2011-11-21 15:25:19

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ፦ ከቅይጥ ውህደት የራቀ እውነተኛ እምነት


ህዳር 19 ቀን 2011 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን በኡዳህ በአገሪቱ የሁሉም ብፁዓን ጳጳሳት የጋራው የዘርአ ክህነት ቅዱስ ጋል መንበረ ጥበብ ከበኒን ዘርአ ክህነት ተማሪዎች ገዳማውያን ልኡካነ ወንጌል እና ዓለማውያን ምእመናን ጋር ተገናኝተው በሰጡት ሥልጣናዊ መሪ ቃል፣ እውነተኛው RealAudioMP3 ኅያው እምነት መኮትኮት ለተቀደሰው ክርስትያናዊ ሕይወት እና ለአዲስ ዓለም ሕንጸት ጽኑ መሠረት መሆኑ በማብራራት፣ የዘርአ ክህነት ተማሪዎች ገዳማውያን ልኡካነ ወንጌል እና ዓለማውያን ምእመናን በአፍሪቃ ሁሉም ምሥጢረ ጥምቀት የተቀበሉት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አንድ መሆናቸው የሚመሰከርባት ለአንዲት ለታደሰች እና ውህደት ለተረጋገጠባት ቤተ ክርስትያን ግንባታ የተጠሩ መሆናቸው በማስገንዘብ፣ ለተገለጸው እግዚአብሔር እና ለቃሉ ለቅዱሳት ምሥጢራቱ ለቤተ ክርስትያኑ ያለን ፍቅር ከእውነተኛው መንገድ የሚያርቅ መደናገር ለሚያስከትለው ቅይጥነት ፈውስ ነው። ይህ በቅድስት ሥላሴ ኃይል የሚንቀሳቀሰው እውነተኛው ፍቅር የባህሎች እውነተኛ እሴቶች እና የክርስትናው እምነት እሴቶች ቅን ውህደት እንዲኖራቸው ያግዛል፣ ከተለያዩ የሐሰት ሃይማኖቶች፣ ከምትሃተኝነት ከመናፍስትነት እና ከክፋት መንፍስ ሁሉ ነጻ የሚያወጣ ነው።
ብዙውን ጊዜ ስቃይ እና መከራ ቢፈራረቅብንም ገዳማውያን ለሱታፌ እና ወንጌል እንዲያበሥሩ የተጠሩ ናቸው። ይህ ደግሞ የእግዚአብሔር ፍቅር ቀናተኞች ምስክር እንዲሆኑ መጠራታቸው ያስገንዘባል። ክርስትያን የተቀበለው ብርሃን በገዛ እራሱ ለገዛ እራሱ ለማስቀረት ሳይሆን እንዲያንጸባርቀው እና ለሌላው እንዲያሳውቅ የተቀበለው ነው። ስለዚህ በሕይወታቸው ከወንጌል ጋር ባላችው የጠበቀ ትሥሥር እና ውህደት አማካኝነት ክርስቶስ እንዲታይ እና እንዲታወቅ ለማድረግ የተጠራችሁ፣ ለወንድሞቻችሁ ተጨባጭ ስጦታ ምሥጢረ ጥምቀት ለተቀበለው የምታነቃቁ ለእያንዳንዱ ሰው ግምት የምትሰጡ ናችሁ።
የተወደዳችሁ ዓለማውያን ምእመናን በእለታዊ ኑሮአችሁ የምድር ጨው እና የዓለም ብርሃት እንድትሆኑ የተጠራችሁ ናችሁ። ፍትሕ ሰላም እና እርቅ እንዲረጋገጥ የሚያደርጉት ጥረት ዳግም እንዲያድሱ አደራ በማለት፣ ይህ ተግባር በእግዚአብሔር እቅድ መሠረት ለሚጸናው ቤተሰብአዊ ክብር እና ለክርስትያናዊ ምሥጢረ ተክሊል ታማኝነት ይጠይቃል። እያንዳንዱ ቤተ-ሰብ እውነተኛ ቤተ ክርስትያን እንዲሆን ተጠርተዋል እንዳሉም የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።
በቅዱስ ጋል የዘርአ ክህነት መንበረ ጥበብ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የሰጡት ሥልጣናዊ አስተምህሮ በማስደገፍ የቲዮሎጊያ ሊቅ በዚያው መንበረ ጥበብ መምህር አባ አምብሮይሰ ደኦዳት ዙኖን ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ የቅዱስ አባታችን ሐዋርያዊ ጉብኝት የእግዚአብሔር ጸጋ ነው፣ በውሉደ ክህነት ብቻ ሳይሆን በሁሉም የቤተ ክርስትያን አባላት ዘንድ ፍቅርን እና እውነተኛ ውህደት እንዲኖር የሚያሳስብ ጨው እና ብርሃን ለመሆን የተቀበልነውን የክርስትና ጸጋ ክርስቶስን ለማሳወቅ ኃላፊነት እና አፍሪቃን ለማደስ መሠረት መሆኑ የሚያስገነዝብ መሪ ቃል ነው ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.