2011-11-25 13:27:19

ብፁዕ ካርዲናል ሳራህ፦ የኤውሮጳው የኤኮኖሚው ቀውስ መንስኤ የግብረ ገብ እና የመንፈሳዊነት መቃወስ ነው።


ካሪታስ በሚል ስያሜ የሚጠውራው የእንተ ላእለ ኵሉ ቤተ ክርስትያን የተራድዖ ማኅበር በኢጣሊያው ያለው ቅርንጫፍ የተመሠረተበት 40ኛው ዓመት ምክንያት በኢጣሊያ RealAudioMP3 ፊዩጂ ከተማ የማርቆስ ወንጌል ምዕራፍ 6 ቍጥር 34 “ኢየሱስ ከጀልባው ሲወርድ ብዙ ሕዝብ አየ፣ እረኛ እንደሌላቸው በጎች በመሆናቸውም አዘነላቸው፣ ብዙ ነገርም ያስተምራቸው ጀመር” የሚለው ቃለ ወንጌል መርህ ፣ ቤተ ክርስትያን በግብረ ሠናይ አማካኝነት ታንጻለች በተሰኘው ርዕስ ተሸኝቶ እ.ኤ.አ. ከህዳር 21 ቀን እስከ ህዳር 23 ቀን 2011 ዓ.ም. በተካሄደው 35ኛው ብሔራዊ ጉባኤ በመገኘት ንግግር ያሰሙት የእንተ ላእለ ኵሉ ቤተ ክርስትያን ግብረ ሠናይ አስተባባሪ ኮር ኡኑም-ውሁድ ልብ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ሮበርት ሳራህ በምዕራቡ ዓለም የሚታየው የኤኮኖሚ እና የቁጠባ ቀውስ መሠረታዊ መነሾ በምዕራቡ ዓለም ያንሰራፋው የባህል የሥነ ምግባር እና የመንፈሳዊነት ቀውስ መሆኑ በማብራራት፣ ይኽንን ዓለም ከቁሳዊነት፣ አርቆ ከማያስበው የቅርብ ጥቅም ከሚለው ጽንሰ ሐሳብ በመንደረደር ከሚከተለው የጥቅማ ጥቅም ሥነ አመክንዮ ነጻ ማውጣት አለብን ካሉ በኋላ፣ ከዚህ የሥነ ምግባር እና የግብረ ገብ መቃወስ ከሚታይበት ሁኔታ በመንደርደር፣ በመስፋፋት ላይ ካለው አዲስ ድኽነት ከሚባለው ሕዝቦችን በከፍ ከሚያጠቃው ጸረ ሕይወት፣ ጸረ ቤተ ሰብ፣ ጸረ ምሥጢረ ተክሊል እና ጸረ ሰብአዊ ክብር ከሚለው ውድቀት ለማላቀቅ መትጋት ይኖርብናል እንዳሉ ሲር የዜና አገልግሎት አመለከተ።
ግብረ ሠናይ አንዱ የማኅበራዊ ሙያ አድርጎ የመመልከቱ አዝማሚያ ከቤተ ክርስትያን የግብረ ሰናይ ተልእኮ መንፈስ ጨርሶ መወገድ አለበት። ሁሉም የቤተ ክርስትያን ዓለም አቀፍ እና ብሔራዊ አቀፍ የተራድዖ ማኅበራት አገልግሎት የማኅበራዊ ሙያ ጉዳይ አድርጎ ከመመልከቱ ፈተና መላቀቅ ይኖርባቸዋል። ስለዚህ በዚህ ተልእኮ እምነት መሠረት በማድረግ ከእምነት የመነጨ ግብረ መልስ የማይጠብቅ የሚሠዋ ግብረ ሰናይ ማቅረብ መቻል አለብን። በዚህ መልኩ የኢጣሊያ ብሔራዊው የካሪታስ የተራድዖ ማኅበር በዓለም የሰጠው እና እየሰጠው ባለው አገልግሎት የሚመሠገን ነው ካሉ በኋላ፣ የእንተ ላእለ ኵሉ ቤተ ክርስትያን የግብረ ሠናይ ማኅበር ከተለያዩ ዓለም አቀፍ እና ብሔራዊ አቀፍ የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን የግብረ ሠናይ ማኅበራት እና ከተለያዩ የተራድዖ ማኅበራት ጋር በመተባበር የሚሰጠው የተቀናጀው አገልግሎት የተዋጣለት መሆኑ ጠቅሰው፣ የድኽነት መሠረት ናቸው የሚባሉትን ሙስና ምግባረ ብልሽት የሕዝብ ጥቅም አለ ማስቀደም የተሰኙትን በተለይ በማደግ ላይ በሚገኙት አገሮች የግብረ ገብ እና የሥነ ምግባር መቃወስ የማይመለከተው፣ ብሥፋት የሚታየው የግብረ ገብ እና የሥነ ምግባር ድኽነት እንዲቀረፍ የቤተ ክርስትያን የግብረ ሠናይ ተልእኮ ሰብአዊ እርዳታ በማቅረብ ብቻ ሳይታጠር በሕንጸት ተልእኮ ያለው ኃላፊነት እጅግ ወሳኝ ነው እንዳሉ ሲር የዜና አገልግሎት አመለከተ።







All the contents on this site are copyrighted ©.