2011-12-02 15:22:47

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. ለጳጳሳዊ የባህል ተቋም “ጥንታዊው የሥነ ሰማዕት ጥናት አብነት ያለው ክብር ኅያው የሚያደርግ ነው”።


“ምስክርነት እና መስካርያን፦ ሰማዕታት እና የእምነት ባለ ድል ታጋይ” በሚል ርእስ ሥር የተመራ የባህል ጉዳይ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት እንዲሁም የቤተ ክርስትያን የባህል ተቋሞች አቀናጅ ምክር ቤት በመተባበር በጋራ ያዘጋጁት አወደ ጥናት እ.ኤ.አ. ህዳር 30 ቀን 2011 ዓ.ም. በር.ሊ.ጳ. ቅዱስ ፕዮስ አስረኛ የጉባኤ አዳራሽ መካሄዱ ሲገለጥ፣ RealAudioMP3 ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16 ለተጋባእያኑ የቀደምት ሰማዕታት ገድል በተመለከተ የሚደረገው የሥነ ሰማዕት ጥናት አብነት ያለው ክብር ኅያው የሚያደርግ ነው የሚል ሃሳብ ማእክል በማድረግ ያስተላለፉት መልእክት፣ በአውደ ጥናቱ ፍጻሜ በቅድስት መንበር ዋና ጸሓፊ ብፁዕ ካርዲናል ታርቺዚዮ በርቶኔ መነበቡ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።
ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የቀደምት የእምነት ሰማዕታት ታሪክ የሚያረጋገጥ የሚመሰክር ቅርስ ከዘመን ወደ ዘመን እየተሸጋገረ የሚወራረሰው ሃብት እምነት ተጨባጭ የሚያደርግ ይህ ቅዱስ ሃብት የእምነት ቅዱሳን ወይንም ብፁዓን ሰማዕታት ምስክርነት የሚያጎላ መሆኑ ባስተላለፉት መልእክት እንዳብራሩ ሲገለጥ፣ ይኸንን 16ኛው ጳጳሳዊ የባህል ተቋሞች ውሎ በንግግር የከፈቱት የባህል ጉዳይ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ጃንፍራንኮ ራቫዚ መሆናቸውም ሲገለጥ። ቅዱስ አባታችን ባስተላለፉት መልእክት የክርስትና እምነት ጸጋ ከመሆኑም ባሻገር የዚህ ጸጋ ተጨባጭ እርሱም የክርስትና ታሪክ ማእከል ሮማ ቅድስት መሬት እና ሌሎች የክርስትና የሥነ ቅርስ ሥፍራዎች ተጨባጭ ምስክርነት መሆኑ በጠቅላላ ክርስትና እምነት የተኖረበት ጥንታዊው ሥፍራ የክርስትና ሥነ ጥንተ ታሪክ ለአሁኑ ክርስትያን ቀልብ ለኅሊና እና ለአእምሮ ችሎታ ጥያቄ መሆኑ የሚያረጋገጥ ነው።
ቅዱስ አባታችን ባስተላለፉት መልእክት አክለውም ጨርሶ የማይጠፋው ተጨባጭ የእምነት ምስክርነት ጥለው ያለፉት ቀደምት ሰማዕታትን የእምነት ባለ ድል ታጋይ በሚለው ሐሳብ በመግለጥ፣ በእነዚህ ባለፉት ቅዱሳን እና ብፁዓን የእምነት ሰማዕታት ምስክርነት ዛሬ እንደ ትላትንቱ፣ በሰው ልጅ ልብ የሚናገር ወንጌል እና አማንያን በቃል እና በሕይወት የሰጡት ኅያው ምስክርነት ያቀርባል፣ የማያወላውል ላድር ባይነት ዝንባሌ እምቢ የሚል ነጻ እምነትን ከሚገበያይ ፈተና በማራቅ፣ ዋናው እና የመጀመሪያ እግዚአብሔር ወደ ሰው ልጅ ሰው ሆኖ መምጣቱን በሰው እና በሰብአዊው ታሪክ መግባቱን የሚያረጋግጥልን የታመነ እምነት ምስክር የሆነው የተሰቀለው ክርስቶስ በመኖር የእርሱ የፍጹም ፍቅር እቅድ መኖር እንደሚቻል የሚያረጋገጥልን ኅያው ምስክርነት ነው።
ክርስትያን ሁሉ ታማኝ የእምነት መስካሪ ሆኖ እንዲገኝ እንዲኖር መጠራቱንም በዚህ አጋጣሚ ቅዱስነታቸው በማሳሰብ፣ ይኽ ደግሞ እንደ የእምነት ሰማዕታት ፍቱን ግልጽ እና የተወኃደ ታማኝ እና በሙሉ ስሜት ከሚያፈቀረው ፍቅር ጋር የሚሰዋ ፍቅር ያጣመረ ባለ እንጀራህን እንደ ገዛ እራስህ አፍቅር የሚለውን ጥሪ የሚኖር ባጠቃላይ አለ ምንም ቅድም ሁኔታ በሙላት ያፈቀረን ክርስቶስን የሚኖር ተጨባጭ ምስክርነት የሚጠይቅ ምርጫ ነው እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።







All the contents on this site are copyrighted ©.