2011-11-23 14:52:06

የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሳምንታዊ የዕለተ ረቡዕ አጠቃላይ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ (እ.ኤ.አ. 23/11/2011)
“ቤተ ክርስትያን በአፍሪቃ ተስፋ ለተሞላው ብሩህ ወቅት ዋነኛ ተወናያን”


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ እንደተለመደው ቫቲካን በሚገኘው በር.ሊ.ጳ. ጳውሎስ ስድስተኛ የጉባኤ አዳራሽ ሳምንታዊው የዕለተ ረቡዕ አጠቃላይ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ አቅርበዋል።RealAudioMP3
ቅዱስነታቸው የዛሬው የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ በቤኒን ያካሄዱት የቅርቡ ሐዋርያዊ ጉብኝት ትውስት አሁንም በሳቸው ዘንድ ጥሎት ያለፈው አስደናቂው ገጠመኝ ማእከል በማድረግ ለማቅረብ እንደሚሹ ገልጠው፣ በቅድሚያ በእግዚአብሔር አሳቢነት ዳግም ወደ አፍሪቃ ተመልሼ እንደ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ በበኒን 150ኛው ዓመት ዝክረ አስፍሆተ ወንጌል እና እንዲሁም በአፍሪቃ ለምትገኘው ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን አፍሪካ ሙኑስ - የአፍሪቃ ቃለ መሓላ በሚል ርእስ ሥር የአፍሪቃ ድህረ ሁለተኛው ሲኖዶስ ምክንያት የደረሱት ሓዋርያዊ ምዕዳን ፊርማቸው በማኖር በይፋ ለማስረከብ ያቀደ ሐዋርያዊ ጉብኝት እንዳከናውን ለፈለገው ጌታ ከልብ የመነጨ ምስጋናዮ አቀርባለሁኝ።
እ.ኤ.አ. በ 2009 ዓ.ም. ጥቅምት ወር በቫቲካን የተካሄደው ሁለተኛው ልዩ ጉባኤ ለአፍሪቃ የብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ ያቀረበው ሃሳብ፣ የሰጠው ትንታኔ መሠረት በማድረግ በዚያች ታላቅ ክፍለ ዓለም ለሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ መመሪያ ይሆን ዘንድ የደረሱት ሐዋርያዊ ምዕዳን፣ ለአፍሪቃ ለማስረከብ፣ ከዚሁ ጋር በማያያዝም ለገናናው አቢይ የቤተ ክርስትያን ሰው፣ ለማይረሱት የቤኒን እና የአፍሪቃ ልጅ የሆኑት በክብር ለሚዘከሩት ለነፍሰ ኄር ብፁዕ ካርዲናል በርናርዲን ጋንቲን በተለይ ደግሞ የአገር አበው ተብለው በሚጠሩበት በበኒን ኅያው ለሆነው ተዘክሮ ክብር ለመስጠት የመቃብር ሥፍራው ለመጎብኘት እና እዛው ለመጸለይ መሆኑ ቅዱስነታቸው ገልጠዋል።
