2011-12-01 15:50:06

ፊታችን ታሕሳስ ወር እንደ ጎርግርዮስ አቁጣጠር :


ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ 16ኛ እኤአ ነገ በሚጅመረው ወርሃ ታሕሳስ የቅዱስ ወንጌል እውነተኛ ስለሆኑ ሕጽናት እና ወጣቶች እንደጸለይ መጠየቃቸው ቅድስት መንበር ላይ የወጣ መግለጫ አስታውቀዋል።
ብዙ ግዜ የሕጻናት እና የወጣቶች ክብር እና መብት ሲጣስ እንደሚታይ እና ይህ አሳዛኝ ተግባር እንዲገታ በዚሁ ወርሃ ሐምለ ላይ ሥርዓተ ጸሎት እንዲደረግ በነዲክቶስ 16ኛ ማሳሰባቸው መግለጫው አስገንዝበዋል።
ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ልደተ እግዚእነ ወመድኀኒነ እየተቃረበ በሚሄድበት በአሁኑ ግዜ ስለ ሕጻናት እንዲጸለይ ጠይቅዋል በማለት ይህ በቅድስት መነብር የወጣ መግለጫ አመልክተዋል።
የቅዱስ ወንጌል ልዑካን ጳጳሳዊ ተግባር መጽሔቶች አውራ ሐላፊ አባ ጁልዮ አልባነሰ የቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ጥያቄ ሲያስተንትኑ እንዳመለከቱት ፡ በዚሁ ዛሬ የሚገባደደው ወርሃ ጥቅምት የቅዱስ ወንጌል ብሥራት እና ምስክርነት ዕለት መከበሩ አስታውሰው ፡ ይህ የእግዚአብሔር ምስክሮች ተግባር መሆኑ ገልጠዋል።
በአባ ጁልዮ አልባነሰ አመለካከት በነዲክቶስ 16ኛ ወርሃ ታሕሳስ ስለ ሕጻናት እና ወጣቶች እንዲጸለይ የጠየቁበት ምክንያት እነሱ የሚመጣው ትውልድ ባለቤት በመሆናቸው ነው ።
ከወቅቱ የተሻለ ዓለም ከተፈለገ የሕጻናት እና የወጣቶች ክብር እና መብት አስጠብቆ በነሱ ላይ ኢንቨስት ማድረግ የግድ ይላል ያሉት አባ ጁልዮ አልባነሰ የትምህርት ተቋሞች ለነሱ ሁለገባዊ እንክብካቤ በመስጠት ረገድ ከፍተኛ ሚና እንዲጨውቱ አሳስበዋል።
በቫቲካን የሕጻናት ጳጳሳዊ ተግባር ለሕጻናት ሁለ ገባዊ እንክብካቤ በመስጠት ላይ እንደሚገኝና በግብረ ገብ በኩል የሚሰጣቸው ትምህርት ለሰላማዊ እና ፍትሐዊ ሕይወት በመሻት ረገድ እዥግ እንደሚጠቅማቸው አባ ጁልዮ አልባነሰ ገልጠዋል።
አባ አልባነሰ በዋነኛነት የሚኖሩት በምስርቃዊ አፍሪቃ በኬንያ ሲሆን ፡ የአፍሪቃ ሕጻናት ትኩረት ሰጥተው ሲገልጡ ፡ በበለጸጉ ሀገራት ከሚገኙ ሕፃናት የተለዩ መሆናቸው እና ከሁሉም በላይ ለሕጻን የሚያስፈልገው ሁሉ ባይኖራቸውም ፈገግታቸው እና በከቤተ ሰቦቻቸው ጋር ያላቸውን ጥብቅ የፍቅር ትስስር ማራኪ ነው ማለታቸው ተዘግበዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.