2011-11-29 10:34:49

የቅድስት መንበር ርእሰ ዓንቀጽ፦ ሁለቱ የአፍሪቃ በሮች


ሁሌ መሳምንት ማገባደጃ የቅድስት መንበር የዜና ማኅተም ክልፍ ተጠሪ የቫቲካን ረዲዮ ዋና አስተዳዳሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ የሚያቀርቡት የቅድስት መንበር ርእሰ አንቀጽ በመቀጠል ከትላትና በስትያን ሁለቱ የአፍሪቅ በሮች በሚል ርእስ ሥር ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በአፍሪቃ በኒን እ.ኤ.አ. ከህዳር 18 ቀን እስከ ህዳር 20 ቀን 2011 ዓ.ም. ያካሄዱት ሐውርያዊ ጉብኝት RealAudioMP3 እና እዛው ለመላ አፍሪቃ ብፁዓን ጳጳሳት የለገሱት ሁለተኛው የመላ አፍሪቃ እና ማዳጋስካር ብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ ያቀረበው የፍጻሜ ሰነድ መሠረት አፍሪካ ሙኑስ-የአፍሪቃ ቃለ መሓላ” የተሰየመው የደረሱት ሐዋርያዊ ምዕዳን በይፋ ያስረከቡበት ወቅት እንደነበርም አስታውሰው፣ ቅዱስ ኣባታችን ር.ሊ.ጳ. በዊዳ በሐዋርያዊው ምዕዳን ፊርማቸውን የማኖር ሥነ ሥርዓት ፈጽመው ባሰሙት ንግግር፣ በአፍሪቃ የምትገኘው ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ሰላም እና ፍትህ ለማነቃቃት ተጠርታለች ብለው፣ ስለዚህ የተቀበልነው የድህነት ጸጋ መሠረት ማንኛውም ዓይነት ባርነት መቃወም እና ማውገዝ እንዳለብን የሚያመለክት ነው። እነዚህ ሁለት በሮች እነርሱም ከአፍሪቃ በአሰቃቂው እና አስነዋሪው ጸአ ሰብአዊው የባርነት ዘመን ወቅት ይሸጡ እና ይለወጡ የነበሩት ሰዎች የሚተላለፉበት በር በዚያ በር በኩል ስብከተ ወንጌል የገባበት መሆኑም በመጥቀስ ያ የሰው ልጅ ለስቃይ የዳረገው አባርነት በር ተዘግቶ፣ የድህነት አዋጅ አብሳሪዎች ልኡካነ ወንጌል ወደ ምዕራብ አፍሪቃ መግቢያ መከፈቱ ዘክርረው፣ የመጀመሪያ በር በሁልተኛው በር እርሱም በድህነት በር፣ ጥፋት በተስፋ የተተካበት መሆኑ አባ ሎምባርዲ በርእሰ ዓንቀጹ አብራርተዋል።
ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16 ለአፍሪቃ ቤተ ርክስትያን የለገሱት ሐዋርያዊ ምዕዳን ስለ አፍሪቃ ያለፈው እና ወቅታዊው ሁኔታ ችግሮችንም ጭምር የሚዳስስ ስለ ክፍለ አለሟ ዘርፈ ብዙ ጥናት በማድረግ ለብሩህ መጻኢ ልትከተለው የሚገባት መንገድ የሚያመለክት እስካሁን በፊት በማንም ያልቀረበ የተሟላ ሰነድ መሆኑና ከዚህ ሐውርያዊው ምዕዳን ጋር የሚስተካከል ስለ አፍሪቃ ጉዳይ የሚያትት ሰነድ እንደሌለ ብዙዎች የሥነ አፍሪቃ ሊቃውንት እና አበይት ምሁራን አስተያየታችው እንደሰጡበትም አባ ሎምባርዲ ጠቅሰው፣ ከአፍሪቃዊው አስተያየት የመነጨ አፍሪቃ ስለ አፍሪቃ የምትለው ማእከል ያደረገ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ በምድር የክርስቶስ ልኡክ በመሆናቸውም መሠረት ባላቸው ኩላዊነት መንፈስ አማካኝነት ተጢኖ ከአፍሪቃ ለአፍሪቃ የደረሱት ሐዋርያዊ ምዕዳን ነው ብለዋል።
ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በበኒን የተደረገላቸው ልባዊ አቀባበል ለምዕራቡ አለም ጥያቄ እና አብነት መሆኑ አባ ሎምባርዲ ገልጠው፣ ቅዱሱነታቸው አፍሪቃ የሰው ዘር መንፈሳዊነት እና ሰብአዊነት ቀመጥ ነች ሲሉ አለ ምክንያት አይደለም በማለት ርእሰ አንቀጹን አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.