2011-11-25 13:23:44

የጤና ጥበቃ ባለ ሙያዎች ጉዳይ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት
26ኛው ዓለም አቀፍ ዓመታዊ ምሉእ ጉባኤ


“የር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ሥልጣናዊ ትምርህት መሠረት የጤና ጥበቃ ሓዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ለሕይወት አገልግሎት” በሚል ርእስ ሥር የተመራ የጤና ጥበቃ ባለ ሙያዎች ጉዳይ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ያዘጋጀው 26ኛው ዓለም አቀፍ ዓመታዊ ምልኡ ጉባኤ ትላትና በአገረ ቫቲካን RealAudioMP3 በሚገኘው በአዲሱ የሲኖዶስ አዳራሽ መጀመሩ የቅድስት መንበር መግለጫ አመለከተ።
ይህ እስከ ነገ እ.ኤ.አ. ህዳር 26 ቀን 2011 ዓ.ም. የሚከናወነው ዓለም አቀፍ ጉባኤ ከተለያዩ 70 አገሮች የተወጣጡ 40 ብፁዓን ጳጳሳት ያካተተ በጠቅላላ 685 ተጋባእያን የሚይሳትፍ ሲሆን፣ ሕይወት ዘወትር አሸናፊ መሆኑ ታምነን እና እርግጠኞች ሆነን በዚህ ጉባኤ ተገኝተናል በማለት የሕይወት ባህል ማእከል ያደረገ ንግግር በማሳማት ጉባኤን ያስጀመሩት የጤና ጥበቃ ባለ ሙያዎች ጉዳይ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ዚግሙንት ዚሞውስኪ ስለ ጉባኤው በማስመለከት ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ ዓለም እንደ አንድ ፍርጃ የሕይወት እና የሞት ሥልጣኔዎች የሚፋለሙበት መድረክ እየሆነ በመምጣቱ ምክንያት፣ ኅሊናን ለማነቃቃት እና ሕይወት ከመጸነስ እስከ ባህርያዊ ሞት የሚል የጤና ተንከባካቢ ሐዋርያዊ ግብረ ኖሎዎ ክቡር ዋጋ የሚሰጥ አንድ የጋራ ሥነ ምግባር በዚህ በሚካሄደው ዓለም አቀፍ ጉባኤ የሚደረገው አስተንትኖ በተለያየ መልኩ እና ደረጃ በደረጃ እንደሚያበክረው ነው ሲሉ፣ በጉባኤው የሚሳተፉት የጤና ጥበቃ ባለ ሙያዎች ጉዳይ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ልሂቅ ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ፊዮረንዞ አንጀሊኒ በበኩላቸውም ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ ር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ስለ በሽታ ጉዳይ በተመለከተ የተናገሩ ብቻ ሳይሆን በሕይወታቸው በመኖር የመሰከሩት የሕይወት ገጠመኝ ነው ብለዋል።
ር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ የክራኮቪያ ሊቀ ጳጳስ በነበሩበት እና ከዛም የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ሆነው ከተሾሙ በኋላም፣ የግል ዋና ጸሓፊያቸው በመሆን ያገለገሉት አሁን የክራኮቪያ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ካሪዲናል ስታኒስላው ድዝዊች፣ ብፁዕ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ በወጣትነት ዕድሜያቸው ካዘም ካህን፣ ጳጳስ በመጨረሻም የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ሆነው በተሾሙበት እና በዚህ ጥሪ በማገልገል የኖሩት ሕይወት በሽታ በጠቅላላ ስቃይ በተለያየ መልኩ መላ ሕይወታቸው እንደሸኛቸው አስታውሰው፣ ሆኖም ግን በሽታና ስቃይ እንደ ጸጋ በመቀበል ነበር የኖሩት በማለት ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ አብራርተዋል።
በጉባኤው የሚሳተፉት የኢጣሊያ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ረናቶ ባልዱዚ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ በሽታ በአወንታዊ መልኩ ወይንም ጸጋ ብሎ ለመቀበል የሚጠይቀው መንፈሳዊ እና ሰብአዊ ጽናት እጅግ ከፍ ያለ በምሆኑም በእውነቱ የሕይወት እና የሥቃይ ወንጌል ለቤተ ክርስትያን እና ለሰው ልጅ መጻኢ አስፈላጊ መሆኑ ለመገንዘብ እና በዚህ መልኩ ለማሰብ የሚቻል ነው ለሚለው እማኔ ለምንኖርበት ዓለም ብቻ ሳይሆን፣ ለዚህ ዓለም አቀፍ ጉባኤ ጭምር ፈታኝ ነው ካሉ በኋላ፣ የሕይወት መብት እና ፈቃድ የግዴታዊ ተግባር ውሳኔ የኢጣሊያ ሕገ መንግሥት የሚጠቅሰው ክብር ብቻ ሳይሆን፣ የሕይወት መብት እና ፈቃድ ግዴታዊ ተግባርነት የሁሉም የሰብአዊ መብት እና ፈቃድ መሠረት ወይንም ቅድመ ሁኔታ በማድረግ እንዳስቀመጠው አብራርተው፣ ስለዚህ የሕይወት መብት እና ፈቃድ ግዴታዊ ውሳኔ መሠረታዊ እሴት፦ የሰብአዊ ክብር መርህ ነው ብለዋል።
ይህ ዓለም አቀፍ ጉባኤ በጤና ጥበቃ ጉዳይ በሚመለከተው የኤኮኖሚ እና የፖለቲካ ዘርፍ እንዲሁም የጤና ጥበቃ ተንከባካቢ ማኅበራት ተጠሪዎች እና የተለያዩ ሃይማኖት ልኡካን ጭምር የሚያሳትፍ መሆኑ የቅድስት መንበር መግለጫ ያመለክታል።








All the contents on this site are copyrighted ©.