2011-11-21 16:36:37

የዓረብ ሊግ እና ሲርያ ፡


የአረብ ሊግ የአረብ ሀገራት ማሕበር የሲርያ ሁውከት እንዲገታ ያቀረበው የሰላም ጉዛ ካርታ እንዲሻሳል የሶርያ መንግስት መጠቅዋ እና ሊጉ ጥያቄውን ውድቅ ማደረጉ ተመልክተዋል።

የሶርያ መንግስት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋሊድ አል ሙዓለም የአረብ ሊግ ሶርያን ከሊጉ አባሮ የሰላም ጉዞ ካርታ እንዲሻሳል አለ መፈለጉ የምዕራብ ሀገራት መሳርያ መሆኑ ያሳያል በማለት አጥላልተው መተቸታቸው ከደማስቆስ ተገልጸዋል።

የአረብ ሊግ የሰላም ጉዞ የሶርያ ልዓላውነት የሚጻረር መሆኑ ዋሊድ አል ሙዓለም በተጨማሪ መግለጻቸው አብሮ የደረሰ ዜና ዘግበዋል ።

የሊጉ የሰላም ጉዞ ካርታ የሲርያ መንግስት ታንኮች ከሀገሪቱ ከተሞች ጐደናዎች እንዲወጡ ጠቅላላ የፖሊቲካ እስረኞች ነፃ እንዲለቀቁ ሲቪሎች ከማጥቃት እንዲቆጠብ ታዛቢዎች ሶርያ እንዲገቡ እንደሚጠይቅ የሚታወስ ነው።

የሲርያ መንግስት ሽብርተኝነት እየተዋጋች መሆንዋ የአረብ ሊግ ለማወቅ አልቻለም ወይም አልፈለገም ሲሉ የደማስቆ መንግስት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አጽንኦት ሰጥተው መግለጣቸው ap የዜና አገልግሎት አስገንዝበዋል።

የሀገሪቱ መሪ ፕረሲዳንት ባሻር አል አሳድ እስከ መጨረሻ ተዋግተው ለሕለፈት መዳረግ እንደሚመርጡ አስገንዝበው የምዕራብ መንግስታት በሲርያ ላይ ጣልቃ ከገቡ በክልሉ የመሬት ነውጥ ያስከትላል በማለት መግለጣቸው የዜና አገልግሎቱ አመልክተዋል።

በሌላ በኩል በወታደራዊ ኀይል ህዝብ ለማስተዳደር ስለማይቻል የሀገሪቱ መንግስት የሚቆጠር ግዜ ብቻ ይኖረዋል በማለት የቱርክ መንግስት ጠቅላይ ሚኒስትር ታዪፕ ኦርዶጋን መግለጣቸው ከአንካራ የመጣ ዜና አስታውቅዋል።

የብሪታንያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዊልያም ሄግ መንግስታቸው በሲርያ መንግስት ተጽዕኖ ማሳረፍ እንደሚቀጥል ጠቁመዋል ። ዛሬም የሲርያ መንግስት እየተፋለመ ያለው የሲርያ ብሔራዊ ምክር ቤት አባላት ተቀብለው ማነጋገራቸው ከላንደን ተመልክተዋል።

ምክር ቤቱ የሽግግር መንግስት እንደሚያቆም እና በአንድ ዓመት ውስጥ ነጻ ህዝባዊ ምርጫ ለማካሄድ ማቀዱ ይፋ መግለጫ መስጠቱ ታውቆዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.