2011-11-18 17:23:30

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ በበኒን ሐዋርያዊ ጉብኝት ለማካሄድ ኮቶኑ ገቡ ፡


ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ 16ኛ በምዕራብ አፍሪቃ በምትገኘው በኒን ሐዋርያዊ ዑደት ለማከናወን ዛሬ ጥዋት ከሐዋርያዊ መንበራቸው ተንስተዋል።

በነዲቶስ 1ኛ በበኒን የሚያካሄዱት ሐዋርያዊ ጉብኝት ሃያ ሁለተኛ አገሮች አቀፍ ሐዋርያዊ ዑደት መሆኑ እና አፍሪቃ ሲጐበኙ ይህ ሁለተኛ መሆኑ አይዘነጋም።

ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ለስድስት ስዓታት በረው ከቀትር በኃላ በሀገሪቱ ሰዓት አቁጣጠር 15 ሰዓት ላይ ርእሰ ከተማ ኮቶኑ በርናርደን ጋንተን

ሀገራት አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ደርሰዋል ።

ቅድስነታቸው ካርዲናል በርናርደን ጋንተን አውሮፕላን ማረፍያ እንደደረሱ እዚያው ሲጠባበቅዋቸው የቆዩት በሀገሪቱ የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ወኪል የረኪበ ጳጳሳት ሊቀመንበር እና በርካታ የቤተ ክርስትያን ባለ ስልጣናት የበኒን መራሄ መንግስት ፕረሲዳንት ቶማስ ያዪ ቦኒ በርካታ ሚኒስትሮች እና ዲፕሎማቶች ደማቅ አቀባበል አድርጎውላቸዋል።

የበኒን ፕረሲዳንት ያዪ ቦኒ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረገ ሲሆን የቅድስነታቸው የበኒን ሐዋርያዊ ጉብኝት ከበኒን ብቻ ሳይሆን ለመላ አፍሪቃ አኩሪ መሆኑ እና በስማቸው እና በህዝብ ስም በነዲክቶስን አመስግነዋል። የተሰማቸው ጥልቅ ደስታ ገልጠው በበኒን ቆይታቸው መልካም ግዜ ተመኝተውላቸዋል።

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ 16ኛ ለተደረገላቸው ደማቅ አቀባበል እና ፕረሲዳንቱ ያሰሙት የእንኳን ደህና መጡ ንግግር አመስግነው እንደሚረዱት ለአፍሪቃ ክፍለ ዓለም እና ለበኒን ያለኝ ፍቅር አቢይ ነው ።

በሀገርዎ ሐዋርያዊ ዑደት ለማከናወን እችል ዘንዳ መንግስትዎ ረኪበ ጳጳሳት በኒን ላደረጋችሁልኝ ጥሪ ከልብ አመስግናለሁኝ ካሉ በኃላ እንደ አጋጣሚ ሆኖ የተያዝነው ዓመት በኒን ቅዱስ ወንጌል የተበሰረችበት መቶ ሐምሳኛ ዓመት በአንድ በኩል በሌላ በኩል ደግሞ ቅድስት መንበር እና በኒን በዲፕሎማሲ የተሳሰረችበት አርባኛ ዓመት በመሆኑ ደስ ይለኛል ብለዋል በነዲክቶስ 16ኛ ።

ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ በካርዲናል በርናርደን ጋንተን አውሮፕላን ማረፍያ ያደረጉት ንግግር በማያያዝ ፡ የድኅረ ሲኖዶስ ቃለ ምዕዳን እዚህ በኒን ውስጥ ለጳጳሳት አፍሪቃ እንዳስረክባቸው የነበረኝ ምኞት እውን መሆኑ ከሀሌ ኩሉ እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን ብለዋል።

በተጨማሪ ግላዊ ስሜት ሊሆን ይችላል የዚች የተባረከች በኒን ዜጋ ብጹዕ ካርዲናል በርናርደን ጋንተን መቃብር ለመጐብኘት ዕድል ማግኘቴ ደስ ይለኛል ካሉ በኃላ ከነፍሰሄር ብጹዕ ካርዲናል በርናርደን ጋንተን ተቋሞች በየፊናችን ለቅድስት ካቶሊካዊት ቤት ክረትያን አገልግሎት ሰጥተናል በማለት አመልክተዋል።

ብጹዕ ካርዲናል ጋንተን የተከበሩ እና የተወደዱ የቤተ ክርስትያን አገልጋይ መኖራቸው ጠቅሰው በኒን እንዲህ ያሉ መንፈሳዊ ዜጋ ማፍራትዋ የተመስገነች ትሁን ብለዋል።

በመጨረሻም የበኒን ቤተ ክርስትርያን ለሀገሪቱ ሕብረተ በትምህርት በጤና እና ማህበራዊ መስኮች የምይሰጠው አገልግሎት አመስግነዋል።

ዛሬ ከቀትር በኃላ በበኒን የሶስት ቀናት ሐዋርያዊ ዑደት ለማድረግ ዋና መዲና ኮቶኑ የገቡ ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ 16ኛ ከአውሮፕላን ማረፊያ አስራ ሁለት ኪሎ ሜትር ተጉዘው ከተማይቱ ውስጥ ወደ ሚገኘው ኪዳነ ምሕረት ካተድራል ተጉዘዋል በርካታ የቤተ ክርስትያን ባለስልጣናት እና ምእመናን ደማቅ አቀባበል አድሮውላቸዋል ። ቤተ ክርስትያኑ ውስጥ በመግባትም የምስጋና ሥርዓተ ጸሎት ፈጽመዋል። እዚያው ለተገኙ የቤተ ክህነት እና ምእመናን ንግግር አድርገዋል ።



