1250 የጤና ጥበቃ እና የግብረ ሠናይ የቤተ ክርስትያን ተቋሞች ሌሎች 20 ሺህ ለሕፃናት ጉዳይ አገልግሎት የሚሰጡ የተለያዩ የቤተ ክርስትያን ማኅበራት፣ ጎዳና ተዳዳሪ ሕፃናትን ከወደቁበተ አደጋ የሚያላቁ በተለያዩ አደንዛዥ እፅዋት የተለከፉትን ከወደቁበት አሰቃቂው እና ካስከፊው ድኽነት ጫንቃ ሥር ለማላቀቅ ዓልመው አገልግሎት የሚሰጡ የቤተ ክርስትያን የተለያዩ የግብረ ሰናይ ማኅበራት ኅላዌ ይመሰክረዋል ብለዋል።
በቅርቡ የሕፃናት ጥበቃ ጉዳይ በመከረው ዓለም አቀፍ ጉባኤ በመገኘት ንግግር ያደረጉት አንቀጸ ሃይማኖት ተንከባካቢ ቅዱስ ማኅበር ሕግና ፍትህ ለሚያንቃቃው ተልእኮ ተጠሪ ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ብፁዕ አቡነ ቻርለስ ሲክሉን በሕፃናት ላይ የሚፈጸመው የግብረ ሥጋ ዓመጽ የሚመለከት ያቀርቡት ቆራጥ እና ግልጽ የመቅጫ ሕግ ጉባኤው በምልአት ጭብጨባን በማቅረብ በማድነቅ የተቀበለውን ሰነድ አባ ሎምባርዲ በማስታወስ፣ ቤተ ክርስትያን ሕጻናትን ለመንከባከብ እና ለመጠበቅ በካህናት በገዳማት በማኅበሮችዋ አማካኝነት ለሰው ዘር የምትሰጠው አገልግሎት የሚመሰክር መሆኑ ገልጠው፣ በዚህ በዘመነ ምጽአት እና በበዓለ ልደት፣ ሁሉም የሰው ዘር የሕፃናት መብት እና ፈቃድ ጥበቃ ጉዳይ ቅድሚያ ሊሰጥበት የሚገባ የማያወላውል ተልእኮ መሆኑ የሚመሰከርበት ወቅት ነው በማለት ርእሰ አንቀጹን አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.