በቤኒን ያካሄዱት ሐዋርያዊ ጉብኝት የተዋጣለት እንዲሆን ካለ መታከት አስተጽዖ ላደረጉት በተለይ ደግሞ የቤኒን ረፓብሊካዊት ርእሰ ብሔር እና በፍቅር ላስተናገድዋቸው ለኮቶኑ ሊቀ ጳጳስ እንዲሁም ለሁሉም ወንድሞቼ የተከበሩት የአገሪቱ ብፁዓን ጳጳሳት ካህናት ገዳማውያን ዲያቆናት የትምህርተ ክርስቶስ አስተማሪዎች ሥፍር ቁጥር ለሌላቸው ወንድሞች እና እህቶች በአቢይ እምነት እና በዚሁ ሓዋርያዊ ጉብኝት ለሸኙዋቸው ዘክረው፣ ከልብ የመነጨ ኅያው ምስጋና ካቀረቡ በኋላ፣ በዚህ ሐዋርያዊ ጉብኝት ሁሉም በጋራ ልብን የሚነካ የእምነት ገጠመኝ ለመኖር እና በዚህ የቤኒን 150ኛው ዓመት ዝክረ አስፍሆተ ወንጌል አገባብ ኅያው ከሆነው ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ያለውን ግኑኝነት ዳግም ለማደስ መቻሉንም ገልጠዋል።
ልዩ ሁለተኛው ጉባኤ ለአፍሪቃ የብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ ያስጨበጠው ውጤት በዊዳ የቅድስት ንጽሕት ድንግል ማርያም ባዚሊካ በቅድስት ድንግል እመቤት እግር ሥር በማኖር ለእርስዋ ጥበቃ ማስረከባቸው ገልጠው፣ በአፍሪቃ የምትገኘው ቤተ ክርስትያን በማርያም አብነት ሥር ብሥራተ ወንጌል በመቀበል በእምነት ብዙ ሕዝቦችን ለማፍራት መቻልዋንም አስምረውበታል።
ማኅበረ ክርስትያን በእምነት ታድሶ ልዩ ሁለተኛው ጉባኤ ለአፍሪቃ የብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ እና እንዲሁም በበኒን ያከናወኑት ሐዋርያዊ ጉብኝት መሪ ቃል የሆነው እርቅ ፍትሕ እና ሰላም ለሚለው መርሆ ዘወትር አገልጋይ እንዲሆን መጠራቱንም ቅዱስ አባታችን ገልጠው፣ በቅድሚያ የመለኮታዊ ምሕረት ደስተኞች መሣሪያ እዲሆኑ በመካከላቸው እርቅ እንዲኖሩ ተጠርተዋል። እያንዳንዱ ያለው መንፈሳዊ እና ቁሳዊ ሃብት ለዚህ ለጋራው ዓላማ ሊያውለው ይገባል።
የእርቅ መንፈስ በማህበራዊው ደረጃ ወሳኝ መሆኑ እና ለተለያዩ የሃይማኖት መሪዎች እና የመንግሥታት ልኡካን ፊት ተገኝተው ባሰሙት ቃል የአፍሪቃው ማኅበራዊ ፖለቲካ እና ኤኮኖሚም ጉዳይ ለተስፋ ክፍት መሆን ያስፈልገዋል እንዳሉም ዘክረው፣ በዚያ አጋጣሚ ባለፉት የመጨረሻ ወሮች ብዙኃን የአፍሪቃ ሕዝብ እያነቃቃ ያለው ጽኑ የነጻነት እና የፍትሕ ፍላጎት እና ጥማት አስታውሰው፣ የአፍሪቃ ጉዞ በተስፋ የተነቃቃ እንዲሆን በማሳሰብ፣ በተለያዩ ጎሳዎች እና ሃይማኖቶች መካከል ያለው ግኑኝነት በውይይት እና በስምምነት መኖር የሚለየው ጠባይ መሠረት የተገነባ ኅብረተሰብ አስፈላጊ መሆኑ እንዳሰመሩበትም አስታውሰው፣ ሁሉም በበተለያየ አካባቢ እና በተጨባጭ ሁኔታም የተስፋ ዘር የሚዘራ ሆኖ እንዲገኝ ጥሪ ማቅረባቸው ገልጠዋል።