በየኮቶኑ ኪዳነ ምሕረት ካተድራል ውስጥ የቀድሞ የከተማዩ ሊቀ ጳጳሳት የሊቀ ጳጳስ የብጹዕ አቡነ ኢሲዶረ ደ ሶዛ እና የሊቀ ጳጳስ የብጹዕ አቡነ ክሪስቶፍ አዲሙ መቃብሮች እንደሚገኙ ይታወቃል።

ቅዱስ አቦና ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ከካተድራሉ ወደ ምያርፉበት ቤተ ጵጵስና ሐዋርያዊ ወኪል ተጉዘዋል።

እኤአ በ2009 ወርሃ ጥቅምት ላይ እዚህ ቫቲካን ውስጥ የአፍሪቃ ቤተ ክርስትያን ለዕርቅ ሰላም እና ፍትሕ በተሰየመ መሪ ቃል ሁለተኛ የአፍሪቃ ጳጳሳት ሲኖዶስ መካሄዱ የሚታወስ ሲሆን ፡ ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ነገ ቅድሜ የድኅረ ሲኖዶስ ቃለ ምእዳን ለጳጳሳት አፍሪቃ እንደሚያስረክቡ የቫቲካን መገናኛ ብዙኀን ዘግበዋል። ሁለተኛ የአፍሪቃ ክፍለ ዓለም የጳጳሳት ሲኖዶስ መሪ ቃል የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል በማቴዎስ ወንጌል የተገለጠው “ እናንተ የምድር ጨው ናችሁ “ ,,, “እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ “ በሚል ቃል መካሄዱ የማይዘነጋ ነው።

የመጀመርያ የአፍሪቃ ጳጳሳት ሲኖዶስ እኤአ በ1994 ዓመተ ምሕረት የአፍሪቃ ቤተ ክርስትያን እና የ200 ዓመተ ምሕረት የስብከተ ቅዱስ ወንጌል ተልእኮዋ በሚል መሪ ሐሳብ መካሄዱ እና ሲኖዶሱ ነፍሰሄር ብጹዕ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ መሪነት መካሄዱ ይታወሳል ።

ይሁን እና ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዛሬ በበኒን የጀመሩት ሐዋርያዊ ዑደት በአህሪቱ ላይ ሰላም ዕርቅና ፍትሕ እንዲገኝ አስተዋጽኦ ያደርጋል ተብሎ ታምኖበታል።

የቢኒን ካሪታስ ተራድኦ ማሕበር ዋና ጽሐፊ እናት ለኦኒ ሐውርያዊ ጉብኝቱ ታሪኻዊ ከመሆኑ ባሻገር ተስፋ እና ሞራ ሰጭ መሆኑ በአጠቃላይ ለበኒን ህዝብ ደስታ ያፈለቀ ዓቢይ ፍጽሜ መሆኑ ጠቅሰው የቅዱስ ጰጥሮስ ተኪ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በመሀከላችን መገኘት ከፍተኛ መንፈሳዊ ጥንካሬ እና ኩራት ይቀሰቅሳል በገማለት መግለጣቸው ከኮቶኑ የመጣ ዜና ገልጠዋል።

በሌላ በኩል በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የቅድስት መንበር ቀዋሚ ታዛቢ የነበሩ ብጹዕ አቡነ ቸለስቲኖ ሚልዮረ አሁን በፖላንድ ዎርሶ ላይ የቅድስት መነብር ሐዋርያዊ ወኪል መሆናቸው የሚታውስ ሲሆን ፡ እዚያው የሚገኙ የአፍርቃ ሀገራት አምባሳደሮች አሰባስበው የበነዲክቶስ 16ኛ በኒን ጉብኝት ኣና ይዘታው ትኩረት የሰጠ ዓውደ ውይይት ማካሄዳቸው ከዎርሶ የደረሰ ዜና አመልክተዋል።

በብጹዕ አቡነ ቸለስቲኖ ሚልዮረ አመካይነት በውርሶ የአፍሪቃ ሀገራት መንግስታት ወኪሎች የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ በኒን ሐዋርያዊ ጉብኝት ለበኒን ቭቻ

ሳይሆን ለመላ አፍሪቃ ጠቃሚ አዎንታዊ እና ለሰላም እና መረጋጋት ያግዛል የሚል ስሜት እንዳሳደረባቸው ስብሰባው ከተካሄደበት ቦታ ከዎርሶ የመጣ ዜና ዘግበዋል።

በሌላ በኩል በበኒን የአላዳ ገዳም ዋና ተጠሪ አባ ሚኪኤለ ማሪያ ዮርዮ የቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ የበኒን ሐዋርያዊ ዑደት ትኩረት ሰጥተው መግለጫ ሲሰጡ እንዳመልከቱት ፡ በነዲክቶስ 16ኛ በኒን ውስጥ የሰው ሰብአዊ መብት ጥበቃ የሰብአዊ መብቶች ጥበቃ እና በማስመልከት የሚያደርጉ ንግግር አስፈላጊነቱ ዓቢይ መሆኑ እንዲሁም ከሕጻናት ጋር የሚያደርጉት ግኝኑነት በጉጉት እየተጠባበቁት ነው ።

በኒን እንደ አብዛኞዎቹ የአፍሪቃ ሀገራት ከድሃ ሀገራት የምትመደብ ሀገር ብትሆንም የመዳግ ሁኔታ እንደሚታይባት ከግጭት እና ሁአከት ነጻ መሆንዋ አባ ሚኪኤለ ማሪያ ዮርዮ መግለጻቸው ኮቶኑ ውስጥ የሚገኙ የራድዮ ቫቲካን ጋዜጠኞች የላኩት ዜና ዘግበዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.