2011-11-29 10:32:41

አባ ካንታላሜሳ፦ ዘመነ ምፅአት፣ ለእምነት ዓመት የበለጠ ማዘጋጃ ነው፣።


የቤተ ጳጳስ ሰባኬ አባ ራኒየሮ ካንታላሜሳ ትላትና በላቲን ሥርዓት የተገባው ወደ ዓመታዊው የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ልደት የሚያሸጋግረን የምጽአት ዘመን ተብሎ የሚለየው ወቅት መሠረት በማድረግ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ የጌታችን ኢየሱስ ክስቶስ በዓለ ልደት በየዓመቱ የሚከበር ነው። ሆኖም የዚህ ዓቢይ በዓል በየዓመቱ በምንከተለው የሊጡርጊያ ዑደት ያለው አዲስ መንፈስ፣ RealAudioMP3 ከመንፈስ ቅዱስ የሚመነጭ ነው። የእግዝአብሔር ቃል ዘወትር የተሰማው ቃል ቢሆንም ቃል ዘወትር አዲስ እና የማያረጅ ነው።
በአሁኑ ወቅት ቤተ ክርስትያን አዲስ አስፍሆተ ወንጌል ርእሰ ጉዳይ በማድረግ በሚቀጥለው ዓመት የሚካሄደው የእንተ ላእለ ኩሉ ቤተ ክርስያን ብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ እንዲከበር የወሰኑት የእምነት ዓመት አማካኝነት በመላ ካቶሊክ ቤተ ክርስትይን የሚንጸባረቅ መንፈሳዊ ተግባር ነው። ዘመነ ምጽአት የማርያም እምነት፣ የእረኞች የከዋክብት ተማራማሪዎች እምነት የሚያስተነትን ነው። ስለዚህ ዘመነ ምጽዓት ለእምነት ዓመት የበለጠ የማዘጋጃ ወቅት ነው መሆኑ አብራርተዋል።
የጸሎት የአስተንትኖ የጽሞና ጊዜ ነው። ስለዚህ ከተደጋጋሚው ዕለታዊ ኑሮ ወጣ ተብሎ፣ እርሱም እያንዳንዱ ኃላፊነቱን ሥራውን እና ተልእኮውን ሳይዘነጋ፣ ለመንፈሳዊ ተግባር መትጋት እንዳለበት በመጥቀስ፣ በዚህ መሠረትም ጸሎት አስተንትኖ እና የጽሞና ጊዜ የምንኖርበት ወቅት ነው። የምንኖረው ዘመነ ምጽኣት ለገዛ እራሱ ትርጉም ያለው ቢሆንም፣ በእኛ ሕይወት ዘንድ ትርጉም እንዲኖረው ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መምጣት የምንሰጠው ክብር መግለጫም ነው። ስለዚህ የቅድስት ድንግል ማርያም አብነት የምንክተልበት ወቅት ነው ካሉ በኋላ ቅዱስ ቦናቨንተር እንደሚለውም መንፈስ ቅዱስ ወደ ሚጠበቅበት ወደ ሚፈለግበት እና ወደ ተፈቀረበት ዘንድ ይነፍሳል ነውና፣ ስለዚህ እኛ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ምጽአት የምንሻ የምንጠባበቅ ሆነን መገኘት አለበን ብለዋል።
በዚህ የዘመነ ምጽአት ሊጡርጊያ መሠረት ነቢይ ኢሳያስ በብዛት የሚነበብበት ወቅት ነው። ነቢይ ኢሳያስ በጣም ሩቅ በሆነ ጊዜ ስለዚህ ምጽአት በጥልቅ የተናገረ መሆኑም አባ ካንታላሜሳ በማስታወስ፣ ቀጥሎም ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ የሚጎላበት የእርሱ ጥሪ ፍጻሜ በመጨረሻም፣ ዘመነ ምጽአት በተስፋ የመጠባበቅ አብነት ማእከል በሆነቸው የማርያም እምነት የሚያተኩር ጌታችን ኢየሱ ስክርስቶስ ጋር ለመገናኘት የምንዘጋጅበት ወቅት ነው በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.