በኮቶኑ በሚገኘው ወዳጅነት የተሰየመው የእግር ኳስ ሜዳ ተገኝተው እሁድ ባሳረጉት መሥዋዕት ቀዳሴ ለተገኙት ጭምር ያሉትን ሃሳብ ዘክረው ክርስትያኖች የተስፋ ሰዎች ናቸው። ስለዚህ ስለ ወንድሞቻቸው እና እህቶቻቸው ግድ የሌላቸው ሆነው መኖር አይችሉም ካሉ በኋላ፣ ሕፃን አዛውንት ወጣቱ ሁሉም የበኒን እና ከተለያዩ የአፍሪቃ አገሮች የተወጡት እዛው በመሥዋዕተ ቅዳሴ ለመሳተፍ የተገኙት ምእመናን ትውልድ የሚያስተባብር አንድነት እንዲኖራቸው የሚያደረገው የተለያየው የሕይወት ወቅት ለሚደቅነው ፈተና እንዲሸገር የሚያበቃው የእምነት እድገት የሚያረጋገጥ የሚያስደንቅ ምስክርነት የታየበት ሁኔታ ነበር ብለዋል።
በዚያ ልብን በሚማርክ ክቡር በዓል ወቅትም የመላ የአፍሪቃ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤቶች ለሚያቅፈው የአፍሪቃ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ሊቀ መንበር አፍሪካ ሙኑስ - የአፍሪቃ ቃለ መሐላ በሚል ርእስ ሥር የደረሱት ድኅረ ሲኖዶስ ሐዋርያዊ ምዕዳን አንድ ቀን ቀደም በማድረግ በዊዳ ፊርማቸውን ያኖሩበት ለአፍሪቃ ብፁዓን ጳጳሳት ካህናት ገዳማውያን ለትምህርተ ክርስቶስ አስተማሪዎች ለዓለማውያን ምእመናን የሚቀርበው መሪ ሰነድ በይፋ መስጠታቸውንም ዘክረው፣ ይህ የዚያ ልዩ ሁለተኛው ጉባኤ ለአፍሪቃ የብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ ውጤት የሆነው ሐዋርያዊ ምዕዳን በኃላፊነት በማስረከብ በዚህ በሶስት ሺሕኛው ዘመን በአፍሪቃ ለምትጓዘው ቤተ ክርስትያን ለምታከናውነው የአስፍሆተ ወንጌል ተልእኮ የሚጠይቀው ጥረት ተገቢ መልስ ለመስጠት እንዲቻልም ሰነዱን ተጠንቅቀው እንዲያስተነትኑበት እና በሙላትም እንዲኖሩት ማሳሰባቸው ገልጠዋል። በዚያ እጅግ አስፈላጊ በሆነው ሰነድ እያንዳንዱ ምእመን በአፍሪቃ የምትገኘው ዘወትር የምድር ጨው እና የዓለም ብርሃን እንድትሆን የተጠራቸው ቤተ ክርስትያን ለምታከናውነው ጉዞ የሚመራ እና የሚያበረታታ መሠረታዊ መመሪያ ያገኝበታል ብለዋል።
ሁሉም የእግዚአብሔር የሰው ልጅ የማዳን እቅድ በሙላት ማረጋገጥ ተልእኮ ተባባሪ እንዲሆን ካለ መታከት የውህደት የሰላም የመደጋገፍ መሣሪያ እንዲሆኑ ያቀረቡት ጥሪ፣ አፍሪቃውያን በሱታፌአቸው በጸናው እምነታቸው ተስፈኝነታቸው ጽኑ ለሕይወት ወንጌል ባላቸው ግብረ ታማኝነት ለአፍሪቃ የአጽናኝ ተስፋ ምልክት መሆኑ ቅዱስነታቸው ቀርበው ለመገንዘብ መቻላቸውም ገልጠዋል።
