2011-11-21 15:28:31

የቅድስት መንበር ርእሰ አንቀጽ፦ “የአፍሪቃ ተልእኮ”


ሁሌ በሳምት ማገባደጃ የቅድስት መንበር የዜና እና ማኅተም ክፍል ተጠሪ የቫቲካን ረዲዮ ዋና አስተዳዳሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ የሚያቀርቡት የቅድስት መንበር ርዕሰ አንቀጽ የአፍሪቃ ተልእኮ በሚል ርእስ ሥር በመቀጠል፣ አፍሪቃ በዚህ የተስፋ እና የእምነት ቀውስ በሚታይበት ዓለም RealAudioMP3 የተስፋ እና የእምነት እስትንፋስ መሆንዋ ያስገነዘበው የቅዱስ አባታችን ሐዋርያዊ ጉብኝት አፍሪቃ ለአፍሪቃ ልማት ከመሆን ይልቅ፣ ብዙዎች ለተለያይ የብዝበዛ እቅዳቸውን ለማራወጥ ለተለያየ ዘርፈ ችግር እንድትጋለጥ የሚያደረጋት የተፍጥሮ ብቻ ሳትሆን ሰብአዊ ባህላዊ እና መንፈሳዊ ሃብት የታደለች ክፍለ ዓለም ነች።
አስፍሆተ ወንጌል በአፍሪቃ፣ አፍሪቃ ስለ ክርስቶስ እና ለክርስቶስ ለምታከናውነው ተልእኮ እና ኃላፊነት፣ ዘርፈ ብዙ ችግሮችዋንም ጭምር የሚፈታ ብቻ ሳይሆን፣ የገዛ እራስዋ ጉዞ ዋነኛ ተወናያን እንዲትሆን የሚያበቃት መሆኑ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በአፍሪቃ ለምትገኘው ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን በሰጡት ድህረ ሲንዶስ ሐዋርያዊ ምዕዳን ዘንድ ተመልክቶ ይገኛል።
ቅዱስነታቸው በበኒን ተገኝተው የሰጡት ሥልጣናዊ አስተምህሮ መሪ ቃል እና በአፍሪቃ ለምትገኘው ካቶሊክ ቤተ ርክስትያን የለገሱት ድህረ ሲኖዶስ ሐዋርያዊ ምዕዳን፣ ተስፋ የተሰኘው ቃል በጋራ አካፋይ ያካተተ፣ ለፖለቲካ አካላት ለመንግሥት ባለ ሥልጣናት ያነጣጠረ ባቀረቡት ንግግር ጭምር ጎልቶ የታየው ተስፋ እና መጪው ብሩህ ተስፋ የሚል መሆኑ አባ ሎምባርዲ በርእስ አንቀጹ በማብራራት፣ ቤተ ክርስትያን የምታስተምረው ተስፋ፣ አገር እና ሕዝብ ራእያቸውን ወደ መንፈሳዊነት እና ዘለዓለማዊነት ያቀኑ ዘንድ የሚያሳብ ነው። በአፍሪቃ የምትገኘው ካቶሊክ ቤተ ርክስትያን በእግዚአብሔር ፈጣሪው ቅዱስ መንፈስ የተነቃቃች አፍሪቃዊነት የሚሰማት ነች በማለት ርእሰ ዓንቀጹን አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.