2011-11-30 13:56:29

ደቡብ አፍሪቃ፣ የተፈጥሮ የአየር ንብረት ጉባኤ


200 ልኡካን ያሳተፈው 17ኛው ዓለም አቀፍ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ያነቃቃው ስለ የአየር ንብረት ርእሰ ጉዳይ የሚወያይ ጉባኤ በደቡብ አፍሪቃ ዱርባን ከተማ እየተካሄደ መሆኑ ሲገለጥ፣ አረንጓዴው የኃይል ምንጭ ተጠቅሞ ለማነቃቃት ብሎም ላስተማማኝ የክዮቶው ስምምነት ትግባሬ RealAudioMP3 የሚወያይ መሆኑ ሲገለጥ፣ በተለይ ደግሞ እስከ ጥር 1 ቀን 2013 ዓ.ም. የክዮቶ ስምምነት ቀዳሚው የተፈጻሚነት የሚመለከት ቀነ ቀጠሮው ከዛሬ እስከ 2020 ዓ.ም. ለማሸጋገር ያለመ እ.ኤ.አ. የ 2009 ዓ.ም. የኮፐንሃገን ቀጥሎም እ.ኤ.አ. የ 2010 ዓ.ም. የካንኩን ውጤት ሳያስገኝ የቀረው ጉባኤ፣ ይህ እ.ኤ.አ. እስከ ታህሳስ 9 ቀን 2011 ዓ.ም. የሚዘልቀው በዱብርባን እየተካሄደ ያለው ጉባኤ ውይይት የሚካሄድበት መሆኑም ተገልጠዋል።
በአሁኑ ወቅት ዓለማችን የሚጠቀምበት የኃይል ምንጭ ሥልት ከነአካንቴ ሥር ነቀላዊ ለውጥ ያሻዋል፣ ካልሆነ ግን የሚከስተው የተፈጥሮ አደጋ እና የሚያስከትለው የሰው እና የንብረት ጉዳት ለመቆጣጠር የማይቻል መሆኑ የሥነ ዓየር ጠባይ ሊቃውን ይናገራሉ። እ.ኤ.አ. ከ 1850 ዓ.ም. ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ የታየው በነዚህ ባለፉ ዓሥር ዓመታት ከፍ እያለ በመሄድ ላይ ያለው አስጊው የመሬት ሙቀፍ ኃይል ጭማሬ ለመቆጣጠር እና ለማስወገድ ከተፈለገ የአረንጓዴው የኃይል ምንጭ ተጠቃሚነት ማስፋፋት እና ማሳየል ወሳኝ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን፣ ይኸንን እቅድ እውን ለማድረግ የባህል ትግል ጭምር የሚጠይቅ ሂደት መሆኑ በኢጣሊያ ሮማ በሚገኘው ላ ሳፒየንዛ መንበረ ጥበብ የኃይል ምንጭ ጉዳይ የሚከታተለው ቢሮ ተጠሪ ሊቪዮ ደ ሳንቶሊ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ አመልክተዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለም ባለፈው እሁድ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ጸሎት መልአከ እግዚአብሔር ከማሳረጋቸው ቀደም በማድረግ ባቀረቡት ስብከት፣ የዓለም ኅብረተሰብ የተወሳሰበውን እና እጅግ አሳሳቢ የሆነውን በተደጋጋሚ የሚከሰተው የተፈጥሮ የአየር ንብረት መዛባት ለመቆጣጠር እና ዝቅ እንዲል ታልሞ የሚደረገው ጥረት፣ የድኾች አገሮች እና የመጪው ትውልድ አስቸኳይ መሠረታዊ ጥያቄ ግምት መስጠት የሚል ኃላፊነት የተሞላው አስተማማኝ መደጋገፍ እና መተሳሰብ የሚያነቃቃ መሆን ይገባል እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ ይጠቁማል።







All the contents on this site are copyrighted ©.