2011-11-30 13:52:00

የሪዮ ደ ጃኒየሮ ሕፃናት “ምኞታችን በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. መጎብኘት ነው”።


ባለፉት ቀናት በተለያዩ ማኅበራዊ ድረ ገጽ አማካኝነት በሪዮ ደ ጃኒየሮ የመንገድ ተዳዳሪ ሕፃናት ከወደቁበት አቢይ ማኅበራዊ እና ሰብአዊ ችግር ለመገላገል እና መጻኢያቸው እንዳይኮላሽ አልመው ዘርፈ ብዙ እንክብካቤ በመስጠት አገልግሎት የተጠመዱት አባ ረናቶ ኪያራ እ.ኤ.አ. በ 2013 ዓ.ም. RealAudioMP3 በብራዚል ሪዮ ደ ጃኔርዮ እንዲካሄድ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የወሰኑት 27ኛው ዓለም ዓቀፍ የወጣቶች ቀን ምክንያት ለወጣት ትውልድ መሪ ቃል ለመስጠት በሚገኙበት ወቅት እነዚህ የጎዳና ተዳዳሪ ሕፃናት ከወደቁበት ችግር ለማላቀቅ የሚረዱበት የሕፃናት ቤት የተሰኘውን ማእከል እንዲጎበኙ በዚሁ ማእከል የሚተዳደሩት ሕፃናት አቢይ ጉጉት መሆኑ ይፋ ማድረጋቸው አባ ኪያራ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ ገልጠው። በዚህ የዘመነ ምጽአት ወቅት ይህ ማእከል ያነቃቃው ሐሳብ መሆኑም አብራርተዋዋል።
በርግጥ ይላሉ አባ ኪያራ፣ ዘመነ ምጽአትን ሳስብ እና ስመለከት፣ የማን ምጽአት የሚል ጥያቄ ለገዛ እራሴ አቀርባለሁኝ፣ በዓለ ልደትን ሳስብ እና ስመለከት ተመልሼ የማን ልደት የሚል ጥያቄም አነሳለሁኝ፣ አካባቢየን ስቃኝ የበዓለ ልደት መንፈስ ከወዲሁ ለማሰማት የተለያዩ መብራቶች ቦግ ሲሉ፣ ለዚያ በዓል የሚቆረሱ የጣፋጭ ዳቦ ንግድ የገበያ ቦታዎች ሲጨናነቁ አያለሁ፣ በእውነቱ የሆነ ነገር ለመግዛት ሽርጉድ ሲባል ይታያል። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ግን በዚያ ቦታ አይገኝም፣ ይኸንን ሁሉ ሳይ በውስጤ እጨነቃለሁ በዓለ ልደት ለምን? እኔ ኢየሱስን ነው የምፈልገው፣ የተፈቀርን መሆናችንን ለማረጋገጥ ሲል ሰው-ሕፃን ሆኖ በመካከላችን ያደረው እግዚኣብሔርን ነው የምሻው፣ ይኸ በገበያ ቦታዎች የማይገኘው ሕፃን አሁን አግኝቼዋለሁኝ በሁሉም ሰው ዘንድ በሁሉም ሕፃናት ዘንድ አግኝቼ ተዋውቄዋለሁ። በሰው እና በሕፃናት ዘንድ ያገኘኹት ጌታ ሕይወቴን ለውጦታል። ይኽ መለወጥ በብራዚል አበይት ከተሞች በሚገኙት ጥጋ ጥግ ክፍለ ከተሞች ወርጄ በሁሉም በተናቀው በድኻው እርም በተባለው እና በተተወው ለእርሱ የሚሆን የማደሪያ ሥፍራ አልነበረም የተባለው ሕፃን ኢየሱስ በመንገድ ተዳዳሪው ሕፃን ዘንድ እንድፈልገው አድርጎኛል። እንደ ኢየሱስ በሕፃናት አቢይ ሥቃይ ውስጥ በመግባት ሥቃያቸውን የራስ በማድረግ በእነዚህ በተተዉት ዘንድ በመሄድ በዓለ ልደት፣ የእነርሱ ልደት እንደሆነና ለብቻቸው እንዳልሆኑ ከአንተ ጋር ነን ለማለት ወደ እነርሱ እንሂድ። ሕፃናት የሚፈልጉት እንደ መሆናቸው የሚያፈቅራቸው ሰው ነው።
የጎዳና ተዳዳሪ ከወደቁበት አደጋ ለማላቀቅ የተከፈተው የተሟላ አገልግሎት የሚያገኙበት ከማደሪያ ማእከል በመቀጠል በተለያዩ አደገኛ አደንዛዥ እጸዋት ተጠቃሚ የሆኑት የጎዳና ተዳዳሪ ሕፃናት ከወደቁበት አሰቃቂው ችግር ለማላቀቅ የተሟላ አገልግሎት የሚሰጥ ማእከል እንደተከፈተም አባ ኪያራ ገልጠው፣ ለእነዚህ ሕፃናት የአደንዛዥ እጸዋት ተጠቃሚ ሱሰኞች ከወደቁበት አቢይ ችግር ለማላቀቅ በሚደረገው ጥረት አማካኝነት ለሁሉም የአደንዛዥ እጸዋት ተጠቃሚው የህብረተሰብ ክፍል ምክር ለመስጠትም ያቀደ ጭምር ነው ብለዋል።
በአሁኑ ወቅት እነዚህ የዚህ ማእከል ተዳዳሪ ሕፃናት የሚጠባበቁት አቢይ ጸጋ የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ሐዋርያዊ ጉብኝት መሆኑ አባ ኪያራ ገልጠው፣ የእነዚህ ሕፃናት ምኞት በተለያዩ ማኅበራዊ ድረ ገጽ አማካኝነት ይፋ መደረጉ ለማወቅ ሲቻል፣ ይኸንን አቢይ ስጦታ ነው በመጠባበቅ ላይ ያለነው ብለው ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. እ.ኤ.አ. በ 2013 ዓ.ም. በብራዚል ሪዮ ደ ጃኒየሮ በሚከበረው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን እንደሚገኙ የሚታወቅ ሲሆን፣ በዚህ ምክንያት የእሳቸውን ሐዋርያዊ ጉብኝት በጎዳና ተዳዳሪ ሕፃናት መርጃ ማእከል የሁሉም ሕፃናት ምኞት መሆኑ ገልጠው፣ በዚህ አማካኝነት የእነዚህ ሕፃናት ማደሪያ እና መርጃ ማእክል የተስፋ ምልክት መሆኑ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በሚያከናውኑት ሐዋርያዊ ጉብኝት ለማረጋገጥ ነው የምንፈልገው። እግዚአብሔር አለ ምንም ቅድመ ሁኔታ እንደ መሆናቸው መጠን የሚያፈቅራቸው መሆኑ በቤተ ክርስትያን እና አቢይ እና እንደ ቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ርህሩኅ አፍቃሪ ልብ ባላቸው ሰዎች አማካኝነት ሊመሰከርላቸው ይገባል ሲሉ የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.