ከታዳጊ ወጣቶች እንዲሁም በተለያየ ችግር ምክንያት በስቃይ ላይ ከሚገኙት የአገሪቱ ክፍለ ኅብረተሰብ ጋር ባካሄዱት ግኑኝነት ቀርበው ያረጋገጡት የተስፋ ምልክት መሆኑም ጠቅሰው፣ በቅድስ ሪታ ቁምስና ከአዲስ ትውልድ ጋር ባካሄዱት ግኑኝነት፣ ከዚህ ክፍለ ኅብረተሰብ የመኖር ደስታ፣ ሓሴት ተስፈኛነት ቀርበው ለማጣጣም መቻላቸው ገልጠዋል። በዚህ የግኑኝነት አጋጣሚም ታዳጊ ወጣቶቹ በኡጋንዳ ወንጌላዊ ሕይወት ለመኖር በመሻቱ ምክንያት የደም ሠማዕትነት የተቀበለው ቅዱስ ኪዚቶ አብነት እንዲከተሉ አደራ እንዳሉዋቸው እና ኢየሱስ ክርስቶስን በወጣቶች መካከል ዘንድ እንዲመሰክሩት ምዕዳን እንዳቀረቡም በማስታወስ፣ ሰላም እና ደስታ የተሰየመው በእናቴ ብፅዕት ተረዛ ዘ ካልኩታ የተመሠረተው የደናግል ማኅበረ አባላት ልኡካን ደናግል የሚያስተዳድሩት ማእከል በመጎብኘት እዛው ከሚተዳደሩት ወላጅ አልባ የሆኑትን በተለያዩ በሽታዎች የተለከፉትን ሕፃናት ሁኔታ ቀርቤ ስመለከት እና ከእነርሱም ጋር ስገናኝ ፍቅር እና መተሳሰብ የአካል ድካም በሚታይበት ሥፍራ ሁሉ የሚገለጠው የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አፍቃሪነት እና ኃይል በግብር እንዲኖሩት እንዳደረጋቸው መስክረዋል።
በካህናት ገዳማውያን የዘርአ ክህነት ተማሪዎች ዓለማውያን ምእመናን ፊት ቀርበው ያረጋገጡት ሓዋርያዊ ጽናት እና ደስታ በቤኒን ላለቸው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ዋስትና ያለው ለተረጋገጠው ተስፋ ምልክት ነው ካሉ በኋላ፣ ለእነዚህ የቤተ ክርስትያን አባላት ለእውነተኛና ለኅያው እምነት በተቀደሰ ተግባር ለሚለየው የክርስትና ሕይወት በቤተ ክርስትያን ውስጥ በተጠሩበት ተልእኮት በውህደት እና በመካከላቸው በሚኖሩት ኅብረት በተለይ ደግሞ ካህናት ጥሪአቸው እንደ ማንኛውም የማኅበራዊ ግብረ ተልእኮ ሳይሆን እግዚአብሔርን ወደ ሰው ሰውን ወደ እግዚአብሔር ማቅረብ መሆኑ በማስገንዘብ ተቀዳሚ ኃላፊነት እንዳላቸው በማሳሰብ እንዲኖሩት ምዕዳን መለገሳቸው ገልጠዋል።
በቤኒን የአስፍሆተ ወንጌል አናሥር እና ለዚህ ተልእኮ ለሁሉም የእግዚአብሔር ፍቅር ለማቅረብ የገዛ ሕይወታቸውን በመለገስ እንዳንዴም የደም ሰማእትነት በመቀበል ጭምር የልኡካነ ወንጌል ተግባር ላይ በማተኮር ያስተነተነ ከቤኒን ብፁዓን ጳጳሳት ጋር ያካሄዱት ግኑኝነት ጥልቅ ውህደት የተመሰከረበት ሁኔታ እንደነበርም ገልጠው፣ በዚህ አጋጣሚም ለሁሉም ብፁዓን ጳጳሳት በቤተ ሰብ በቁምስናዎች በተለያዩ የቤተ ክርስትያን ማኅበረሰብ እና እንቅስቃሴዎች ያ ለመንፈሳዊ ኅዳሴ እና የእምነት ጥልቅ ግንዛቤ እንዲኖር የሚያበቃ ምንጭ የሆነው መጽሓፍ ቅዱስ ዳግም ማእከል ለማድረግ የሚያነቃቃ ሓዋርያዊ የመሪነት ብቃት እንዲኖራቸው ማሳሰባቸውም ቅዱስ አባታችን ገልጠው፣ ከዚህ ከታደሰው የእግዚአብሔር ቃል ማእከልነት እና እያንዳንዱ የተቀበለው ምሥጢረ ጥምቅት ላይ ከሚኖረው የታደሰ ግንዛቤ አማካኝነት ዓለማውያን ምእመናን በክርስቶስ ላይ ያላቸው እምነት እና ወንጌሉንም ጭምር በእለታዊ ሕይወታቸው እንዲመሰክሩ ኃይሉን ዳግም እንደሚያገኙ ማብራራታቸው አስታውሰዋል።
በዚህ ለመላ ክፍለ ዓለሚቱ መስቀለኛ በሆነ ወቅት፣ በአፍሪቃ የምትገኘው ቤተ ክርስትያን ወንጌልን ለማገልገል ካላት ቸርነት እና በግብረ ሠናይ የምታቀርበው የትብብር ምስክርነት አማካኝነት ተስፋ ለተሞላው ብሩህ ወቅት ዋነኛ ተወናያን ሆና ለመገኘት እንደምትችል ነው። በአፍሪቃ ለሕይወት እሺ ባይነት፣ አዲስ መንፈስ፣ ያለው የሃይማኖት እና የተስፋ መንፈስ ቀርበው በተግባር ያረጋገጡበት፣ የሆነው ሁሉ ወይንም ተጨባጩን ጉዳይ ተስፋን በሚያጨልም ከጥቅም አንጻር ወይንም በፋይዳኣዊነት ሥር የሚያይ ሳይሆን እግዚአብሔር ባለው ምሉእነት አማካኝነት መገንዘብ የሚለው ጠባይ ቀርበው ለመመልከት መቻላቸው ቅዱስ አባታችን ገልጠው፣ በዚህች ክፍል ዓለም ቤተ ክርስትያን እና ሁላችንም ጭምር ተስፋ የምናደርግበት ለሕይወት የተያዘ ቦታ እና መጪው ሕይወት የሚል ኅያውነት እንዳለ ገልጠዋል።
በዚህ በአፍሪቃ ባካሄዱት ሐዋርያዊ ጉብኝት አፍሪቃ መላ ኃይልዋ ወንጌልን ገና ወዳላወቁት እንዲደርስ ለሚያደርግ ተልእኮ ማስፈጸሚያ እንዲውል ጥሪ ማቅረባቸው ገልጠው፣ ይህ ደግሞ ማንኛውም ምሥጢረ ጥምቀት የተቀበለው ሁሉ እንዲፈጽመው እርቅ ፍትሕ እና ሰላም እንዲያነቃቃ የተጠራው የሚመለከተው የአስፍሆተ ወንጌል ተልእኮ ያለው የኃላፊነት ጥሪ ዳግም ማደስ ማለት መሆኑም አብራርተዋል።
ለማርያም የቤተ ክርስትያን እናት የአፍሪቃ እመቤታችን በዚህ በአፍሪቃ ባካሄዱት ሐዋርያዊ ጉብኝት የተገናኙዋቸውን ሁሉንም በማቅረብ። በአፍሪቃ የምትገኘው ቤተ ክርስትያን ለማርያም ድጋፍ ተማጥነው። “የማርያም እናታዊ አማላጅነት የእግዚአብሔር ፈቃድ ላይ ያተኮረ ልብ የተረጋገጠበት፣ የመለወጥ ጥረት ትደግፍ፣ የእርቅ መነሾ እቅዶችን ታጸና ዘንድ በዚህ የሰላም እርሃብ እና የፍትህ ጥማት በተሞላው ዓለም ለሰላም የሚደረገው ጥረት ተፈላጊው ውጤት የሚያስገኝ እንዲሆ ታድርግ” (አፍሪካ ሙኑስ- የአፍሪቃ ቃለ መሓላ, ቁ. 175) በማለት በማርያም አማላጅነት ጸልየው ከተለያዩ ከውስጥ እና ከውጭ አገር የመጡትን መእመናን በተለያዩ ቋንቋዎች ሰላምታን አቅርበው ሓዋራዊ ቡራኬ ሰጥተው ወደ መጡበት ሸኝተዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.